TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ለetv የተናገሩት፦

“በሲዳማ ዞን ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ መደፍረስ የጸጥታ ኃይሉ ከሕዝቡ ጋር በመሆን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር አውሎታል። ይርጋለም፣ አለታ ወንዶ፣ ሃገረ ሰላም እና ወንዶ ገነት ችግሮች ተከስተው ነበር፤ በተጠቀሱት አከባቢዎች ንብረት የመዝረፍ እና የማውደም ተግባራት ተስተውሏል፤ በተፈጠረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት አጣርተን ስንጨር ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን!"

#ቢቢሲ_አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እስራኤል ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ #ትግራይ ክልል ማስወጣቷን " ጄሩሳሌም ፖስት " ዘግቧል። እስራኤል በአማራ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭትና የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቅርበት እየተከታተለችው መሆኑ ተነግሯል። ባለፈው ሰኞ ከአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ተጓዥ ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ እንዲወጡ ማድረጓ ተገልጿል። ዘገባው ተካሂዷል ባለው የእስራኤል ዜጎችን ከግጭት ቀጠና…
#Update

እስራኤል ዜጎቿን ከአማራ ክልል አስወጣች።

በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ትዕዛዝ ከ200 በላይ እስራኤላውያን ከባሕር ዳር እና ጎንደር መውጣታቸው ተዘግቧል።

በርካታ ቤተ እስራኤላውያን በሚገኙበት የአማራ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ፦
- የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣
- በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ፣
- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣
- የእስራኤል የደኅንነት ም/ቤት
- የአይሁዳውያን ተቋም በጋር ሆነው ዜጎቻቸው ከክልሉ እንዲወጡ አድርገዋል።

በዚህም ከጎንደር ከተማ 174 ከባሕር ዳር ደግሞ 30 ቤተ እስራኤላውያን ትላንት እንዲወጡ ተድረገዋል።

እስራኤላውያኑ እንዴት ወጡ ?

ረቡዕ ምሽት ላይ ካሉባቸው ከተሞች እንዲወጡ ለማስቻል በተመቻቹላቸው የመሰባሰቢያ ቦታዎች ላይ እንዲገኙ ከተደርገ በኋላ ወደ ጎንደር እና ባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያዎች ተወስደዋል።

በአየር ማረፊያዎቹም ቀድመው በተዘጋጁ ልዩ በረራዎች አማካይነት እንዲጓጓዙ ተደርገው አዲስ አበባ ሐሙስ ዕለት ገብተዋል።

እስራኤላውያኑን ከአማራ ክልል የማስወጣት ተልዕኮ በእስራኤል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ባለ የመከታተያ ክፍል (ሲችዌሽን ሩም) እገዛ የተደረገለት ሲሆን ዲፕሎማቶች፣ የአይሁዳውያን ተቋም ሠራተኞች እና አማርኛ የሚችሉ የእስራኤል ሠራዊት አባላት በቡድኑ ውስጥ ነበሩበት ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት እንዳለው ዜጎቹ ወደ አስራኤል ለመመለስ አስኪወስኑ ድረስ በአዲስ አበባ ውስጥ ይቆያሉ።

ኔትያንያሁ ምን አሉ ?

ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ፤ " እስራኤል ዜጎቿን ባሉበት ቦታ ሁሉ ጥበቃ ታደርጋለች " ያሉ ሲሆን " ባለፉት ቀናት ግጭት ባለበት የኢትዮጵያ አካባቢ ዜጎቻቻን ነበሩ። ከዚያ እንዲወጡ እንዲደረግ አዝዣለሁ " ብለዋል። አገራቸው ዜጎቿን በደስታ እንደምትቀበልም መግለፃቸውን #ቢቢሲ_አማርኛ ዘግቧል።

እስራኤል ከቀናት በፊት ጥቂት ዜጎቿን ከአማራ ክልል ደባርቅ ወደ ትግራይ ሽረ ከተማ ማስወጣቷ ይወሳል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የእስራኤል ጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia