TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GONDAR

የአማራ ክልል ሰላም እና ህዝብ ደህንነት ቢሮ በጎንደር ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ 6 የፖለቲካ እና የፀጥታ መዋቅር አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ነው ብሏል።

እነዚህ ስድስት የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር አመራሮች ስማቸው በይፋ ያልተገለፀ ሲሆን በምን አይነት የአመራርነት ቦታ ላይ ያሉ እንደሆኑ አልተብራራም።

ቢሮው ፤ ከህዝቡ ፣ ከፖለቲካ አመራሩ እና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ውይይት እና ግምገማ ከተደረገ በኃላ የማስተካከያ እና የእርምት እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Gondar

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ሊያካሂድ የነበረውን የጠቅላላ ጉባኤ ወደ አዲስ አበባ ቀይሯል።

ይህ የሆነው ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳ ጉባኤውን ስትጠባበቅ ነው።

ፌዴሬሽኑ ቦታ ተመቀየር ለምን ፈለገ ?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፤ የአማራ ክልል መንግስት የስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የጠቅላላ ጉባኤ ሥራ ወደሚያከናውኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ሰራተኞች ስልክ በመደወል ከክልሉ ክለቦች የተላኩ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ወኪሎች ስሞች መቀየር እንዳለባቸው እና ይህንን እንዲያደርጉ ፤ ካላደረጉ ግን ጉባኤው እንዲስተጓጎል እንደሚያደርጉ በማስፈራራት ጭምር ስሜታቸውን መግለፃቸው ማረጋገጡን ገልጿል።

ጠቅላላ ጉባኤው ከጉባኤው አባላት በተጨማሪ የፊፋ እና የካፍ ታዛቢዎች የሚታደሙበት ነው ያለው ፌዴሬሽኑ ነገር ግን የክልሉ ከፍተኛ አመራር ሆነው ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ሥራ መሥራት ሲገባቸው ችግር እንደሚፈጥሩ መግለፃቸው የጉባኤው ውጤታማነት ላይ ስጋት እንዲያድርብን ምክንያት ሆኗል ብሏል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር እያደረገ ያለው ተግባር ፍፁም የሚያስመሰግነው ቢሆንም ፤ የክልሉ አመራር በዚህ ደረጃ ችግር ለመፍጠር እየሞከሩ በመሆኑ እና ሌሎች የእርምት እርምጃዎችን ለመውሰድ ያለው ጊዜ አጭር በመሆኑ የጉባኤውን ቦታ መቀየር ማስፈለጉንዳማስፈለጉን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

በዚህም ጉባኤው አዲስ አበባ ከተማ እንዲሆን መወሰኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ሊያካሂድ የነበረውን የጠቅላላ ጉባኤ ወደ አዲስ አበባ ቀይሯል። ይህ የሆነው ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳ ጉባኤውን ስትጠባበቅ ነው። ፌዴሬሽኑ ቦታ ተመቀየር ለምን ፈለገ ? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፤ የአማራ ክልል መንግስት የስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የጠቅላላ ጉባኤ ሥራ ወደሚያከናውኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ሰራተኞች ስልክ በመደወል…
#Gondar

" ውሳኔያችሁን በድጋሜ አጢኑት " - ጎንደር

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔን #ተገቢነት_የሌለው ነው አለ ፤ ውሳኔውንም ድጋሜ እንዲያጤነው ጠይቋል።

የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ከተማ የፌዱሬሽኑን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ እንደተዘጋጀ ለከተማው አስተዳደር አሳውቆ ነበር።

ነገር ግን ፌዴሬሽኑ የጉባኤ ቦታው እንዲቀየር መወሰኑን የገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ይህ ውሳኔ ተገቢነት የለውም ብሏል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2014 ዓ.ም የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤውን ከነሀሴ 21-ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ እንደሚያካሂድ በቀን 22/11/2014 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ነበር ያሳወቀው።

ፌደሬሽኑ በከተማዋ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ካሳወቀ በኃላ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከፌዴሬሽኑ አብይ ኮሚቴ ጋር በቅንጅት በተሳካ ሁኔታ ማከናወን መቻሉን የጎንደር ከተማ አስተደር ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ገልጿል።

ይሁን እንጅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው ጉባኤውን በመጠበቅ ላይ እያለ አሳማኝ ባልሆነ ምክኒያት ፌደሬሽኑ ጉባኤውን ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበትን ቦታ ቀይሬያለሁ ሲል በቀን 12/12/2014 ዓ.ም ማሳወቁን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

ፌዴሬሽኑ የወሰነው ውሳኔ #ተገቢነት_የሌለው መሆኑን የገለፀው የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፌደሬሽኑ የወሰነው ውሳኔው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ውሳኔውን በድጋሜ ሊጤን ይገባል ብሏል።

(ጎንደር ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopia
#GONDAR

በአጣጥ የኬላ ፍተሻ ላይ 308 ሽጉጥ ተያዘ።

በጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ከተማ 308 የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በኬላ ፍተሻ መያዙን የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አሳውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ሽጉጡ የተያዘው በክፍለ ከተማው በድማዛ ቀበሌ አጣጥ በተባለው የኬላ ፍተሻ መሆኑን ገልጾ 2 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ማለቱን ከጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Bishoftu #Mojo #Debrebrihan ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች መጀመሩን አሳውቋል። ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር #ስምንት የሚያደርሰው ሲሆን ባለፉት ሦስት ሳምንታት ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር እና አዳማ ላይ ሙከራው መጀመሩ ይታወቃል። ደንበኞች…
#Awaday #Gondar

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እያካሄደ የሚገኘውን የሙከራ ኔትዎርክ አገልግሎቱን እያስፋፋ ይገኛል።

ዛሬ በተላከልን መልዕክት ፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች አስጀምሯል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር 10 አድርሶታል። ከዚህ በፊት በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ላይ ሙከራ መጀመሩ ይታወቃል።

የአወዳይ እና ጎንደር ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በአወዳይ አንድ በቀበሌ ዐ1 የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር እና በጎንደር አራት (በፒያሳ፣ አራዳ፣ አዘዞ እና ኮሌጅ) የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው ሲል በላከልን መልዕክት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥምቀት ጎንደር ከተማ በጥምቀት በዓል ሰሞን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጓ አሳውቃለች። የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ፤ በጥምቀት በዓል ሰሞን እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አሳውቋል። በጥምቀት በዓል ወቅት ከ750 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ጎብኚ ወደ ጎንደር እንደሚመጣ ይጠበቃል…
#GONDAR

የጥምቀት በዓል እጅግ በድምቀት የሚከበርባት ጎንደር ከተማ ዝግጅቷ በማጠናቀው እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው።

በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና በክብር ለማስተናገድ ዝግጅታችንን ሁሉ አጠናቀናል ብለዋል።

ዘንድሮ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የከተማ አስተዳደሩ " የጥምቀት በዓልን የጥበብ መፍለቂያና የፍቅር ከተማ በሆነችው በጎንደር  ኑ አብረን እናክብር " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ጎንደር የሃይማኖት፣ የፍቅር ፣ የጥበብ መፍለቂያ፣ የቱሪስት ምስእብ ፣ የኩሩ ህዝብ ባለቤት ከተማ ናት " ያለው አስተዳደሩ ፤ የጎንደር ህዝብ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰው አክባሪ ህዝብ ነው ፤ ኑ የጥምቀት በዓል በጋራ እናክብር ብሏል።

@tikvahethiopia
#GONDAR

በጎንደር ክልከላዎች ተጣሉ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ክልከላዎችን አስቀመጠ።

ኮማንድ ፖስቱ ፤ ክልከላው " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል " የተቀመጠ መሆኑን ገልጿል።

የተቀመጡ ክልከላዎች ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።

3. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
- የልዩ ኃይል ፣
- የፓሊስ ፣
- የመከላከያ ሠራዊት ፣
- የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።

9. ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የመጡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተለልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ  ይጠየቃል።

መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ነው።

@tikvahethiopia
#Gondar

ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት።

አቶ ባዩህ አቡሃይ በዛሬው ዕለት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

የጎንደር ከተማ ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ነው አቶ ባዩህ አቡሃይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ የሾመው።

ምንጭ፦ የጎንደር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
Audio
#Gondar

የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል።

የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል።

በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ መድሃኒት ቤት ከመድሃኒት ውጭ እየሆኑ መሆኑን ገልጿል።

" የከባባድ መሳሪያ ድምጾች ከሆስፒታሉ ውስጥ ሆነን ይሰማን ነበር " ያለው ዶክተሩ ላለፉት ቀናት ከተማዋ በተኩስ ስትናጥ መቆየቷን አመልክቷል።

እስከ ትላንት ሰኞ ከሰዓት ድረስ በግጭቱ ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል የሚያመላልስ እና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ አንድ አምቡላንስ ብቻ እንደነበር እሱም በሚያስዝን ሁኔታ ዒላማ መደረጉን የጎንደር ሆስፒታል ዶ/ር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

የንፁሃን ነዋሪዎች ጉዳይ ትኩረት የሚሻው መሆኑን አስገንዝቧል።

(ድምፅ ዛሬ ጥዋት ላይ የተቀዳ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል። የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል። በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ…
#GONDAR

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህክምና ዶክተር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በከተማው ስላለው ሁኔታ መረጃዎችን አጋርቶናል።

- ታማሚዎች በኦክስጂን እና ደም እጥረት እየሞቱ መሆኑን ገልጿል።

- ለአምቡላንስ ጨምር ምንምአይነት የትራንስፖርት አማራጭ እንደሌለ ፤ ታማሚዎች በሰው ኃይል በሸክም ወደ ሆስፒታሉ እየመጡ መሆኑን አስረድቷል።

- ወደ 20 (ሰላማዊ ሰዎች) ወደ ሆስፒታሉ ከደረሱ በኃላ እንደሞቱ እንዲሁም ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደሚጡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን ገልጿል።

- በርከታ ሰዎች በቤታቸው ሞተው፣ ቀብራቸውም በአካባቢያቸው በተለይም በቀበሌ 4 ፣ 12 ፣ 11 እና 18 መፈፀሙን አመልክቷል።

- ባለፈው ሰኞ በነበረ ግጭት ከሆስፒታሉ የተወሰኑ ህፃዎች በመሳሪያ ቢመቱትም የተጎዳ ሰው ግን እንዳልነበር ገልጿል።

- ሆስፒታሉ ምግብ እንዲሁም መድሃኒት እያለቀበት መሆኑን አመልክቷል።

ዛሬ ጎንደር እንዴት ናት ?

አሁን ላይ በጎንደር ከተማ ከየትኛውም አቅጣጫ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ አይደለም። ጥዋት ላይ ለጥቂት ሰከንድ ፒያሳ እና ቀበሌ 18 አካባቢ ተኩስ ተሰምቶ ነበር።

ከትላንት ማታ አንስቶ ዛሬም ጥዋት በከተማው አብዛኛው ክፍል ላይ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለ ሲሆን ሰራዊቱ በሆስፒታሉ አካባቢም መኖሩን ይኸው ዶክተር ገልጿል።

የህክምና ዶክተሩ ከምንም በላይ በሆስፒታል ያለው የኦክስጅን ፣ የደም እጥረት እንዲሁም የአምቡላንስ ትራንስፖርት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።

ጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ #ጎንደር ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የሆነ ግጭት ካስተናገዱ የአማራ ክልል ከተሞች መካከል አንዷ ናት።

@tikvahethiopia