TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace
የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሃይማኖት ተቋማት እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አድርገው ነበር።
በዚህ ውይይት ላይ ምን አሉ ?
- የሰላም ስምምነቱ #የህዝብ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።
- የሰላም ስምምነቱ ፤ ከፍተኛ የሆነ ችግር ላይ ያለውን ህዝብ ለማዳንና ህዝቡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲጠቀም ሰላም እንዲያገኝ ለማድረግ የተደረሰ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ጉዳዮች በህገመንግስት መሰረት ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚፈለግላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ስምምነቱ ከምንም በላይ ተኩስ የማቆም ጉዳይ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
- የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት ላይ አሁንም የኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ኃይል በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ እየፈፀመ፣ ንብረት እየዘረፈ ፣ እያወደመ መሆኑና ስምምነቱ እንዲደናቀፍ እየሰራ እንደሆነ ገልፀው የፌዴራል መንግስት የህዝቡን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነበት ስላለበት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
- በስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ እርዳታ እና መድሃኒት እየገባ መሆኑን ተናግረዋል። " ስምምነቱ ላይ ድጋፍ በአቸኳይ እንዲገባ የሚል ነገር ነበር በወቅቱ ወዲያው የገባ ድጋፍ አልነበረም አሁን ግን ቀስ በቀስ የሚገባው ሰብዓዊ ድጋፍ እየጨመረ ነው " ብለዋል። እህል እና መድሃኒት ይዘው የሚገቡ ተሽከርካሪዎች እየጨመሩ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ ዓለም አቀፍ እርዳታ አቅራቢዎች በሙሉ ወደ እንቅስቃሴ ገብተዋል ብለዋል።
- ወደ ክልሉ ከሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ በስምምነቱ መጀመሪያ ሰሞን ላይ አስፈላጊው ስራ በጊዜ ስላላለቀ እና ባለመዘጋጀቱ ወደ ትግበራ እንዳልተገባ አሁን ላይ ግን ሁሉም ዝግጁ መሆኑን ፣ የሚያደናቅፍ ነገር እንደሌለው ፣ በመንገድ ላይ የነበረው በርካታ ፍተሻና የቁጥጥር ጣቢያዎች አሁን መስተካከሉን ተናግረዋል።
- ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ፤ " የተቋረጡት መሰረታዊ አገልግሎቶች መልሰው አልተከፈቱም " ያሉ ሲሆን " በኛ በኩል ሙሉ ዝግጅት አድርገናል #ባንክ፣ #ቴሌኮም እንዲጀምር ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለን አነስተኛ አቅም እየተጠቀምን ብንቆይም መስተካከል ያለባቸው ነገሮች መስተካከል አለባቸው። በፌዴራል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ እያንዳንዳቸው ተፈትሸው ስራ ለመጀመር ምን ያስፈልጋቸዋል ? የሚለው ተጠንቷል። አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል ፤ አሁን የሚቀረው ስርዓት አስይዞ ከፌዴራል አገልግሎት ሰጪ አካላት ጋር በመነጋገር በቅደም ተከተል ማስፈፀም ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia