አሳዛኝ ዜና‼️
በድሬዳዋ ከተማ የትራፊክ ህግ በማስከበር ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ በባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ተገጭቶ ህይወቱ አልፏል፡፡
ረዳት ኢኒስፔክተር #ዮናታን_ባልቻ የተሰኘው የትራፊክ ፖሊስ በድሬዳዋ ከተማ ከሳቢያን መልካ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚወስደው በግንባታ ላይ በሚገኘው አዲስ መንገድ የቁጥጥር ስራ እያከናወነ ባለበት ወቅት ነው አደጋው የደረሰበት።
የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዋና ሳጅን #ባንተ_አምላክ ግርማ እንደተናገሩት ሟቹ ስራውን እያከናወነ ባለበት ሰዓት ሲኖትራክ መኪና ባለ 3 እግር መኪናውን ሲገጨው ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱ የትራፊክ ፖሊሱ ላይ ጉዳት አድርሷል። በትራፊክ አደጋው በስራ ላይ የነበረ ሌላ የትራፊክ ፖሊስ ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia