TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሊያ ሶማሊያ ቲክቶክ እና ቴሌግራም እንዲሁም 1ኤክስቤት (1XBet) የተባለውን የስፖርት ውርርድ ገጽን እንዲዘጉ አዘዘች። " ቲክቶክ " እና " ቴሌግራም " የአሸባሪዎች መረጃ ማስተላለፊያ ሆነዋል ብሏል የሶማሊያ መንግሥት። መተግበሪያዎቹ " አሸባሪ ድርጅቶች እና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውለዋል " ሲል ገልጿል።…
ኔፓል ሀገሪቱ ላይ " ቲክቶክ " እንዲታገድ ወሰነች።

ኔፓል ፤ ማህበራዊ መስተጋብርን የሚረብሹና የቤተሰብን መዋቅር እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያውኩ ይዘቶችን ለማጋራት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ያለችውን የቻይናውን " #ቲክቶክ " መተግበሪያ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈች።

ሀገሪቱ ፤ " ቲክቶክ " በማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ያለች ሲሆን በመተግበሪያው ላይ የሚለቀቁት ተንቀሳቃሽ ምስሎችና የሚተላለፉት መልዕክቶች ለሀገሪቱ ህዝብ ባሕል እንግዳ የሆኑና ቀድሞ በማህበረሰቡ ዘንድ የነበረውን ማህበራዊ መስተጋብር የሚሸረሸሩ ናቸው ስትል አሳውቃለች።

የመገናኛ ና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሬካ ሻርማ ፤ የቲክቶክ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ የሀገሪቱ ካቢኔ ተሰብስቦ መመክሩንና #ለማገድ ውሳኔ እንዳሳለፈ ይፋ አድርገል።

የቴሌኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ኃላፊ የሆኑት ፑሩሾታም ካናል በሰጡት ቃል ፤ በኔፓል የሚገኙ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች " ቲክቶክ " ን እንዲዘጉ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

አንዳንዶች መዝጋታቸውን ሌሎችም በቀጣይ እንደሚያደርጉት ጠቁመዋል።

" ቲክቶክ " የማህበራዊ ህይወት ላይ እያሳደረ ነው ከተባለው አሉታዊ ተፅእኖ በተጨማሪ በርካታ ከመተግበሪያው ጋር የተያያዙ የሳይበር ደኅንነት ወንጀሎች መመዝገባቸው ተመላክቷል።

የኔፓል መንግስት ተቃዋሚዎች ውሳኔው " ውጤታማነት ፣ ብስለት እና ኃላፊነት " የጎደለው ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

አንድ የእገዳው ተቃዋሚ ፤ በሌሎችም ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ብዙ የማያስፈልጉ ነገሮች እንዳሉ አንስተው መደረግ ያለበት እነሱን መቆጣጠር ነው እንጂ መገደብ አይደለም ብለዋል።

ወደ አንድ ቢሊዮን የሚጠጉ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች አሉት የሚባለው ታዋቂው የቪዲዮ ማጋሪያ መድረክ " ቲክቶክ " መረጃን በመበርበር እና በወጣቶች ላይ ጎጂ ተፅእኖ እያመጣነው በሚል ከዚህ ቀደም በአንዳንድ ሀገራት እገዳ ገጥሞታል።

አንዳንድ ሀገራት መተግበሪያው የቻይና መንግሥት መረጃ ለመበርበር ይጠቀምበታል በሚል ይተቹታል።

የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " በቤጂንግ ቀጥተኛ ቁጥጥር ስር ነው እየተባለ የሚቀርቡበትን ክስና ትችቶችን በተደጋጋሚ #እንደማይቀበል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#TikTok #USAHouse

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል/ፓኬጅ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።

" ቲክቶክ " በአሜሪካ እንዲታገድም ድምጽ ሰጥቷል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ድምፅ የሰጠው በ " #ቲክቶክ " ጉዳይ ሲሆን ባለቤትነቱ የባይትዳንስ የሆነው መተግበሪያ ለአሜሪካ ኩባንያ ካልተሸጠና ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቋረጠ በመላው አሜሪካ ውጤታማ በሆነ መንገድ #ለማገድ 360 ለ 58 በሆነ ድምጽ ረቂቅ ሕግ #አጽድቋል

" ቲክቶክ " በአሜሪካ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።

በመቀጠል ምክር ቤቱ ፦

➡️ ለዩክሬን 60.8 ቢሊዮን ዶላር (3,422,796,000,000 ብር)፤

➡️ ለእስራኤል 26.4 ቢሊዮን ዶላር  (1,483,211,600,000 ብር)፤

➡️ ለታይዋን እና ለኢንዶ ፓስፊክ ሀገራት  ' ቻይናን ለሚጋፈጡ ' የ8 ቢሊዮን ዶላር (456,372,800,000 ብር) የእርዳታ ድጋፍ በድምሩ የ95 ቢሊዮን ዶላር ጥቅል እርዳታ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።

የምክር ቤቱ አባላት የዩክሬን ድጋፍ ሲጸድቅ ፤ " ዩክሬን !! " እያሉ በመጮህ የሀገሪቱን ባንዲራ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።

@thiqahEth @tikvahethiopia