TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሶማሌ_ክልል

አልሸባብ የሽብር ቡድን ዳግም ድንበር አቋርጦ ለመግባት ሞክሮ በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል መታቱ ታውቋል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ሰራዊት ዛሬ ድንበር አቋርጦ ለመግባት የሞከረውን አሸባሪውን የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን መደምሰሱን የክልሉ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

ልዩ ሀይሉ የሽብር ቡድኑን ታጣቂዎች ከመደምሰስ ባለፈ በርካታ የጦርና የመገናኛ መሣሪያዎችን መያዝ ችሏል።

ወደ ውስጥ ለመግባት ከሞከሩ ታጣቂዎች መካከል የተማረኩም አሉበት።

አልሸባብ ከሶማሊያ ሂራን ግዛት ተነስቶ ነው ድንበር አቋርጦ ወደ ሸቤሌ ዞን ፌርፌር ወረዳ ለመግባት የሞከረው።

ነገር ግን በሶማሌ ልዩ ኃይል በደረሰበት ምት ኤል ቁዱን በምትባል ቦታ ላይ ተደምስሷል።

ከጥቂት ቀን በፊት ይህ የሽብር ቡድን ድንበር ጥሶ ሊገባ ቢሞክርም በሶማሌ ልዩ ኃይል ደረሰበት ከፍተኛ ምት ከ100 በላይ ታጣቂዎቹን እንዳጣ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል የሶማሌ ክልል ህዝብ ለልዩ ኃይሉ እያደረገ ያለው ድጋፍና እገዛ እንደቀጠለ መሆኑን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

@tikvahethiopia