TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥምቅት 30/2017 ወደ ቤታችሁ ግቡ ፤ ይህ ካልሆነ የሽያጭ ውሉ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ለቤት ተጠቃሚዎች በዕጣና በጨረታ የሚያስተላልፈው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " በሽያጭ ከተላለፉና ውል ከተፈጸመባቸው ቤቶች መካከል የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ገብተው…
" እስከተባለው ጊዜ ካልገባችሁ በዕጣና በሽያጭ ነው ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፈው " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ ውል የሚቋረጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማስጠንቀቁ ይታወሳል።

ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ማስተላለፉ አመልክቷል።

" በተለያዩ ጊዜያት በሽያጭ ተላልፈው የቤት ባለቤቶች  ውል የተዋዋሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸው እና ለፀጥታ ስጋት እየሆኑ ይገኛል " ብሏል።

ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ  የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው እንደሚቋረጥ ገልጿል።

ውል ከተቋረጠ በበኃላ #በዕጣ እና #በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፍ ነው ኮርፖሬሽኑ ' ለመጨረሻ ጊዜ ' ሲል ያስጠነቀቀው።

@tikvahethiopia