TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለግል_መገልገያ_እንዲውሉ_ወደ_አገር_የሚገቡ_ወይም_ከአገር_የሚወጡ_ዕቃዎችን_ለመወሰን_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር.PDF
4.6 MB
#ጉምሩክ_ኮሚሽን

የግል መገልገያ እቃዎች መመሪያ ተሻሻለ።

የግል መገልገያ እቃዎች ወደሀገር የሚገቡበትን ሁኔታ የሚወስነው በስራ ላይ ያለው መመሪያ ለህገወጥ ንግድ በር የከፈተና የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ተፅዕኖ የፈጠረ በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 923/14 ተተክትቷል ሲል የጉምሩክ ኮሚሽን አሳውቋል።

ቀድሞ በነበረው መመሪያ ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው በመንገደኞች እንድገቡ የተፈቀዱ 102 አይነት እቃዎች ወደ 16 አይነት (84%) ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል።

ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ቢያንስ ለ12 ወራት ሲገለገሉባቸው የነበሩትን የግል መገልገያ እቃዎች ከቀረጥ ታክስ ነፃ ማስገባት ይችላሉ።

የግል መገልገያ እቃ በስጦታ የተላከለት ሰው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሌለው ከሆነ ከቀረጥና ታክስ በተጨማሪ 30% የገቢ ግብር ይከፍላል።

በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ ስጦታ መቀበል አይቻልም።

መመሪያው ከነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን እንደጀመረ ተገልጿል።

የመመሪያው ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተሽከርካሪዎች_ጨረታ_ጉምሩክ_ኮሚሽን_አዳማ_.pdf
ውዝግብ የፈጠረው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ !

" ' የጉምሩክ ኮሚሽን ' የገንዘብ ሚኒስቴርን ውሳኔ በመጣስ 237 መኪኖችን ለሐራጅ አወጣብን " - ከሰደት ተመላሾችና 10 የሚደርሱ የአገር ውስጥ አስመጪዎች

" በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በአግባቡ በተከተለ መልኩ ነው። ' ህጋዊ ስርዓቱን አልተከተለም ' በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ፤ #ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ እንጠይቃለን " - ጉምሩክ ኮሚሽን

ከሰሞኑን የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት ያወጣው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ውዝግብ የፈጠረ ሆኗል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ከሰደት ተመላሾችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ፤ " ጉምሩክ ኮሚሽን የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔን በመጣስ 237 ተሽከርካሪዎች ለሐራጅ አወጣብን " በሚል ከሰዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ ፤ " ምንም አይነት የህግ ጥሰት አልፈተፈፀም ህጉን እና አሰራሩን በተከተለ መልኩ ነው ተሽከርካሪዎቹ ለጨረታ የቀረቡት " ሲል አሳውቋል።

ያንብቡ 👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-24

@tikvahethiopia
#ጉምሩክ

° “ ጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን በደብዳቤ ሽሮ ከእጥፍ በላይ ቀረጥ ‘ ክፈሉ ’ እያለን ነው ” - አስመጪዎች

° “ ከአፈጻጸም አኳያ ምን ሊያስቸግረን ይችላል ? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” - ጉምሩክ ኮሚሽን

የጉምሩክ ኮሚሽን ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ምክንያት በማድረግ ከተቀመጠው አዋጅ ውጪ የቀረጥ ክፍያ እየጠየቃቸው መሆኑን አስመጪ ነጋዴዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል፡፡

ነጋዴዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

ጉምሩክ እስከዛሬ የሚሰራበት አዋጅ ነበር።

አዋጁ፣ ‘ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡም ሆነ ከአገር የሚወጡ እቃዎች የቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ የሚሰላው ስለእቃዎቹ የቀረበው የእቃ ዲክላራሲዮን በተመዘገበበት ቀን በብሔራዊ ባንክ የተገለጸውን የገንዘብ ምንዛሪ በመጠቀም ይሆናል ’ ይላል፡፡

ግን አዋጁን በደብዳቤ ሽረው ‘እቃው በተመዘገበበት ሳይሆን እቃው ከጉምሩክ መልቀቂያ ባገኘበት ቀን ባለው ሬት ተሰልቶ ልዩነቱን እንዲከፍሉ>’ የሚል አዲስ መመሪያ አውጥተዋል፡፡

አዋጅ በደብዳቤ ይሻራል ወይ ? ግን ሽረውት ቅሬታ ለማቅረብ ከዋና መስሪያ ቤት ስንሄድ የተወሰንን ነጋዴዎች ተሰባስበን ቅሬታ ለማቅረብ በነበርንበት ጥያቄችንን ሳይሰሙን ፌደራል ፖሊስ መጣ የተሰበሰበውን ሰው እንዳለ በመኪና ጭኖ ይዟቸው ሄደ ፤ ወደ 40 ነጋዴዎችን፡፡

አዋጅን የሚያክል ነገር በአንድ ደብዳቤ ተሽሮ፣ ' ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ክፈሉ ' የሚል አሰራር አመጡ፡፡

ሲቀጥል ጭማሪው እጅግ በጣም የተጋነነ ነው፡፡ በ57 ብር የተመዘገበን እቃ 100 በላይ ብር ክፈሉ እያሉ ነው፡፡ ከእጥፍ በላይ ነው የሚጠይቁት።

ለምሳሌ ፦ የቀድሞ የተመዘገበው ቀረጥ 2 ሚሊዮን ብር ከነበረ አሁን በእጥፍ 4 ሚሊዮን ብር ይሆናል፡፡ ጉምሩክ ያሉት ኦፊሰሮች እንኳ የሚሰሩበት ሲስተም የላቸውም፡፡ ' ዝም ብላችሁ አቻኩሏቸው ' ተብለው እቃችን እናዳለ ተይዟል ” ብለዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የነጋዴዎቹን ጥያቄና ቅሬታ ይዞ ለምን እንደዚህ ሆነ? ሲል የጠየቃቸው የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ተከታዩን ምላሽ ሰጥጠዋል፡፡

ምን አሉ ?

“ እንደሚታወቀው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ አስፈጻሚ ተቋማት የራሳቸውን ሚና አላቸው፡ አንዱ አስፈጻሚ ተቋም ጉምሩክ ኮሚሽን ነው፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ ህጎችን ያስፈጽማል፡፡ አንዱ የብሔራዊ ባንክ ጋር ተያይዞ ያሉ ህጎችን የሚያስፈጽም ነው፡፡

በምን መልኩ መስተንግዶ መሰጠት እንዳለበት ውይይቶች ሲደረጉ ቆይቶ ነበር፡፡ ያ ሰርኩላር ከዛ ጋር በተያያዘ ነው የመጣው፡፡ ሰርኩላሩ አጠቃላይ ነገሮችን የያዘ ነው፡፡

ከተጠቀሱት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አስመጪዎች ዋናው መስሪያ ቤት (አዲስ አበባ) አካባቢ ቅሬታውን ለማሰማት እንደመጡ ሰምቻለሁ፡፡

ከምን አንጻር ነው ይሄ ሰርኩላር ? ለሚለው ተጨማሪ ውይይቶች የሚያስፈልጉ ከሆነ ውይይቶች እየተደረጉ ነው፡፡ አጠቃላይ ሰርኩላሩን አንልም ሰርኩላሩ ተፈጻሚ ነው የሚሆነው፡፡ ግን ያነሷቸው ጉዳዮች ታይው ምላሽ ይሰጣል፡፡

በኋላ ብዙ አመጪዎችን ማወያየት እንደተቻለም ከአመራሮች ያገኘሁት መረጃ አለ፡፡

ግን አንዳንዴ እንዲሁ በጋራ መጥቶ አቤቱታዎችን የማሰማት ሁኔታዎች ሲኖሩ እዚያ አካባቢ ያሉትን ነገሮች ጸጥታ የማስከበር ሥራዎች ተሰርተው ሊሆን ይችላል፡፡

በኋላ ላይ ግን የተወሰኑ አስመጪዎችን በማናገር ያላቸውን ቅሬታ ኮሚሽኑ እንደሚያየው፣ ተገቢነት ያለው ከሆነ ሊፈታ፣ ከህግ አንጻር የሚያስኬድም ከሆነ በዚያው ሊቀጥል የሚችልበት እድል እንዳለ ነው የሰማሁት፡፡

አስመጪዎቹ የሚያነሳቸውን ጉዳዮችን ኮሚሽኑ ተረድቷል፡፡

ከህግ አንጻር ምን መሆን ነው ያለበት ? ከአፈጻጸም አኳያስ ምን ሊያስቸግረን ይችላል? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ጉዳዩ ከምን እንደሚደርስ ኮሚሽኑን ጠይቆ ምላሽ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ ° “ ጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን በደብዳቤ ሽሮ ከእጥፍ በላይ ቀረጥ ‘ ክፈሉ ’ እያለን ነው ” - አስመጪዎች ° “ ከአፈጻጸም አኳያ ምን ሊያስቸግረን ይችላል ? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” - ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ምክንያት በማድረግ ከተቀመጠው አዋጅ ውጪ የቀረጥ ክፍያ እየጠየቃቸው መሆኑን አስመጪ ነጋዴዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል፡፡…
#ጉምሩክ

➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች

➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን

አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡

ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅነው የጉምሩክ ኮሚሽን፣ “ አስመጪዎቹ የሚያነሳቸውን ጉዳዮችን ኮሚሽኑ ተረድቷል፡፡ ከህግ አንጻርም ምን መሆን ነው ያለበት ? ከአፈጻጸም አኳያስ ምን ሊያስቸግረን ይችላል ? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር፡፡

አስመጪዎቹ ዛሬስ ምን አሉ ?

“ ምንም የተቀየረ ነገር የለም፡፡ አሁንም ከዶላር ጭማሬው በፊት ለተመዘገቡት እቃዎች መፍትሄ አልተሰጠም፡፡ ወቅታዊ ስራ እያለፈን ነው፡፡ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው፡፡

በሌላ በኩል ፥ ለተማሪዎች መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች አሉን፡፡ ይህ ጊዜ አለፈን ማለት እቃው ለአንድ ዓመት መጋዘን ነው የሚቀመጠው፡፡ ብዙ ጊዜ የሚያልፍባቸው ዕቃዎችም ይኖራሉ ምግብ እና መድኃኒቶች ” ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ትላንትና (ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ/ም) የተወሰነ ማሻሻያ አድርጎ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም ወዲህ ለተመዘገቡት እቃዎች መልቀቂያ እንዲሰጥ በቃል ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ፤ ነገር ግን ‘ ከጉምሩክ ፕሮሰስ ደብዳቤ ነጻ ነህ ’ ተብሎ መልቀቂያ የሚሰጥበት ክፍል ‘ ደብዳቤ አልደረሰኝም ’ እያለ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ውይይት ማድረጉን መግለጹ መልካም ሆኖ እያለ፣ ለውሳኔ በዘገዬ ቁጥር ብዙ አሉታዊ ተፅዕኖዎች እንደሚደርሱባቸው ገልጸው፣ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ በሰጡን ምላሽ፣ “ ኮሚሽኑ እየሰራበት ነው በጉዳዩ ላይ፡፡ ምናልባት ነገ ምላሽ ይሰጣል፡፡ ሌላው ጉዳይ ካልዘገዬ በስተቀር ነገ (ነሐሴ 10) ምላሽ ይሰጣል ብዬ ኤክስፔክት አደርጋለሁ ” ብለዋል፡፡

“ ነገ ጠብቁ ፣ ብቻ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ብዬ ነው ኤክስፔክት የማደርገው ” ነው ያሉት።

(አስመጪዎቹን ቅር ያሰኘው የኮሚሽኑ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጉምሩክ

(አስመጪዎች)

" በኢንቮይስ ያልተከፈሉ አሉ። ብዙ እቃዎች ናቸው ያሉት። እቃዎቹ አንድ ላይ ጉምሩክ የገቡ ናቸው።

የነዛና የነዚህ ልዩነት በጣም ሰፊ ነው። ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን በኮንቴነር ጭማሪ የሚያመጡ ናቸው።

እነዚህም አብረው የሚስተናገዱበት መንገድ መኖር አለበት።

እቃዎቹ ሰሞኑን የታሪፍ ፣ የቀረጥ ለውጥ ሁሉ ተደርጎባቸው ነበር። በአንድ አይተም እስከ 10 ዶላር ጭምር ተደርጎ ነበር ከሬት ውጭ እሱ ላይ ብዙ ቅሬታ አልነበረም ሁሉም አንድ ላይ ስለጨመረበት።

አሁን ላይ እቃው አብሮ ገብቷል። እነዚህ ኢንቮይስ ከፍለዋል። እኛ በኢንቮይስ አልከፈልንም። ተመሳሳይ እቃዎች ናቸው።

የእነሱ ይውጣ ፤ እናተ ደግሞ በአዲሱ ሬት ክፈሉ ብንባል በጣም ትልቅ ልዩነት ይኖራል። በአንድ ገበያ ላይ ተወዳድሮ ለመስራት የሚቻል አይደለም።

ጉምሩክ ይኔንም ስጋታችንን ቢይይልን።

ሁለት ቦታ ተከፍለናል ፤ በኢንቮይስ የከፈሉ አሉ በኢንቮይስ ያልከፈልን አለን። ልዩነቱ ብዙ ነው በሚሊዮኖች ነው።

አንድ ገበያ ላይ  ነው የምንሰራውና እኛንም ከገበያ እንዳያስወጣን ይሄም ይታይልን። "

#CustomsCommission

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው። በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው…
#ጉምሩክ🚨

" አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች አስወጡ !! " - ጉምሩክ

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፦

" መንግስት ያወጣውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መደረጉ ይታወሳል።

በመሆኑንም ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ሰነዱ ተቀባይነት ባገኘበት እለት በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ  ይደረጋል።

ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በኋለ ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ደግሞ በአዲሱ የውጭ የምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ  መሰረት በየእለቱ በሚኖረው የምንዛሬ ተመን ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ባለመገንዘብ የተነሳ እቃዎችን በደረቅ ወደብ ያከማቹ አስመጭዎች አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች ሊያስወጡ ይገባል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመተላለፍ እቃዎችን በደረቅ ወደቦች ያላግባብ በማከማቸት በገበያ ላይ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን። "

#EthiopianCustomsCommission

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ሞጆ ቅርንጫፍ እየተጉላላን ነው። ትላንት የተላከውን ደብዳቤ ስራ አስኪያጅ ‘አልመራበትም’ ተብሎ ” - አስመጪዎች “ ደብዳቤው ትላንትና ከመሸ ነው እኛ ጋ የደረሰው ከዋና መስሪያ ቤት፡፡ ተመርቶ ለሚመለከተው ክፍል ሰጥጠናል ” - ሥራ አስኪያጅ ክፍሉ አስመጪዎች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በጉምሩክ እያጋጠማቸው ስላለው ሁኔታ ፤ ክፈሉ ስለተባሉትም ከፍተኛ ቀረጥ በተመለከተ ለቲክቫህ…
#ጉምሩክ

" ሰርኩለሩ በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " - አስመጪዎች

በርካታ የመኪና አስመጪዎች ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አስመጪዎቹ በጋራ ፈርመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባላኩት ደብዳቤ ፤ " መንግስት በሀምሌ 22/2016 ዓ.ም በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ ያስተላለፈው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከዚህ በፊት የነበሩ ውስብስብ የንግድ መዛባቶችን እና ብሮክራሲዎችን እንደሚያስቀር እንተማመናል " ብለዋል።

ነገር ግን የኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ነሐሴ 03/2016 እና ነሐሴ 10/2016 ያወጣቸው ሰርኩላሮች ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

" ይህም ሰርኩላር ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ከግምት ውስጥ ያላስገባ እና ከጉምሩክ ትራንዚት እና መጋዘን አስተዳደር የሚጣረስ በመሆኑ ነው " ብለዋል።

አስመጪዎቹ " የኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር FXD/01/2024 ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን ከ22/11/2016 በፊት የተመዘገቡ እና ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች ላይ በደብዳቤ ቁጥር 4/0/04/17 ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ስርኩለት የተላከ ሲሆን ነገር ግን ሰርኩለር በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " ነው ብለዋል።

ጉዳዩን ሲያብራሩም ፦

" በጉምሩክ ደንቡ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው የቀረጥ ማስከፈያ የሚወሰነው ዲ/ዬን. በተመዘገበበት እለት ያለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ተመን በመጠቀም ነው።

ይህ ማለት በዮኒሞዳል አሰራር ሕጋዊ ዶክሜንት አሟልተን ዲ/ዬን ሞልተን ክፍያ ፈፅመን ሰነዱን የተሟላ መሆኑን ለጉምሩክ ኦፊሰር ተረጋግጦ ትራንዚት ተፈቅዶልናል፡፡

ትራንዚት ካስፈቀድን በኋላ ደግሞ ሕጉ በሚፈቅደው በአንድ ወር የትራንዚት ጊዜ ገደብ ውስጥ ኘሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን ወደ አገር ውስጥ አስገብተናል የጉምሩክ ሪስክ የሚጣለው ደግሞ እቃዎቹ አገር ውስጥ / መድረሻው ጣቢያ / ሲደርሱ መሆኑን ከግምት ያላስገባ ውሳኔ ነው።

እቃዎቹ ተጓጉዘው በድሬዳዋ መስመር /ደወሌ/ ለሚገቡ በድሬዳዋ ድልድይ ተሰብሮ ከ3 ሳምንት በላይ መቆማቸው ግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ ነው " ብለዋል።


" የጉምሩክ ኮሚሽን ከላይ የተገለጸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአስቸኳይ የውሳኔ ማሻሻያ እንዲደረግልን እና በአዋጁ መሰረት እንድንስተናገድ " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ፤ " ጉምሩክ  ኮሚሽን አዋጅን በሴኩላር በማሻር የማይሆን ስራ እየሰራ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀረቡ አስመጪዎች አሁንም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሴኩርላር ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም።

አሁንም ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ አስገንዘበዋል።

ጉዳዩ  በገበያና ስራው ላይ ሚያመጣውን ከፍተኛ ተፅእኖ በመረዳት እውቀትን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ በውይይት መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#Customs #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ " ሰርኩለሩ በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " - አስመጪዎች በርካታ የመኪና አስመጪዎች ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አስመጪዎቹ በጋራ ፈርመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባላኩት ደብዳቤ ፤ " መንግስት በሀምሌ 22/2016 ዓ.ም በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ ያስተላለፈው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከዚህ በፊት…
#ጉምሩክ

🔴 “ በኢንቮይስም ከፍለን እቃው በገባበት ቀን ነው የምንሰራላችሁ አሉን ” - አስመጪዎች

⚫️ “ በሁሉም ጉዳይ አቤቱታ ይቀርባል አቤቱታ የቀረበበት ሁሉ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሁኔታ አይኖርም” - ኮሚሽኑ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከማክሮ ኢኮኖሚ ፓሊሲ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ባወጣው አዲስ መመሪያ "ከእጥፍ በላይቀረጥ ክፈሉ'' እየተባሉ መሆኑን አስመጪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ኮሚሽኑም ከቅሬታው በኋላ ማሻሻያ ማድረጉን መረጃ ነግረናችሁ ነበር።

ሆኖም ከ150 በላይ የሚሆኑ “ በኢነቮይስ ከፍለናል ” የሚሉ አስመጪዎች፣ ኮሚሽኑ ከማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራወሰ በኋላ ያወረደውና በአስመጪዎች በኩል “ አዋጅን በደብዳቤ ሽሯል ” በሚል ቅሬታ ቀርቦበት ኮሚሽኑ በድጋሚ ማሻሻያ አደረኩበት ያለው ደብዳቤም ቅሬታቸውን እንዳልፈታላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

በዚህም እንዲያወያያቸው ጭምር ኮሚሽኑን በደብዳቤ እንደጠቁ ሆኖም ምላሽ እንዳልጠሰጣቸው ገልጸው፤ ጉዳዩን በድጋሚ እንዲያጤነው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስበዋል።

አስመጪዎች በዝርዝር ያቀረቡት ቅሬታ ምንድን ነው ?

“ ደብዳቤው (ማስተካከያ የተደረገበት) መልስ ስላልሰጠን መልሰን ደብዳቤ ፃፍንላቸው፡፡ ምክንያቱም ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ በፊት የገቡ እቃዎች እንዲስተካከሉ ተብሎ ብዙዎቹም አውጥተዋል፡፡

የእኛ ጥያቄ፤ ቅድሚያ እቃው ዶኩሜንት እንደደረሰን ጂቡቲ ላይ እንዳለ በኢንቮይስ ዲክላራሲዮን ይቆረጣል። ጂቡቲ ጭነት ሊዘገይ ስለሚችል ፤ በየሳምንቱ ደግሞ ሬት ስለሚቀይር ያንን ነገር እንዳይነካው ሁሉም ነጋዴ ከዚህ በፊት ለዓመታት የሰራው በዚህ አይነት አካሄድ ነው፡፡

እቃው ጂቡቲ እያለ ዶኩሜንቱ ከመጣ በኢንቮይስ ይከፈላል። ቀሪ ሂሳብ ደግሞ ከፍተሻ በኋላ 'ይለቀቅ' ሲባል ያኔ ተከፍሎ ይመጣል፡፡ አሁን ግን በኢንቮይስም ከፍለን 'እቃው በገባበት ቀን ነው የምንሰራላችሁ' አሉን፡፡

እኛ ደግሞ አልተስማማንም፡፡
ጉምሩክ  በገባበት ሳይሆን ዶኩሜንት ባስገባንበት፤ ዲክራላሲዮን ባስቆረጥንበት ነው መስተናገድ ያለብን፡፡ 5 ሚሊዮን ስንከፍል የነበርነው 10 ሚሊዮን፣ 10 ሚሊዮን ይከፍል የነበረ 20 ሚሊዮን ብር ከፈሉ እየተባልን ነው፡፡

አሁን ጠዋት አንድ ሬት ከሰዓት ሌላ ሬት አለው
ጉምሩክ፤ ድሮ ግን በየሳምንቱ አንድ ሬት ነበረው፡፡ ሐሙስ ቀን የሚቀየር ሬት ብቻ ነበር የሚሰጡት፡፡

ይህ ደግሞ ኪሳራና ተጠቃሚውም ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚጣመጣበት ጉምሩክም ይገነዘባል፡፡ ይህን ነገር ቢያስተካካል ባለው ዋጋ መሸጥ ይቻላል ”
ነው ያሉት፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለቀረበው ቅሬታ የኮሚሽኑ ምላሽ ምንድን ነው ? ኮሚሽኑ ባለፈው አደረኩት ባለው ማሻሻያ የአሁኖቹ ቅሬታ አቅራቢዎችን ጉዳይ አካቶ ምላሽ ሰጥቷል? ከሆነ እንዴት ? ሲል ጉምሩክ ኮሚሽኑንን ጠይቋል።

የኮሚሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ኮሚሽኑ የተለዬ ምላሽ የለውም ከዚያ ጉዳይ ጋር በተያያዘ። የተሰጠው ምላሽ ሁሉንም ጉዳዮች ከቨር ያደረገ ስለሆነ ቀደም ሲል በወጣ ደብዳቤ ምላሽ የተሰጠበት ጉዳይ ነው፡፡

የተለዬ ኮሚሽኑ የሚያየው ጉዳይ የሌለ መሆኑን ነው የማውቀው። ሁሉም ጉዳዮች እዛ ላይ ቴኪኒካሊ ከጉምሩክ አዋጅ አንጻር ታይተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

አጠቃላይ ነው ባለፈውም አቤቱታ የቀረበው፡፡ ስለዚህ ምላሽ የተሰጠበት አግባብ አለ፡፡ በሁሉም ጉዳይ አቤቱታ ይቀርባል አቤቱታ የቀረበበት ሁሉ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሁኔታ አይኖርም፤ ይታወቃል።

'መስተናገድ የለብን በዚህ የሚል ጉዳይ' ካለ ኮሚሽኑ የሰጠውን ምላሽ መቃወም መብት ነው። ተራ ቁጥር 1፣ 2፣ 3፣ 4 በሚሉ ተራ ቁጥሮች ላይ ተገልጿል፡፡

የተቀመጡት ኮንዲሽኖች ጂቡቲ ላሉት እቃዎች፣ አገር ውስጥ ላልገባ እቃ በነባሩ የውጭ ምንዛሪ እንስተናገድ ነው ጥያቄያቸው። ያነም ኮሚሽኑ ደብዳቤው ላይ በገለጸው ልክ (ተራቁጥር አራት ይመስለኛል) በግለጽ የተቀመጠ ጉዳይ ነው።

እነርሱ አቤቱታቸውን መቀጠል ይችላሉ፤ ኮሚሽኑ እኮ ከዚህ አንጻር የከለከለው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ የተሰተው ምላሽ ይሄው ነው ከዚያ ውጪ የተለየ የሚሰጥ ምላሽ የለንም በዚያ ደብዳቤ ተመልሶ ያለፈ ጉዳይ ስለሆነ”
ብለዋል።

#TikvahethiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia