TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ #አካልጉዳተኞች

“ አጠቃላይ የሆነ የአካል ጉዳተኞች የህግ ማዕቀፍ እንፈልጋለን ” - የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር  “ ስለረቂቅ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ አያያዝ በኢትዮጵያ የመወያያ መነሻ ሀሳብ ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከፍትህ ሚኒስቴር የሕግ ማርቀቅ ባለሙያዎቸ ጋር ከሰሞኑን የምክክር አውደ ጥናት አድርጓል።

የምክክር አውደ ጥናቱ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ20 ሚሊዮን በላይ አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ ያልሆኑባተቸውን፦
- የኢኮኖሚ፣
- የትምህርት፣ 
- የቅጥር፣ 
- የማኅበራዊ ተሳትፎዎችና የመብት ጥሰቶች ችግሮችን እንዲቀረፍ “ ሁለንተናዊ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ ” ለማውጣት ማኀበሩ ከአጋር አካላት ጋር በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ማድረግ ነበር።

በመርሀ ግብሩ የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ያሉት አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ ህጎችስ በትክክል እየተፈጸሙ ነው ወይ ? ይህ ረቂቅ አዋጅስ በዘርፉ  ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ምን ጉልህ ሚና አለው ? ሲል ማኀበሩን ጠይቋል።

የማኀበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ጥላሁን በሰጡት ቃል፣ “ አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ የተወሰኑ (ጥቅል/ግልፅ ያልሆኑ) ህጎች አሉ። በአጠቃላይ አካል ጉዳተኞችን በማስመልከት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ህጎች በርካታ ችግሮች አሉባቸው ” ብለዋል።

የተወሰኑ ህጎች ቢኖሩም፦
- ጥቅል/ግልጽ ያልሆኑ፣
- አስፈጻሚ አካል የሌላቸው፣
- ተጠያቂነትን የማያሰፍኑ፣ 
- ዝርዝር መመሪያ የሌላቸው በመሆናቸው የነበሩት ህጎች አስቻይ ሁኔታ እንዳይፈጥሩ አድርጓቸዋል ” ነው ያሉት።

“ ወቅቱን የዋጀ የወቅቱን የአካል ጉዳተኞች ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እንቅስቃሴን መሠረት ያደረገ አዋጅ የለም ” ያሉት አቶ ሙሴ፣ በሂደት ላይ ያለው “ ሁለንተናዊ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ ” ሲወጣ ችግሩን ሊቀርፍ እንደሚይችል አስረድተዋል።

ረቂቅ አዋጁ፦
- የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ግልጽ የሆነ በጀት እንዲኖር፣
- የአካል ጉዳተኛ ቤተሰቦች የሚደርስባቸውን መገለልና አድሎ ችግር የሚቀርፍ፣ 
- አካል ጉዳተኞች በህንፃ፣ ትምህርት፣ በትራንስፖርት ተደራሽነታቸው እንዲረጋገጥ የሚያደርግ፣ 
- ከውጩ ሀገራት የሚገቡ አካል ጉዳተኞች የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ጭምር የሚደነግግ መሆኑን ተናግረዋል።

#TiavahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia