TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Nekemte

በነቀምቴ ከተማ ባለፈው አንድ ዓመት ገደማ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት የንግድና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና በማሳደሩ አንዳንድ ባለሃብቶች ወደ ሌላ ቦታ እየሄዱ እንደሚገኙ ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ገልፀዋል።

የኢንተርኔት አገልግሎትም በከተማው መቋረጡና በአብዛኛው የወለጋ ዞኖች የስልክ አገልግሎት አለመኖርም ሥራቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን እንዳንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የነቀምቴ ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስጌን ከተማዋ በአሁኑ ሰዓት ተረጋግታለች፣ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዋም እንዲቀላጠፍ ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።

#የአሜሪካድምፅሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEKEMTE

የስም ዝርዝራቸው በምስሉ ላይ የተገለፀ ግለሰቦች በነቀምት ከተማ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አንድ ላይ በመሆን 416,000 ብር በማዋጣት 200 ኩንታል የስንዴ ዱቄት ገዝተው አበርክተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Nekemte

" ግድያው የተፈፀመው የቤታቸው ደጃፍ ላይ ነው "

ዛሬ የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት የ33 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ በታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

ግድያውን በተመለከተ የከተማ አስተዳዳሩ ምን አለ ?

- ለሥራ ከቤታቸው ሲወጡ በቤታቸው ደጃፍ ነው ባልታወቁ ሰዎች ነው የተገደሉት ብሏል።

- አቶ ደሳለኝ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር በቁርጠኝነት እና በተቆርቋሪነት. . . ያለምንም ፍርሐት ሕዝቡን ሲያገለግሉ ነበሩ ሲልም ገልጿል።

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ምን አሉ ?

- ግድያው የተፈፀመው በታጠቀ አካል ነው ብለዋል።

- ምንም እንኳን ግድያውን የፈፀሙ አካላትን ማንነት በስም ባይገልፁም ግድያውን የተፈፀሙት ከአገሪቱ የለውጥ መንገድ በተጻራሪ የቆሙ አካላት ናቸው ብለዋል።

@tikvahethiopia