TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደቡብ_አፍሪካ

የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል።

የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ባሳየው ቸልተኝነት ምክንያት መሆኑ ታውቋል።
የዛምቢያ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳይጓዙም አስጠንቅቋል።

በተመሳሳይ ዜና...

ታዋቂው የናይጄሪያ ድምፃዊ ቡራን ቦይ በዘርኝነት ጥቃቱ ምክንያት በጭራሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዝ እንደማይፈልግ ተናግሯል።
ናይጄሪያም በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቅቃለች።

አቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች።
የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷልም ተብሏል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት በበኩላቸው በደቡብ አፍሪካ ባሉ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎችን ኢላማ አድርጎ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት አውግዘዋል።

ሊቀ መንበሩ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት በንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ንብረት መዝረፍ እና ማውደምን ጨምሮ ሌሎች እየፈፀሙ ያሉ ድርጊቶችን ክፉኛ ኮንነዋል። የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመራቸውንም ሊቀ መንበሩ የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል።

Via #EBC
@tikvahethiopia
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እስካሁን ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል። #ደቡብ_አፍሪካ #SouthAfrica
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ደቡብ_አፍሪካ

ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ ከወትሮ ለየት ከባድ ዝናብ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እየጣለ ይገኛል:: ሰሞኑን የጣለው ይህ ከባድ ዝናብ በኳዙሉናታል፣ ፑማላንጋ እና ሊምፖፖ እንዲሁም ሌሎች የደቡብ አፍሪካ ግዛቶች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

ይህን ተከትሎ ጆሃንስበርግ ከተማ እየጣለ ባለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት የ " አስቸኳይ ግዜ ምላሽ " ለመስጠት በተጠንቀቅ ላይ ነች ሲል የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግቧል። ዝናቡ ቀጣይነት ሊኖረው ስለሚችል የደቡብ አፍሪካ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

በደቡብ አፍሪካ የምትኖሩት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻችንም ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ እናሳስባለን።

Video:- eNCA

Fa ya
(Tikvah-Family)
South Africa

@tikvahethiopia
#ደቡብ_አፍሪካ | " በ3 ወራት በትንሹ 6,000 ሰዎች ተገድለዋል "

ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ድርጊቶች ይፈፀምባቸዋል ተብለው ከሚጠሩ ሀገራት አንዷ ደቡብ አፍሪካ ናት።

ከፖሊስ በወጣ ሪፖርት መሰረት በሀገሪቱ በሶስት ወራት በትንሹ 6,000 ሰዎች ተገድለዋል።

በጥር እና መጋቢት መካከል 6,083 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር (4,976 ነበር) የ22.2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ከግድያ በተጨማሪ የፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተፈፀሙ ወንጀሎች በ13.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን 10,818 ሰዎች ተደፍረዋል።

እገታ እና አፈናም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን 3,306 ኬዞች ሪፖርት ተደርጓል ፤ ይህም ከአንድ አመት በፊት ከነበረው በእጥፍ ይበልጣል ተብሏል።

የሀገሪቱ ፖሊስ " የዚህ አመት የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ጨካኔ የተሞላበት እና ለብዙ ደቡብ አፍሪካውያን ደህንነታቸው ያልተጠበቀ ነበር " ብሏል።

" ብቻዬን ከሚሰሩ ወንጀሎች ጋር ተፋልሜ ላሸንፍ አልችልም " ያለው የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ " ከማህበረሰቡ ጋር በጠንካራ እምነት ላይ የተገነባ ጥልቅ አጋርነት ያስፈልገኛል " ሲል ገልጿል።

#TikvahFamilySouthAfrica

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አምባሳደር ማይክ ሐመር ኬንያ ይገኛሉ። የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ተነጋግረዋል። ፕሬዜዳንት ሩቶ ከአሜሪካው አምባሳደር ሐመር ጋር ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ " ሰላምና መረጋጋት ለአገሮች ልማትና ብልፅግና የግድ አስፈላጊ ነው " ያሉ ሲሆን ኬንያ ፤ አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም…
#Update

አምባሳደር ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው አምባሳደር ማይክ ሐመር በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር #ዛሬ ውይይት አካሂደዋል።

አቶ ደመቀ መኮን በውይይቱ ወቅት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆኑን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር በበኩላቸው፤ አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " በውይይቱ ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ተስማምተዋል " ሲል አሳውቋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ከቀናት በፊት #ኬንያ እንደነበሩና ከኬንያው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

አሜሪካ አምባሳደር ሐመርን ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም እና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ ወደ ኬንያ ፣ #ደቡብ_አፍሪካ ፣ ኢትዮጵያ እንደላከች ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።

Photo Credit : Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

@tikvahethiopia
#ደቡብ_አፍሪካ

• " የመንግሥት ለውጥ በምርጫ እንጂ በግርግር  አይመጣም " - ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ

• " መንግሥት እየተንቀጠቀጠ ነው ፤ ፈርቷል " - የራማፎሳ ተቃዋሚ ጁሊየስ ማሌማ (የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ)

• በተቃውሞው ሳቢያ የንግድ መደብሮች ገና ካሁኑ ሥጋት አድሮባቸዋል።

#በመጪው_ሳምንት በደቡብ አፍሪካ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ታቅዷል።

በዚህም ሳቢያ የአገሪቱ መንግሥት ቁልፍ የሚባሉ መሠረተ-ልማቶችን ለመጠበቅ እና የጸጥታ ጥበቃውን ለማጠናከር የሀገሪቱን ጦር (ወታደሮች) እንዳሰማራ ዶቼ ቨለ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ጁሊየስ ማሌማ የሚመሩት ግራ ዘመም የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ በመጪው ሰኞ በመላ ደቡብ አፍሪካ የሥራ ማቆም አድማ መጥራቱ ተነግሯል።

ፓርቲው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፖሳ የደቡብ አፍሪቃን ኤኮኖሚ በመሩበት ስልት፣ በመብራት እጥረት እና እየበረታ በሚሔደው የሥራ አጥነት ሳቢያ ከሥልጣን መልቀቅ አለባቸው የሚል አቋም አለው።

የደ/አፍሪቃ ጦር ለአገሪቱ ፖሊስ እገዛ እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውቋል።

ጦሩ በእጁ በሚገኙ የስለላ መረጃዎች መሠረት ሥጋት አለባቸው የተባሉ ቁልፍ ቦታዎችን ለመጠበቅ ከትላንት አርብ ጀምሮ ለአንድ ወር ወታደሮች አሰማርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ከጸጥታ አስከባሪ ተቋማት አቅም በላይ ለሚፈጠሩ ኩነቶች ወታደሮች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል።

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አንድ ዓመት የቀረው ሲሆን ፕሬዜዳንት ራማፎሳ የታቀደው ሰልፍ " ፖለቲካዊ ሴራ ነው "  የሚል አቋም አላቸው።

ፕሬዜዳንቱ ባለፈው ሐሙስ " ሥርዓተ-አልበኝነት እና ግርግር እንደማይፈቀድ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ራማፎሳ የመንግሥት ለውጥ " በምርጫ እንጂ በግርግር " እንደማይመጣም ገልጸዋል።

የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ትላንት በስዌቶ ለደጋፊዎቻቸው " ማንም አብዮትን ሊያስቆም አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" መንግሥት እየተንቀጠቀጠ ነው፤ ፈርቷል " ያሉት ማሌማ ራማፎሳ ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል።

በተቃውሞው ሳቢያ የንግድ መደብሮች ገና ካሁኑ ሥጋት እንደገባቸው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
ስለብፁዕነታቸው የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳወቀች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ #ደቡብ_አፍሪካ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞ መሰረዛቸውን ተከትሎ #የሐሰት_ዜና በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦
- በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣
- ቅዳሴ ቤቱን ለማክበር
- በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለመባረክ
-  ምዕመናንን ለማስተማር ዛሬ ከቅዱስነታቸው ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ መርሐ ግብር ይዘው ነበር።

ይሁን እንጂ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ካለባቸው ተደራራቢና አስቸኳይ ሥራዎች አንጻር ለ10 ቀናት ሙሉ ፦
° ከጽ/ቤታቸው ርቀው መቆየት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎች ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር በመስጋታቸው
° ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊውና ምክትል ሥራ አስኪያጁ በሌሉበት ሁኔታ ለበርካታ ቀናት ከጠ/ጽሕፈቱ ርቀው ከተጓዙ ሥራዎች ስለሚበደሉ ቀደም ሲል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ሐዋርያዊ ጉዞ ከቅዱስነታቸው ጋር በጥሞና በመወያየት #ለመሰረዝ መገደዳቸው ተነግሯል።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ማኅበራዊ ገጾች ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ " ብፁዕነታቸው ወደ ኤርፖርት እንዳይሔዱ እንደተከለከሉ እንዲሁም ፓስፖርታቸው እንደተያዘ " በማስመሰል የሚሰራጨው ዜና ፍፁም መሰረተ ቢስና የሐሰት ዜና መሆኑን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከታቀደው ሐዋርያዊ ጉዞ ለመቅረት የተገደዱት በተደራራቢ ሥራ ምክንያት  መሆኑን እና የብፁዕነታቸው ፓስፖርትም ለጉዞ ሲባል ቀደም ብሎ ከሚመለከተው አካል መጥቶ በልዩ ጽሕፈት ቤቱ ጉዳይ አስፈጻሚ እጅ የሚገኝ መሆኑን ገልጻለች።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከብፁዓን አባቶች ጋር ሆነው በዛሬው ዕለት ደቡብ አፍሪካ ፤ ጁሐንስበርግ ከተማ በሰላም የገቡ ሲሆን ምዕመናንም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ደቡብ አፍሪካhttps://telegra.ph/EOTC-05-10

@tikvahethiopia