TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰከላ

" ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ 47 ሰዎች ናቸው የተገደሉት " - ነዋሪዎች

" በተጨባጭ የሞተ አንድም ሲቪል የለም። ይህ ነው ትክክለኛው እውነት " - የኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሰቢ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ላይ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ/ም በ " ፋኖ " እና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ፣ ከዚያ በኋላ ባሉት ቀናት " በጸጥታ ኃይሎች " ንጹሐን መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቃላቸውም የሰጡ ነዋሪዎች ምን አሉ ?

° #ሰርገኞች ሳይቀሩ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተገድለዋል። ሰርግ ላይ የነበሩ የሙሽራው ወንድም፣ አጃቢዎች ሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ/ም መንገድ ላይ ተረሽነዋል።

° ሴቶች ተገድለዋል።

° 3 ካህናት ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ተገድለዋል።

° ባለፈው ሳምንት ብቻ 47 ሰዎች ናቸው የተገደሉት።

° እውነት የተናገሩ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል።

° ግንቦት 15/2016 ዓ/ም ከሰከላ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ 6 ሰዓት የተጀመረ ተኩስ እስከ ምሽቱ 12 ቆይቷል።

° ተራው ህዝብ ወደ ገጠራማው አካባቢ፣ ባለሃብቶች ወደ ባሕር ዳር ከተማ ለመፈናቀል  ተገደዋል።

አንድ አሽከርካሪ አባትም ልጃቸው ሱቅ ብሎ እንደወጣ እንደተገደለባቸው በሀዘን ስሜት ሆነው ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ተኩስ ያለው ሰሞኑን ብቻ ነው ከዚህ በፊትም ነበር ?  ተብሎ ጥያቄ የቀረበላቸው ነዋሪዎች ፣  የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ/ም ነበር። ከየካቲት 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሰከላ ብቻ 107 ሰዎች ተገድለዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ሰላም እንዲያሰፍንላቸው የጠየቁ ሲሆን  " ሰላም ይውረድልን ግጭት በመጣ ቁጥር እየሞተ ያለው ንጹሃን እንጂ የታጠቀ ኃይል አይደለም " ብለዋል።

የምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ እና የዞን ዋና አስተዳዳሪ እድሜአለም አንተነህ ከሰሞኑን ለ ' አሻም ቴሌቪዥን ' በሰጡት ቃል ፥ " አንድም ንጹሃን አልተገደለም " ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ምን አሉ ?

- ከሳምንት በፊት ሰከላ ላይ ሌሎች ቦታዎች አልፎ አልፎ እንደሚደረገው ግጭት ነበር። ግጭት የነበረው ከከተማው 18 ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ነበር። ግጭቱ የነበረው በታጠቁ ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ነው። ሁለቱም መሳሪያ የያዙ ናቸው።

- እዛ የነበረውን ክፍተት መነሻ አድርጎ ሌላው የታጠቀ ኃይል እኛ ' ፅንፈኛው ኃይል ' የምንለው  ሾልኮ ገብቶ ባንኮችን እና የግለሰብ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ ነው የፈጸመው። በቦታው ላይ በሁኔታው ላይ የተሳተፈ በተጨባጭ የሞተ አንድም ሲቪል የለም።

- በተጨባጭ የሞተ አንድም ሲቪል የለም። ይህ ነው ትክክለኛው እውነት።

- ሲቪሊያን ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ግጭት መተንኮስ አግባብ አይደለም። የተፈናቀለ ሰው የለም፣ የወጣ ሲቪልም የለም። በግጭቱ የተሳተፈ ሲቪል የለም። ከተማው ላይ ያችግር ሲፈጠር ሰዎች ቤታቸው ውስጥ ነበሩ።

- አሁን የገጠሩ ህዝብ ዘር እየዘራ ነው። የአካባቢው ኑሮም መደበኛው ነው። የተፈናቀለም የለም፤ እንደዛ የሚባል ስጋት የለም።

በሰከላ ተፈጸሟል የተባለውን ግድያ ሰምቶ እንደሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፣ ሰሞኑን በአማራ ክልል ስላለው ጥቃት ሪፓርት ይፋ እንደሚያደርግ፣ የሰከላውም በዚሁ ሪፖርት ውስጥ ተካቶ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia