TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን⬆️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን #በስራ እንቅስቃሴዎቻቸው ጎልተው በመውጣት ከተጠርጣሪዎች #የገንዘብ መደለያ #አንቀበልም ሲሉ ለህግ በማቅረብ ለሰሩት #አኩሪ ተግባር ለአመራርና ለአባላቱ የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውና በአይነቱ የተለየ #የመልእክት እና #የገንዘብ መላላኪያ የስልክ መተግበሪያ በትላንትናው እለት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተመርቆአል። ይህ 'ሜዳ ቻት' የተሰኘ መተግበሪያ #360_ግራውንድ በተባለ ሀገራዊ ድርጅት የተሰራ ሲሆን በአማርኛ, በኦሮምኛ, በትግርኛ እና በኢንጊሊዘኛ ቻት ማድረግ ያስችላል። የገንዘብ መላላኪያው አዲሱን የዳሽን ባንክን አሞሌ ኦንላይን ገንዘብ የሚጠቀም ሲሆን Wechat እንደተሰኘው የቻይናዊውያን መተግበሪያ ገንዘብን ልክ እንደመልክት እጅግ በቀለለ መልኩ መላክ እና መቀበል ያስችላል። ሜዳ ቻት በየቀኑ የሚያሸልም ጨዋታ, በርካታ ሀገራዊ ስቲከሮች እና ሌሎችም አገልግሎቶችን የያዘ ሲሆን መተግበሪያውን ለመስራት ከሶስት አመት በላይ ፈጅቷል።

ምንጭ፦ ብሩክ(ከሜዳ ቻት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን ዲጂታል የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ባንኩ #ወርልድ_ሪሚት ከተሠኘው ዓለም አቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ዲጂታል ዓለም አቀፍ #የገንዘብ_ማስተላለፊያ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች #ተፈናቅለዋል፡፡›› የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
.
.
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሠጠው መግለጫ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ክልሉ 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲደረግ ቢቆይም አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ እንደሆነ ገልጻል፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል፡፡ በአማራ ክልልም ከክልሉ ውስጥና በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንዳሉት ከክልሉ ውጭ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ደግሞ በተለይም በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች ዜጎች በስፋት ተፈናቅለዋል፡፡

የመፈናቀል አደጋው ከተከሰተበት በተለይም ከሕዳር ወር ጀምሮ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት በጋራ ተፈናቃዮችን በጊዜያዊና በዘላቂነት ለማቋቋም 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ አሰማኸኝ ‹‹አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ ሆኗል›› ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለሰፋ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች በመጋለጣቸው ዘላቂ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የክልሉ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፤ ‹‹ድጋፉ በተደራጀ እና በአንድ አግባብ እንዲሆን ይፈለጋል›› ሲሉም አሳበዋል፡፡

የሚደረገው ድጋፍ በገንዘብ፣ በዓይነት እና በዕውቀት ሊሆን እንደሚችል ያስረዱት አቶ አሰማኸኝ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን በተከፈተው የሒሳብ ቁጥር ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#የገንዘብ_ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ፕሮግራሞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000258250811 እንዲሁም በዓይነት ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ አካላት በስልክ ቁጥሮች 0582180196፣ 0582181096፣ 0582181151፣ 0918701136፣ 0918340128 ወይም 0953600333 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር አብይ አህመድ በ29 ቢልዮን ብር ለሚከናወነው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት የሚውል #የገንዘብ_ማሰባሰብያ ፕሮግራም በቅርቡ በቤተ- መንግስት እንደሚያዘጋጁ ተነግሯል። በፕሮግራሙ ላይ 1,000 ሰዎች ይጋበዛሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን አንድ እራትም 5 ሚልዮን ብር ያወጣል ተብሏል። በፕሮግራሙ ላይም ከሀገር ውስጥ፣ ከመላው አፍሪካ እንዲሁም ከቻይና እንግዶች ይጋበዛሉ ተብሏል። ውጥኑ ከተሳካ ጠ/ሚሩ 5 ቢልየን ብር ለፕሮጀክቱ ማሰባሰብ ይችላሉ ማለት ነው።

ምንጭ፦ ዮናስ አለማየሁ (ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገፅ የተወሰደ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለአምባ መርጃ ማህበር ቤት ለመስጠት ቃል ገቡ!

ኢ/ር ታከለ ኡማ በዛሬው ዕለት አምባ ትምህርት ለተቸገሩ መርጃ ማህበርን ጎብኝተዋል፡፡ ከ9 ዓመት በፊት በተለያዩ ህፃናት ማሳደጊያዎች አድገው በተለያዩ ስራዎች ላይ በተሰማሩ ግለስቦች የተቋቋመው ማእከሉ ወላጅ አልባ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ አካል ጉዳተኛ ህፃናትን ተቀብሎ #የምገባ አገልግሎትን ያካተተ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ማእከሉ ባጋጠመው #የገንዘብ_እጥረት የቤት ኪራይ ለመክፈል መቸገሩን እና ሊዘጋ መቃረቡን የተመለከቱት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ማእከሉ ባለበት አካባቢ የሚገኝ እና ለበርካታ ዓመታት ተዘግቶ የተቀመጠ ቤት ለማእከሉ በስጦታ ለማስረከብ ቃል ገብተዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ መሰል ትውልድ ላይ የሚሰሩ ማእከላትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- የከንቲባ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia