TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለመሀላ ፈጸሙ። ፕሬዚዳንቱ ወደ ቢሮ እንደገቡ 200 ገደማ ትዕዛዞች ላይ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተናግረዋል። ፕሬዜዳንቱ ፊርማቸውን ከሚያኖሩባቸው ትዕዛዞች መካከል ፦ - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከአሜሪካ ማባረር ፤ - ጾታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ ማድረግ ፤ - ብዝሀነት፣ እኩልነትና…
" ሁለት ፆታዎች ብቻ ነው ያሉት እነሱም #ወንድ እና #ሴት ናቸው " - ፕሬዝዳንት ትራምፕ
47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ እንደገቡ ከሚሰሯቸው ዋነኛ ስራዎች አንዱ በሀገሪቱ ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እውቅና መስጠት ነው።
ይህም በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣን የመልቀቂያ ጊዜ ለትራንስጀንደር / ፆታቸውን ለሚቀይሩ ሰዎች የሚሰጠውን ከለላና ጥበቃ የሚሽር ነው።
ለወንድ እና ለሴት ብቻ እውቅና መስጠት ትራፕም ከሚያስተላልፏቸው ትዕዛዛት አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ታውቋል።
ትራምፕ ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ ፥ " ከዛሬ ጀምሮ / ከእንግዲህ ወዲህ / የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ እውቅና የሚሰጠው ለሁለት ፆታ ብቻ ነው እነሱም ወንድ እና ሴት " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።
የአሜሪካ መንግሥት ከአሁን በኃላ እውቅና የሚሰጠው ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እንዳሆነ የገለጹት ትራፕም ፤ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ብዝሀነት፣ እኩልነትና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ለማስወገድ የአፈጻሚ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ ተነግሯል።
ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፤ ፆታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ትዕዛዝም ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ትራምፕ " ሰዎች ተፈጥሯዊ ፃታቸውን መቀየር የለባቸውም " ብለው የሚያምኑ ሲሆን ከዚህ ቀደም ፆታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ መነገሩ ይታወሳል።
15 ሺህ ፆታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉ መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቪድዮው የፎክስ ኒውስ መሆኑን ይገልጻል።
#USA #PresidentDonaldTrump
@tikvahethiopia