TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ~ትግራይ🔝

"የጉዞ አድዋ" የእግር ተጓዦች #በትግራይ! #ጉዞ_ዓድዋ_6! ሰላም፤ ፍቅር፤ አንድነት! #ኢትዮጵያ #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 11...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የተገኙበት የህወሃት 44ኛ ዐመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ #ኢንተር_ኮንትኔንታል ሆቴል እየተከበረ ይገኛል። #በድምፂ_ወያነ እና #በትግራይ_ቲቪ በቀጥታ እየተላለፈ ስለመሚገኘ መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ዲያስፖራዎች ዛሬ ችግኝ ተከሉ!

#በትግራይ ህዝቡ ለተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ እየሰጠ ያለውን ትኩረት አዲስ የሚተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ሊያጠናክር እንደሚገባ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ተናገሩ። ዳያስፖራዎቹ ዛሬ ጠዋት መቐለ በሚገኘው የትግራይ ሰማዕታት ኃውልት ግቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል።

ከአሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ የመጡት ዲያስፖራ አቶ ዮሐንስ ተክለብርሃን እንደገለጹት፣ በክልሉ ከሚያስደስቷቸው መልካም ሥራዎች መካከል አንዱ የትግራይ ክልል ህዝብ ለተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ የሰጠው ትኩረት ነው። “ችግኝ እንደ ህጻን ልጅ በመሆኑ አዲስ በተለይ ለሚተከል ችግኝ ተገቢ እንክብካቤ በማድረግ ለታለመለት ውጤት ማድረስ ያስፈልጋል” ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦ - ትግራይ ነባር እና አዳዲስ ፖሊሶችን እያሰለጠነች ነው። ከፌዴራል ፖሊስ የሄዱ #ተጋሩ የፖሊስ አባላት ተደራጅተው በ6 ዞኖች መደበኛ 15 መሃል ወረዳዎች በመምረጥ ተመድበው የሚሰሩበት ሁኔታም እየተመቻቸ ነው። - ለትግራይ አዳዲስና ነባር ፖሊሶች ወንጀል ለመከላከል የሚሆን አስፈላጊ ትጥቅ መፈቀዱ። - የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል…
#BREAKING

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ #በትግራይ ጉዳይ ያለ ምንም ስምምነት መጠናቀቁን ዲፕሎማቶች መግለፃቸውን AFP ዘግቧል።

ሩስያ ፣ ቻይና እና ህንድ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አስፈላጊ አይደለም የሚል አቋም ይዘዋል ፤ በዚህም የተ.መ.ድ. የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ስምምነት ተጠናቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መረጃ ማጣሪያው የስም ቅያሪ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም #በትግራይ ጉዳይ ላይ መረጃዎችን እያጣራ ሲያቀርብ የነበረው በፌዴራል መንግስት ስር የሚገኘው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ" ስሙን ቀይሯል።

ይህንንም በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ያሳወቀ ሲሆን አዲሱ ስያሜው "የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፅ/Ethiopia Current Issues Fact Check" እንደሆነ ተገልጿል።

ከዚህ በኃላ ገፁ የትግራይን ጨምሮ #በመላው_ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን እንደሚያጣራ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ኢሰመኮ

EHRC / ኢሰመኮ #በትግራይ_ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በሲቪል ሰዎች ላይ እንግልት እና እስር ፣ የንግድ ቤት መዘጋት ፣ ብሎም በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መከሰቱንና ሕይወት መጥፋቱን፣ እንዲሁም በታሳሪዎችና በምርኮኞች ላይ የሚደርስ ኢሰብአዊ አያያዝ፣ በስደተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ሕጻናትን ለውትድርና መጠቀም የሚያመላክቱ መረጃዎች እጅግ የሚያሳስበው መሆኑን ገልጿል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ICRC የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት ህይወታቸውን እንደሚታደግ ገልጾ ፦ በሐይቅ፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ኮምቦልቻ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ዓዲግራት፣ መሆኒ፣ ሽሬ፣ ኣክሱም፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ዋድላ፣ ባህር ዳር፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢዶሎ ሆስፒታሎች ያሉትን የአንድ መስኮት የአገልግሎት ማዕከላትን በመደገፍ…
#ICRC #Tigray

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በተለያዩ ክልሎች በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል።

ኮሚቴው #በትግራይ_ክልል በግጭት የተጎዱ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ ፦

👉 በማዕከላዊ፣
👉 በምስራቅ ፣
👉 በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ዞኖች ለሚገኙ ለ20,000 አባውራዎች (120,000 ግለሰቦች) የአፈር ማዳበሪያ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ዛሬ አሳውቋል።

ICRC ፤ ከሰሞኑን በትግራይ፣ አማራ እንዲሁም ኦሮሚያ ክልል ከተሞች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ እና ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተቀብረው ሳይፈነዱ ሚቀሩ ፈንጂዎች በሰዎች አካል ላይ የሚያደረሱትን ጉዳት ተንተርሶ ተጎጂዎችን ለመርዳት በተለያዩ ከተሞች የአካል ማገገሚያ ማዕከላትን በማጠናከር ላይ እንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

- ከደቡብ አፍሪካ ፣ ፕሪቶሪያ የቀጠለው የናይሮቢው የሰላም ውይይት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም ውይይቱ እስከ ትላንት ሀሙስ ድረስ መቀጠሉን ለጉዳዩ ቅርበትና መረጃው ያላቸው አካላት ተናግረዋል።

እስካሁን ውይይቱ ስልተደረሰበት ደረጃ ምንም ይፋ የሆነ መረጃ የለም።

#በዝግ እየተካሄደ በመሆኑ ሚዲያዎችም ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለመናገር እድል አላገኙም። በውይይቱ ፍፃሜ ላይ ስለተደረሰበት ደረጃ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የፖለቲካ ተደራዳሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እየተካፈሉበት ያለው የናይሮቢው የሰላም ውይይት #አጀንዳዎች ናቸው ከተባሉት መካከል ፦

👉 የሰላም ስምምነቱን ሂደትና አፈፃፀም መከታተል፣
👉 የህወሓት ኃይሎችን ትጥቅ ስለማስፈታት፣
👉 በትግራይ ክልል ለወራት ተቋርጦ የነበረውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ስለማስቀጠል፣
👉 የመሠረታዊ አገልግሎቶች መልሶ ስለማስጀመር ይገኙበታል።

- የሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ላይ በኬንያ ፣ ናይሮቢ እየተመከረ ባለበት በአሁን ወቅት የኤርትራ ኃይሎች #በትግራይ ውስጥ መጠነ ሰፊ ዘረፋ ፣ አፈና ፣ ግድያ ፣ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ሲሉ ከህወሓት አመራሮች መካከል ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት በትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

በሽረ አካባቢ የኤርትራ ኃይሎች ሲቪሎችን / ሴቶችን ጨምሮ በዘረፋ ላይ ተሰማርተው ታይተዋል ያሉ ሲሆን በከተማው ከሰዓት እላፊ በኃላ በጨለማ ሁሉንም ክፉ ነገር እያደረጉ ነው ብለዋል።

ይህንን መልዕክት ካሰራጩ በኃላ በናይሮቢ የሚገኙት የህወሓት ተደራዳሪ እና የሰላም ስምምነቱ ፈራሚ አቶ ጌታቸው ረዳ መልዕክቱን " ክንደያ ትግራይ ናቸው " ሲሉ አጋርተዋል።

አቶ ጌታቸው ይህንን ከማለት በዘለለ ምንም ዝርዝር ነገር አልፃፉም።

- አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ትላንትና ለሊት ባሰራጫችው ፅሁፍ ፤ " አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በናይሮቢ እንደተናገሩት ፤ በፕሪቶሪያ እንደተደረሰው ስምምነት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ የሰብዓዊ እርዳታ ያለምንም እንቅፋት ይገባል ብለዋል " ብላለች።

አሜሪካ ፤ " በትግራይ፣ አፋርና አማራ የሚገኙ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያን አሁኑኑ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል " ስትል ገልፃለች።

#የመሰረታዊ_አገልግሎቶች ወደ ነበረበት መመለስ ፣ የሲቪሎች ጥበቃ እና የሰብአዊ መብቶች ተጠያቂነትን ያነሳችው አሜሪካ ስምምነቱን ለማክበርና ለመተግበር የሚወሰዱ እርምጃዎችን በአስቸኳይ በመጠባበቅ ላይ ነን ብላለች።

- ኬንያ ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የጠ/ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በአሁን ሰዓት ሰባ በመቶ (70%) ትግራይ በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝ ገልፀዋል። እስካሁን በሀገር መከላከያ ባልተያዙ ቦታዎች ሳይቀር እርዳታ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየገባ ነው ብለዋል።

ምግብ  የጫኑ 35  ተሽከርካሪዎችና መድሃኒት የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ሽረ ከተማ መግባታቸውን የገለፁት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ " በረራዎች ተፈቅደዋል፣ አገልግሎቶች እንደገና እየተገናኙ ነው ። " ብለዋል።

የሰላም ስምምነቱ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እድሎችን ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል። እርዳታን በተመለከተ ምንም አይነት እንቅፋት የለም ሲሉ አክለዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ፤ " አንዳንድ ጥግ ላይ ያሉ አካላት የአፍሪካውያን እውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት #ደስተኛ_አይመስሉም ፤ መንፈሱንም ለማበላሸት እየተሯሯጡ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት የርክበ ካህናትጉባኤ ነገ ግንቦት 2 ቀን 2015  ዓ/ም ይከፈታል። በአሁን ሰዓት የግንቦት 2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መክፈቻ የጸሎት ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሔድ ላይ ነው። ፎቶ ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ @tikvahethiopia
#Update

የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተከፍቷል።

ይህን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል።

ምን አሉ ?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባቀረቡት ንግግር ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው ብለዋል።

" በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል " ሲሉ ገልጽዋል።

" የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ " ጌታችን፡- ' እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ ' ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል " ብለዋል።

በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በተለይም #በትግራይ እና #በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል " ብለዋል።

" በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል " ሲሉም አክለዋል።

" እኛ ያጐደልነው ፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያኩ " ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም " ሲሉ አሳውቀዋል።

(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ ስፍራ ምን ተፈጠረ ? በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል የራያ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በትጥቅ የተደገፈ ግጭት እንደነበረ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል። የካቲት 6 / 2016 ዓ.ም የተቀሰቀሰው መጠነኛ ነው የተባለው ግጭት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥረት ሊቆም እንደቻለ ነው የተነገረው። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ…
" ችግሩ በሰላማዊ መንገድ የፌደራል መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲፈታ ፍላጎታችን ነው " - አቶ ኃይሉ አበራ

ከሰሞኑን #በአማራ እና #በትግራይ ክልሎች መካከል ተቀሰቀሰ የተባለውን ለአጭር ጊዜ የቆየ የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ በአማራ ክልል በኩል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ በአሁን ሰዓት በአማራ ክልል ስር እየተዳደረ ያለው የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ኃይሉ አበራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ኃይሉ አበራ ምን አሉ ?

- በባላ አቅጣጫ ማሮ በሚባል ቦታ ከእኛ ሚሊሻ ጋ ገጠሙ። ተመትተው ተመልሰዋል አሁን ላይ ቦታውን ለቀዋል።

- ወደ ሁለት ቀበሌዎች ወረራ ለማድርግ ሙከራ አድርገው ነበር። በመጀመሪያ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ ነበር እየተላለፈ የከረመው፣ አሁን ግን እሳቢያቸው የነበረው በወረራ ቦታውን ይዘው ‘እንደራደራለን’ አይነት፣ በተፈናቃይ ስም ግጭት መፍጠር ነው።

* የጉዳት መጠንን በተመለከተ ፦ " እኛ ጋር የደረሰ ጉዳት የለም። እነሱ ግን ሊያጠቃ የመጣ ምንጊዜም ተመትቶ ነው የሚሄደው። የተወሰኑት ተመተው ሂደዋል። " ብለዋል።

- አላማጣን፣ ኮረምን ለመውረር እንዲሁ በጡሩባ እና በጩኽት የሚለቅ ህዝብ መስሏቸው ነበር። ሕዝቡ ማዕበል ሆኖ ነው የወጣው ከዚህ በኋላ የሰላሙን ጥሪ የማይቀበሉት እና ሰላሙን የማይፈልጉት ከሆነ አሁን እኛ ህዝባዊ አድርገነዋል።

* የመፍትሄ ሀሳብን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ፦ " ችግሩ በሰላማዊ መንገድ የፌደራል መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲፈታ ፍላጎታችን ነው። 'አይ የለም ህዝቡ ወደ ሚፈልገው መሆን አይችልም፣ እኔ ብቻ ነኝ የምወስንልህ' የሚል እሳቤ የሚቀሳቀስ ከሆነ እሱ የሚቻል አይደለም። ፋሽኑም ግዜውም አልፎበታል። አሁን ላይ ወደ ኋላ የሚመልስ ኃይል የለም። Already ሁሉም ተደራጅቷአል። " ብለዋል።

- የትግራይ ፖለቲከኞችም ሀይ ሀይ የሚሉትን ዲያስፖራ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል። ' አይ የለም የትግራይ ሉዐላዊ ግዛት ' እያሉ በወረራ የያዙትን ቦታ 'በኃይል እናስመልሳለን' የሚሉ ከሆነ ግን ከዚህ በኋላ የሚኖረው ሕዝባዊ ነው። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው። በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ነው ሊፈጠር የሚችለው። ይህንን እንዲያስቡበት ነው የምናስገነዝበው።

- እኛ የማንንም መብት አንጋፋም የትኛውንም ሰው በማንነቱ ምክንያት የምናደርስበት ጉዳት የለም። ሊወርና ሊገድል ኃይል ከመጣ ግን ህዝብን መቆጣጠር አይቻልም። ስለዚህ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ከመሆናቸው በፊት ቆም ብለው ቢያስቡ ይሻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ/ም
አላማጣ

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia