TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፈተና መቼ ይሰጣል ?

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል።

ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው።

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው።

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል።

በሌላ በኩል ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሬሜዲያ ተማሪዎች ከታህሳስ ወር ጀምሮ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።

ተማሪዎቹ የትምህርት ጊዜያቸው እያለፈ እንደሆነና አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅሬታ አቅርበዋል።

70% ፈተናው በሰኔ ወር ይሰጣ መባሉ ደግሞ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
- የነዚህ ልጆች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?
- ከዚህ በኃላ መቼ ተጠርተው ተምረው ለፈተና ይቀርባሉ ?
- ለምን ምቹ ሁኔታ ከሌለ ቀደም ብሎ ሌላ ግቢ አይመደቡም ነበር ?
-  አሁን መፍትሄ ምንድነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች በተደጋጋሚ በድምጽ እና በፅሁፍ ለማናገር ጥረት ቢያደርግም #ቁርጥ ያለ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

በቀጣይም ጥረቱን ይቀጥላል።

ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ካገኘ ያቀርባል።

Via @tikvahUniversity

@tikvahethiopia