TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን በዕጩነት የመመዝገብ ሂደት መጀመሩን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ የፓርቲው አመራሮች ለሚወዳደሩባቸው ቦታዎች፤ ቀደም ሲል አሳትሟቸው የነበራቸውን ወደ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እንዲቃጠሉ ትዕዛዝ ማስተላለፉንም ገልጿል።

ቦርዱ ይህን የገለጸው ዛሬ ላስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት፤ አንደኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ነው።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለችሎቱ እንደተናገሩት፤ የባልደራስ ፓርቲ ቀደም ሲል አስመዝግቧቸው በነበሩ ዕጩዎች ምትክ፤ ለምርጫ እንዲቀርቡለት የሚፈልጋቸውን ግለሰቦች እንዲያሳውቅ፤ በመስሪያ ቤታቸው በኩል ጥያቄ ቀርቦለታል። በዚህም መሰረት ፓርቲው በትላንትናው ዕለት አዲሶቹን ዕጩዎች ማሳወቁን አስረድተዋል።

የቦርዱን ሰብሳቢ ገለጻ የባልደራስ ፓርቲ ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለፍርድ ቤቱ አረጋግጠዋል።

ምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ ለመፈጸም እንዲያስችለው ባልደራስ በተተኪነት የሚያቀርባቸውን ዕጩዎች ፎቶግራፎች እንዲያቀርቡ መጠየቁን ጠበቃው ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

በጥያቄው መሰረት የዕጩዎችን “ፎቶግራፎች ለቦርዱ ሰጥተናል” ያሉት አቶ ሄኖክ፤ ሆኖም “ማረጋገጥ የምንችለው የዕጩዎችን ሰርተፊኬት ስንቀበል ነው” ብለዋል።

“የዕጩዎች ሰርተፊኬት የመስጠት ሂደት ቦርዱ በ30 ደቂቃ ማከናወን የሚችለው ነገር ነው። ነገር ግን ቦርዱ ይህን ማድረግ አልቻለም” ሲሉ የባልደራስ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

የዕጩዎች ሰርተፊኬት የመስጠት ሂደት በምን ያህል ጊዜ ሊያልቅ እንደሚችል በፍርድ ቤቱ የተጠየቁት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ፤ “ነገ ጠዋት ያልቃል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል።

የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል።

የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች፤ በ" ክላስተር" የሚደራጀውን አዲስ ክልል የመቀላቀል ውሳኔን ያጸደቁት በሙሉ ድምጽ መሆኑን ተነግሯራ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚል ስያሜ ያለው አዲስ ዞን ለመመስረት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብም በተመሳሳይ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን ተነግሯል።

የ4ቱ ወረዳዎች ም/ቤቶች ዛሬ የወሰኗቸውን ውሳኔዎች ለፌደሬሽን ም/ቤት ያስገባሉ ተብሏል።

የፌዴሬሽን ም/ቤት ወረዳዎች እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች የማሳለፍ ስልጣን አላቸው ወይ ? በሚል ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።

የም/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ " ምክር ቤቶቹ ስለ ህዝብ ጥያቄ የመወያየት፤ ተወያይተውም ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን አላቸው፤ ሆኖም ጥያቄው የሚቀርበው #በዞን እና #በክልል ምክር ቤቶች አልፎ ነው " ሲሉ ማስረዳታቸውን #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር ዘግቧል።

ከቀናት በፊት የጉራጌ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ዞኑን ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳ ጋር አንድ ላይ በክልል እንዲደራጅ በመንግስት የቀረበውን ምክረ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎ ነበር።

በምክር ቤቱ ከተገኙ 92 አባላት ውስጥ 40ዎቹ የ " ክላስተር " አደረጃጀት ምክረ ሃሳብ የደገፉ ቢሆንም 52 አባላት ክላስተርን በመቃወማቸው ነው ምክረ ሀሳቡ ውድቅ የተደረገው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ተጀምሯል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ፤ የሰላም ንግግሩ እስከ እሁድ ጥቅምት 20 እንደሚዘልቅ አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና ህወሓት መካከል የሚካሔደውን የሰላም ንግግር እንድታስተናግድ በመመረጧ ክብር ተሰምቷቸዋል ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን እንድታስተናግድ ስትጋበዝ " ያለ ማቅማማት ተስማምተዋል " ያሉት ቃል አቀባዩ ፤ እንዲህ አይነት ንግግር አፍሪካ " ደህንነቷ የተረጋገጠ እና ግጭት የሌለበት አህጉር " እንድትሆን ከሚሻው የአገራቸው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዓላማ ጋር የተስማማ እንደሆነ ገልጸዋል።

አውዳሚው የትግራይ ግጭት ሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሔ ለማፈላለግ የተጀመረው የሰላም ንግግር በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አመቻችነት የሚካሄድ ነው።

በሰላም ንግግሩ ላይ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፑምዚ ለምላምቦ በደጋፊነት ይካፈላሉ።

" ደቡብ አፍሪካ ለአመቻቺው ቡድን መልካሙን ትመኛለች " ያሉት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቃባይ፤ የሰላም ንግግሩ " የእህት አገር ኢትዮጵያ ህዝቦችን ሁሉ ወደ ዘላቂ ሰላም የሚመራ ስኬታማ ውጤት " ያመጣል የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ታሕሳስ 19 ጀምሮ ወደ መቐለ መደበኛ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ማሳወቁ ይታወቃል። አየር መንገዱ ፤ ወደ መቐለ ከተማ መደበኛ በረራ መጀመሩን ተከትሎ በደንበኞች አገልግሎት ጥሪ ማዕከሉ እና ትኬት ሽያጭ ቢሮዎቹ ላይ ከፍተኛ መጨናነቅ መስተዋሉን ገልጿል። ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ሆነው የአየር መንገዱን ድረ ገፅ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪ ተጠቅመው ምዝገባ…
#Tigray

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ የተናገሩት ፦

- ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ የሚያስጀምሩት በዋና መ/ቤት የሚገኙ ሰራተኞች በጊዜያዊነት በከተማዋ በማሰማራት ነው። በአሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት የሚሰሩ ሰራተኞችን የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው። ለጊዜው ከዚህ ሰዎች እየሄዱ ይሰራሉ፤ ይመለሳሉ። እዚያም ጥቂት ሰዎች አግኝተናል። ጥቂቶቹ ሰዎች እዚያ ያሉትም አብረው ይሰራሉ።

- አየር መንገዱ የመቐለ በረራን በቀን አንድ ጊዜ በማድረግ የሚያስጀምረው፤ ወደ ከተማዋ ለመጓዝ ፍላጎት ያለው መንገደኛ ቁጥር ባለመታወቁ ነው።

-  በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሽረ ከተማ የመንገደኞች በረራ ይጀምራል። ወደ ሽረ ከተማ የባለሞያዎች ቡድን በመላክ፤ በዚያ ያለውን አውሮፕላን ማረፊያ ያለበትን ሁኔታ ተገምግሟል።

- አክሱምን በተመለከተ አውሮፕላን ማረፊያውን አላየነውም። በወሬ የምንሰማው አውሮፕላን መንደንደሪያው ጉዳት አለው ስለተባለ፤ በደንብ አይተን በደንብ ተጠግኖ ነው በረራ የምንጀምረው። በየደረሰውን የጉዳት መጠን የሚያጠና ቡድን ወደ አክሱም ከተማ የሚላክበት ጊዜ ገና አልተወሰነም።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#MoE

ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ " የደከሙባቸው ትምህርቶችን " ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ከእስር ተፈተው ወደ ቤታቸው ገብተዋል " - ጠበቃ ሃፍቶም ከሰተ

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ከእስር ተፈቱ።

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21/2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት ጠበቃ ሃፍቶም ከሰተ ተናግረዋል።

ጠበቃው ይህን የተናገሩት ለ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ ነው።

በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ ፦ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አሳውቀዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahethiopia