TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያደረገውን #ክትትል መሰረት በማድረግ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ A 77608 በሆነ «አቶዝ» የቤት መኪና በባለሙያ በመፍታት ወደ አዲስ አበባ የገባ አራት መትረየስ ጠብመንጃዎች ጥር 28 ቀን 2011 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አዲሱ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ትብብር መሳሪያው ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

የጦር መሳሪያ ዝውውሩ እየተራቀቀ መምጣቱን ኮሚሽኑ ገልፆ አሁን በቁጥጥር ስር የዋለው የጦር መሳሪያ የመኪናዋን አካል በባለሙያ በመፍታት ፍፁም በማያስጠረጥር ሁኔታ መሳሪያዎቹ ተደብቀው የተገኙ ሲሆን ሁለት የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ባዶ ካርታ እና የሌላ ተሸከርካሪ የፊትና የኋላ ሰሌዳ እንዲሁም 47 ሺ የአሜሪካ ዶላር እንደተያዘ ኮሚሽኑ ከላከው ዘገባ መረዳት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ዜና ከአማራ ብሄራዊ ክልል አዊ ዞን እንጅባራ ወረዳ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 53119 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ #ከከሰል ጋር በመጫን 46, 404 ልዩ ልዩ የሽጉጥ ጥይቶች ወደ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ/ም ከለሊቱ 9፡20 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው #አጂፕ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባከናወኑት ተግባር ጥይቱን ከሦስት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡

የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ልዩ ልዩ ስልቶችን በመጠቀም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ስጋት ውስጥ ለመጣል እየሰሩ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቆ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ህገ-ወጥ ተግባር በማጋለጥ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካለት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ተቋማቱ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia