TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ🚨

" በከፍተኛ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ #የጅብ_መንጋ ተከስቷል ማህበረሰቡ ሊጠነቀቅ ይገባል " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሠላምና ጸጥታ ቢሮ

ከሰሞኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል በምሽት አንዳንዴም በቀን ጅቦች በሰው ላይ በተለይ በህጻናት እና ሴቶች እንዲሁም በአቅመደካሞች ላይ ጥቃት እያደረሱ ተነግሯል።

በደረሰን መረጃ በስልጤ ዞን 2 ሰዎች ሲሞቱ በሀዲያ ዞን እንዲሁም በሀላባ አካባቢ ሌሎች 2 የአካል ጉድለት ያደረሱ ጉዳቶች ተመዝግበዋል።

ከሟቾች አንዷ የ3 ዓመት ህጻን ናት። በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ነዋሪ የሆነችው ይህች ህጻን በእናቷ ጀርባ ላይ ታዝላ (እናትየው ከወፍጮ ቤት እህል አስፈጭታ ስትመለስ) በነበረበት ወቅት አድፍጦ ይጠብቅ በነበረ የተራበ ጅብ ተወስዳ ጉዳት ከደረሰባት በኃላ ህይወቷ አልፏል።

በአጠቃላይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ተመስገን ካሳን አነጋግሯቸዋል።

አቶ ተመስገን ፤ በዚህ አመት ከፍተኛ የጅብ መንጋ መፈጠሩን አመልከተዋል። መንጋው ሲበዛ ለረሀብ በመጋለጡ ወደ ሰዎች እንደሚሄድ ገልጸዋል።

እስካሁን በክልሉ የሁለት ሞትና በርካታ ለሞት ያላበቁ ጉዳቶች ሪፖርት እንደደረሳቸዉ ጠቅሰዉ ጉዳቱ በህጻናት ላይ የበረታ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ባካሄዱት ግምገማ መንጋዉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እንደሆነ ገልጸዋል። ይህን ለማጥፋት ከሚመለከተዉ አካል ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ማህበረሰቡ ግን የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #ጅቦቹ ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ ጀምረዋል " - ነዋሪዎች " በኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጸናት በጅቦች ተበልተዋል። 2ቱ ሲሞቱ አንዷ ተርፋለች " - አቶ ማርቆስ ቡታ ከሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተራቡ ጅቦች እያደረሱ ስላለው ጥቃት የሚመለከቱ መረጃዎችን ማጋራታችን ይታወሳል። በተለይ በስልጤ ዞን እና በሀላባ ዙሪያ በተፈጸሙ የጅብ ጥቃቶች ምክኒያት…
#የጅብ_መንጋ

የጅብ መንጋ ከፍተኛ የሆነ ስጋት በመፍጠሩ ነዋሪዎች በጊዜ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ፤ መጠጥ ቤቶችም ከምሽት 12:00 ሰዓት በኃላ እንዳይሰሩ ተከለከሉ።

በዲላ ዙሪያ ወረዳ #የጅብ_መንጋ በሰው ላይ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ባልተለመደው መልኩ በዲላ ዙሪያ ወረዳ አንዳንድ አከባቢዎች የጅብ መንጋ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ግንቦት 11/2016 በሽጋዶ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ባፋኖ " ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ አንድ ግለሰን አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በጅብ መንጋ መበላታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ ወደ ቤት ሳይመለሱ በመቅረታቸው ቤተሰቦች ፍለጋ በወጡበት ወቅት መንገድ ላይ ልብስ ፣ ጫማ እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ፣ የቀሩ ስጋና አጥንት ማግነታቸውን ተከትሎ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ ነው ግለሰቡ በጅብ መበላታቸው የተረጋገጠው።

በአከባቢው ላይ ከፍተኛ የጅብ ጩኸት እንደነበረ ከአከባቢው ማህበረሰብ ማረጋገጥ መቻሉን ፖሊስ አመልክቷል።

የጅብ መንጋ እንቅስቃሴ ስጋት በመጨመሩ ፦
° ነዋሪዎች በጊዜ ወደየቤታቸው  እንዲገቡ
° ነዋሪዎች ማንኛውም የማህበራዊ እንቅስቃሴ ካደረጉ በኃላ በጊዜ ወደቤት እንዲመለሱ
° ገበያ ከሄዱም በጊዜ ወደ ቤት እንዲገቡ
° ልጆች የቤት እንስሳትን ሲጠብቁ ጥንቃቄ እንድያደርጉ ወደ ጫካ ውስጥ እንዳይሄዱ አሳስቧል።

በተጨማሪ ማነኛውም መጠጥ ቤቶች እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ መስራት እንዳለባቸው ከዚህ ውጭ እንሆናለን ትዕዛዙን አናከብርም በሚሉት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቅርቡ በስልጤ ዞን፣ በሀላባ ዙሪያ ፣ በሀዋሳ ዙሪያ የተራቡ ጅቦች ጉዳት ማድረሳቸውን የሚገልጹ መረጃዎችን ማካፈሉ ይታወሳል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃልም ፤ በከፍተኛ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ #የጅብ_መንጋ መከሰቱን በመግለጽ ማህበረሰቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ ማሳሰቡ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia