TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት #የዕግድ ትዕዛዝ መስጠቱ ተገለፀ። ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ አውግዛ በለየቻቸው ተጠሪዎች ላይ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዚህ ጉዳይ…
የእነ አባ ሳዊሮስ እግድ ተነሳ።

የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ እግድ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በቅርቡ የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ ፦

- የአባ ሳዊሮስ፣
- የአባ ኤዎስጣቴዎስ
- የአባ ዜና ማርቆስ #ዕግድ_መነሳቱን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቀሪዎቹ 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ተገልጿል።

#ተሚማ

@tikvahethiopia