TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለኩ⬆️

በለኩ ከተማ በ"እኔም ለወገኔ ወጣቶች" አስተባባሪነት ትላንት በጁኒየር ትምህርት ቤት የተጀመረው የደም ልገሳ በዛሬው ዕለት በለኩ #ሆስፒታል መቀጠሉን ሰምተናል። "ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ውዱ ስጦታ #የደም ስጦታ ነው" በሚል መሪ ቃል ነው የድም ልገሳው እየተደረገ የሚገኘው።

#ደም_በመገስ_ተደምረናል!

©Devila
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ተግባር እንኮርጅ🔝

"የቅዱስ ጊዮርጊሰ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች እና አስተባባሪዎች #የዓይን_ብሌናችውን ለምልገስ ቃል ገቡ። በዛሬው ዕለት በተካሂደው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ #የደም_ልገሳ ፕሮግራም ላይ በተደረገልን ግበዣ መሰረት በደም ባንክ ግቢ ውስጥ በመገኘት በሰራነው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ከ100 በላይ የሚሆኑ የቅድስ ጌወረጊስ ክለብ ደጋፊወች ከህልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸው ተነስቶ ለሌላ ብርሃኑን ላጣ ወገን ተሰጥቶ ብርሃኑ እንድመለስለት በማለት የቃልኪዳን ሰነዳችን ላይ በመፈረም የአባልነት መታወቂያ ወሰውደዋል፡፡ ይህ የቅዱስ ጌወርጊስ ክለብ ቃል የመግባት ስረአት በከለብ ደረጃ ሲካሂያድ የመጀመሪዉና ፈር ቀዳጅ ሲሆን ሌሎች የስፖርት አፍቃሪ ቤተሰብ፣ አመራሮችና ደጋፊወችም የነሱን አርእያ በመከተል የዚህ መልካም ተግባር ተባባሪ እንዲሆኑ ጥሪያችንን እናቀረባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለቅዱስ ጌወረጊስ ክለብ አስተባባሪወች ለደም ባንክ ሃላፊወችና ሰራተኞች ያለንን አክብሮት በመግለጽ ላደረጉለን ቀና ትብብር ሁሉ ልናመሰግናቸው እንወዳለን፡፡ በዓይነዎ ሶስት ጊዜ ይዩበት!!! በርሃን ይስጡ ብርሃን አይቅበሩ!!!" ነጋ ደምሴ አዌርነስ ኮኦርድኔተር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የነዋሪዎች መታወቂያ መታደል ጀመረ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጊዜው #አቋርጦት የነበረውን ነባሩን የነዋሪዎች መታወቂያ እንደገና ማደል መጀመሩን ካፒታል አስነብቧል፡፡ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ኮምፒውተር ላይ የጣት አሻራን በመስጠት ሊያትመው ባሰበው አዲስ የነዋሪዎች መታወቂያ ላይ #በብሄር ማንነት ፋንታ #የደም_ዐይነትን ለማስፈር አቅዶ ነበር፡፡ ሆኖም ባጋጠመው የሶፍትዌር ቴክኖሎጅ ችግር እና በባለድርሻ አካላት ቅንጅት ማነስ ሳቢያ ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም፡፡ እናም ቀደም ሲል በ5 ብር ይሰጥ የነበረውን ነባሩን የቀበሌ መታወቂያ እንደገና ለነዋሪዎች በ10 ብር ክፍያ መስጠት ጀምሯል፡፡ ለመታወቂያ ዕድሳት ከ10-20 ብር፣ የጠፋውን ለመተካት ደሞ ከ10-30 ብር ይከፈላል፡፡ በቅርቡ ግን ሁሉንም ነገር አስተካክየ አዲሱን መታወቂያ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሏል- ኤጀንሲው፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል‼️

ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #የደም_ስር_መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የፒሲአይ የነጻ ህክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑ የገለጸ ሲሆን፥ ህክምናው በግል ሆስፒታሎች ውስጥ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

via walta
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህክምናው ከዛሬ ጀምሮ ይሰጣል!

ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት #የደም_ስር_መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የፒሲአይ የነጻ ህክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ህክምናው የሚሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በጋራ ባስገነቡት የልብ ህክምና ማዕከል ውስጥ ነው ተብሏል፡፡

ማዕከሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ የሚገኝ ሲሆን፥ ህክምናው ከኮሪያ በሚመጡ የህክምና ቡድን አባላትና በማዕከሉ ባለሙያዎች ይሰጣል ተብሏል፡፡

ህክምናው የሚደረግላቸው ታካሚዎች በማዕከሉ ቀጠሮ ተይዞላቸው ሲጠባበቁ የነበሩ መሆናቸውን ማዕከሉ ይፋ አድርጓለ፡፡ይህ ህክምና ለዘጠነኛ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን፥ በዚህ ዙር የፒሲአይ ህክምና ብቻ እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡

ህክምናው በጣም ውድ ከሆኑ የልብ ህክምና አገልግሎቶች አንዱ ሲሆን፥ በግል ሆስፒታሎች ከመቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ ተግልጿል፡፡

በመሆኑም ከፍለው መታከም ለማይችሉ ታካሚዎች ማዕከሉ በነጻ ህክምና አገልግሎት መስጠቱ ለታካሚዎቹ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ ቀደም ከኮሪያ፣ ከአሜሪካና አውስትራሊያ በመጡ የልብ ህክምና ቡድኖች የፒሲአይ አገልግሎትን ጨምሮ የቫልቮቶሚና የፔስሜከር የልብ ህክምና አገልግሎቶች መሰጠታቸው ይታወሳል፡፡

ባለፉት ጊዜያት ከዘጠና በላይ ለሚሆኑ #ታካሚዎች አገልግሎቱን ማግኘታቸውን ከቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 20/2011 ዓ.ም.

የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ፍራንክ_ዋልተር_ሽቴይንሜይር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
.
.
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ አቶ #ዳዊት_ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።
.
.
ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #የደም_ስር_መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የፒሲአይ የነጻ ህክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ካሉት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
ለኢፌድሪ ፕረዝዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) የEuropean Tourism Academy Membership ሽልማት ሊሠጥ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 4 ሚሊየን 234 ሺህ 856 መቶ ተሸከርካሪዎች በማስተናገድ በአጠቃላይ ብር 124 ሚሊየን 578 ሺህ 594 መቶ ብር መሰብሰብ መቻሉ ተሰምቷል።
.
.
#አለን_ኢትዮጵያ የበጎ-አድራጎት ድርጀት የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል ህጋዊ እውቅና በማግኘት ትላንት በ19/05/01 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ሥራ ጀምሯል።
.
.
በአንድ ፒካፕ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዙ የነበረ ሦስት መትረየስ፣ 1924 የስታር እና 1856 የማካሮቭ ሽጉጥ ጥይቶች ከ37 የጥይት መያዥ ጋር #መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ቮልስዋገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
የሚድሮክ ግሩፕ የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንን ከእስር #መፈታትን ምክንያት በማድረግ ሠራተኞቹን #አንበሻብሿል
.
.
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሙስና ተጠርጣሪው የጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም #ኢሳያስ_ዳኘው ፈቅዶት የነበረውን የዋስትና መብት ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሻረው ካፒታል ዘግቧል፡፡
.
.
ጠ/ሚር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ምሽት #በብሄራዊ_ቴአትር በየሶስት ወሩ የሚካሄደውን የኪነ ጥበብና የባህል ምሽት ተካፍለዋል።
.
.
ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ፦ የሚድሮክ ንብረት በሆነው #ዩኒቲ_ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ላንድ ወሰነ ትምህርት(1 ሴሚስተር) #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡
.
.
ምንጭ፦ ዋልታ፣ ፋና፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ሬድዮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጎንደር👆

"ዛሬ በጎንደር ከተማ #የረመዳን መግቢያን በማስመልከት በረመዳን ወር ተወዳጁ ስራ #ሰደቃ እንደመሆኑ የበረካ 'የበጎ አድራጎት እና የልማት ማህበር' ትልቁን ሰደቃ #የደም_መለገስ ፕሮግራም ያካሄደ ሲሆን በ45 ወንዶች እና በ1ሴት በጥቅሉ የ46 ሰዎች የደም ልገሳ አካሂደዋል #አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላቹህ!" Nurhusien Shimelash

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቀለ👆

"ትናንት በመቀለ #አረህማን_መስጊድ የአካባቢው ነዋሪዎች ከመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በመተባበር ታላቁን የረመዷን ወር በማስመልከት #የደም_ልገሳ ኘሮግራም አድርገዋል፡፡ ከሀያ በላይ ሴቶችና ከአርባ በላይ ወንዶች የተሳተፉበት ሲሆን በአጠቃላይ 75 ሠወች ደም ለግሰዋል፡፡ ነዋሪዎችና የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተመሳሳይ ወገንን ደም በመለገስ የመርዳት ተግባር ከዚህም በፊት በተደጋጋሚ ያደርጉት ነበር፡፡ስራቸውም ይበል የሚያሰኝና ለወደፊቱም ሊቀጥሉበት የሚገባ ሠናይ ምግባር ነው፡፡ ተምኪን ነኝ ከአይደር ግቢ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ዛሬ የዓለም የደም ግፊት ሕመም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው፡፡

በሽታው ምንም አይነት የህመም #ምልክት_ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል።

በዚህ ምክንያት አንዳንዴ የደም ብዛትድምጽ አልባው ገዳይ በሚል ስም ይጠራል።

የደም ግፊት ያለበት ሰው ምልክት ባያሳይም ሰውነቱ እየተጎዳ አይደለም ማለት አይደለም። እንዲያውም ህክምና ያልተደረገለት የደም ግፊት ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል።

ከነዚህም መካከል የኩላሊት በሽታ፣ የአይን ህመም እና የልብ እና የደምስር በሽታዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ሆኖም ህሙማኑ በአብዛኛው የሚከተሉት ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላል፡፡
➡️ የራስ ምታት
➡️ የአይን ብዥታ
➡️ ራስ ማዞር
➡️ ደረት ላይ የሚሰማ ህመም

መልዕክቱን አዘጋጅቶ ያሰራጨው ፦ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ነው።

#የደም_ግፊትዎን_በየጊዜው_ይለኩ !

#worldhypertensionday17may #hypertension
#WorldHypertensionDay

@tikvahethiopia