TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

በትግራይ የክረምቱ ሃይለኛ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፋዋል።

በበርካታ የክልሉ አከባቢዎችም ከአሁን በፊት ታይቶ በማያውቅ መልኩ የመሬት መደርምስ አደጋ እየተከሰተ ነው።

ነሃሴ 17 እና 19/2016 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሓውዜንና ብዘት ወረዳዎች የጣለ ሃይለኛ ዝናብና በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ ውሃ የ7 እና 9 ዓመት እድሜ ህፃናት የሚገኙባቸው 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የሓውዜን ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ህፃናቱ በአከባቢያቸው በሚገኘው በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ የዝናብ ውሃ ሊዋኙ ሲሉ ነው ለህልፈት የተዳረጉት። 

በዞኑ ብዘት ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት በሃይለኛ ዝናብ ምክንያት ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሶ የ5 ልጆች አሳዳሪ የሆኑ ባልና ሚስት ወድያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

ልጆቻቸው እቤት ስላልነበሩ የሟቾች ቁጥር ሊቀንስ እንደቻለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከወረዳው ያጋኘው መረጃ ያሳያል።

ልጆቹ ወላጅ እናት አባታቸውን አጥተው በፈረሰ ቤት ሜዳ ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

ከአሁን በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።

በአላጀና ሰለዋ ወረዳዎች በሚገኙ አራት የቀበሌ ገበሬ ማህበራት ፣ በእንደርታና ሕንጣሎ ወረዳዋች ፣ በዓዴትና ፀለምቲ ወረዳዎች የመሬት መደርመስ አደጋ መከሰቱ ከአከባቢዎቹ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#ትግራይ

በአንድ ሳምንት ብቻ የክረምቱ ከባድ ዝናብና ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የሰው ህይወት ጠፍቷል። አዝርእት ወድሟል። በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተወስደዋል። 26 አባወራዎች አፈናቅሏል።

በያዝነው ሳምንት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በከባድ ዝናብና ጎርፍ ከፍተኛ የተባለ አደጋ ደርሷል።

በአጠቃላይ 25 ሰዎች እንደሞቱም ተነግሯል።

በአፅቢ ወረዳ ያጋጠመው አደጋ ግን የከፋ ነው ተብሏል።

በአፅቢ ወረዳ " ስዩም ቀበሌ ገበሬ ማህበር " ሃይለኛ ዝናብ ቤት አፍርሶ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አልፏል።

ቤቱ በውድቅት ሌሊት መፍረሱ አደጋውን የከፋ አደርጎታል።

ቤተሰባቸው ያጡ እማወራ እንዳሉት ፥ ባለቤታቸውና ሁለት ልጆቻቸው በአደጋው ምክንያት በማጣታቸው የመኖር ተስፋቸው ጨልሞ ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

የአደጋው ሰለባ የመኖር ተስፋቸው ዳግም እንዲያንሰራራ መንግስትና አቅም ያለው ሁሉ እንዲያግዛቸው ጥሪ አማቅረባቸውን ከዞኑ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተያያዘ በቀጠለው ሃይለኛ ዝናብና ከባድ ክረምት በተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መንሸራተት እየተስተዋለ ነው።

በአምባላጀ ፣ በእንትጮ ከተማ ዙሪያ ሃይለኛ ዝናብ ያስከተለው የመሬት መንሸራተት 31 ቤቶች አፍርሶ 31 ሄክታር መሬት ላይ የነበረውን አዝርእት ከጥቅም ውጭ በማድረግ ዘጠኝ አባወራዎች አፈናቅሏል።

እንስሳትም በጎርፍ ተወስደዋል። 

በመቐለ ዙሪያ የሚገኘው የገረብ ግባ ግድብ ከልክ በላይ ሞልቶ በመፍሰሱ ምክንያት በ 138 ሄክታር መሬት የተዘራ እህል ላይ ጉዳት አድርሷል።

በአደጋው የተጎዱ 270 የእንደርታ ወረዳ አርሶ አደሮች ጊዚያዊ  አስተዳደሩ ግብረ ሃይል አቋቁሞ እንዲያግዛቸው ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

" እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴና መሳሳብ ህዝብ ስላልወደደው አሁኑኑ መቆም አለበት !! " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ም/ ፕሬዚደንትና የሰላምና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ካቢኔ ሃላፊ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ፥ " በአሁኑ ወቅት ለሁለት በተከፈለው ህወሓት መካከል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴና መሳሳብ ህዝብ ስላልወደደው መቆም አለበት " ብለዋል።

ሌ/ጄነራሉ " በተቃውሞ ሆነ በድጋፍ የህዝብ ማእበል ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ህዝቡ ስጋት ውስጥ እየከተተ ስለሆነ ከአሁን ጀምሮ መቆም አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

" ሰላማዊ የአዳራሽ ውስጥ ሰብሰባ ማድረግ ይፈቀዳል " ሲሉ አክለዋል።

ሌ/ጄነራል ታደሰ " አዳዲስ የመንግስት የስራ ምደባዎች እየታዩ ነው ምደባዎች እንዲቆሙ ሁሉም ነገሮች በስከነ አካሄድ እንዲፈፀሙ እንጠይቃለን " ብለዋል።

" የማስማማት ጥረት እየተደረገ ነው (ለሁለት የተከፈሉትን የህወሓት አመራሮች) ፤ ከተቻለ አንድ እንዲሆኑ ካልተቻለ ልዩነታቸው አክብረው በህግ እንዲጓዙ ከዚህ ውጭ ያለው አካሄድ ግን ቀይ መስመር አለው የሚባል ስላልሆነ መገታት አለበት " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል ሌ/ጄነራሉ " የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች ዘላቂ ግንኙነት የሚጎዳ ማንኛውም እንቅስቃሴ መቆም አለበት " ብለዋል።

ተመላሽ ተፈናቃዮች ላይ ሰላምን የሚረብሽ እንቅስቃሴ እንዳለ በመጠቆም " ይሄ መቆም አለበት " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ይህንን ዓይነት እንቅስቃሴ ፍሬ ያለው ትርጉም የሌለው መሆኑ ካለፈው እንማር " ሲሉ ገልጸዋል።

" በጠብመንጃ የሚወሰድ መሬትም ሆኖ የሚቀየር ድንበር የለም ስለሆነም በአማራ ክልል በኩል ያሉ ታጣቂዎች ከድርጊታቸው በመቆጠብ ወደ ቀልባቸው ይመለሱ " ሲሉ ማሳሰባቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመግለጫው የአማራ ክልል ስም በመነሳቱ በክልሉ በኩል የሚሰጥ ምላሽ ጠይቆ ያቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#TigrayRegion

" የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለ ነው " - የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር

በትግራይ ዛላኣንበሳና ኢሮብ የኢትዮ-ኤርትራ ደንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር አሳውቋል።

አሁንም ላለፉት 4 ዓመታት አከባቢ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ስምንት የሚደርሱ የጉሎመኻዳና የኢሮብ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ላይ የታየ አዲስ ለውጥ እንደሌለ ተመላክቷል።

ከሰሞኑን አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች " በትግራዩ ዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ አለ " ዘገባ ሲያሰራጩ ነበር።

የአከባቢው ነዋሪዎችና የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ግን ይህ ሀሰት ነው ሲሉ መልሰዋል።

ነዋሪች እና የዞኑ አስተዳደር " በዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅሰቃሴ የለም " ብለዋል።

የምስራቃዊ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህ/ቤት የጉሎመኻዳና ኢሮብ ወረዳ አስተዳደሮች ጠቅሶ ባሰራጨው መረጃ ፥ አከባቢዎቹ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊትም ሆነ በኋላ በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

" ሉኣላዊ ግዛት ያለመከበር ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ባላፉት ቀናት በአከባቢው አዲስ ወታደራዊ እንቅሰቃሴ የለም " ብሏል። 

" በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች በዛላኣንበሳና በኢሮብ አከባቢ ከኤርትራ መንግስት በኩል የተለየ እንቅሰቃሴ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለና የአከባቢው ነዋሪዎች ይሁንታ ያለገኘ ነው " ሲል አክሏል።

አስከ አሁን ድረስ ዛላኣንበሳ ከተማ ጨምሮ 5 የጉሎመኸዳ ወረዳ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም ከኢሮብ ወረዳ 4 የገጠር ቀበሌዎች  በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ፅ/ ቤት አስታውሷል።

ዞኑ " በሬ ወለደ ወሬ የሚናፍሱ ሚድያዎችና የማህበራዊ ትስስር ገፅ ፀሃፊያን ከድርጊታቸው እንደዲታቀቡ እናሳስባለን " ሲል አስጠንቅቋል።

በቅርብ እና በረቁ የሚገኙ የዓጋመና አከባቢዋ ተወላጆችና ወዳጆች በየዓመቱ በትግራይ ደረጃ በዓዲግራት ከተማ የሚከበረው የመስቀል በዓል ለማከበር እንዲታደሙ ጥሪ በማቅረብ አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ እንዳለ አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Tigray የትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው የተደገፈ ይፋዊ ምክክር አደረጉ። ዛሬ በዓፋርዋ ሰመራ ከተማ የተሳለጠው ግንኙነት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ እና በዓፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ የተመራ ነው።  በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ሰመራ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ፕሬዜዳንት አወል አርባ እና ካቢኔያቸው አቀባበል አደርገውለታል። የሁለቱ…
#Afar #Tigray

ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ።

በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል።

ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል አጎራባች ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጸጋይ ገብረተኽለ ፥ " ውይይቱ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ጉርብትና ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያግዝ ውጤታማ ውይይት ነው " ብሎውታል።

" በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ፣ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ፣  ነፃ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እና የቆየው የሰላም እና የልማት ግንኙነት እንዲቀጥል በውይይቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።

" ሁለቱ ክልሎች በሚያዋስኑ አከባቢዎች ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚከሰቱ " የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው " ግጭት ጠማቂዎችና ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ ፣ የጋራ የሰላም እና የፀጥታ እቅድ እንዲኖርና በየወሩ እየተገመገመ እንዲመራ ትግራይ እና ዓፋር ተስማምተዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል የነበረው የአንድ ቀን ቆይታ አጠናቅቆ ወደ መቐለ መመለሱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት በመጥቀስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia  
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ። በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል። …
#TPLF

" ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን

በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል።

" ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን አሳውቋል።

የቁጥጥር ኮሚሽኑ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ጉባኤ ያካሄደው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ህጋዊ ነው " ብሏል።

" የህወሓት መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 8 ቁጥር 4 በውሳኔ አሰጣጥ ላይ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው በብዙሃን ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ያስቀምጣል " ያለው መግለጫው " በዚሁ መሰረት በ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ከጠቅላላ ተሳታፊ 83 በመቶ ጉባኤተኛ የተገኘበት " ህጋዊ ነው !! " ብሎታል።   

ስለሆነም " ህጋዊ አለመሆኑን እያወቀ ህጋዊ መስሎ ማደናገር አግባብነት እና ተቀባይነት ያለው አይደለም " ሲል በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት ከሷል።

" ከጉባኤ ራሳችን አግልለናል ወይም ወደ ጉባኤ አንገባም ያሉት በድርጅቱ መተዳደሪያ ህገ ደንብ መሰረት ከድርጅት አባልነታቸው እንደተባረሩ እውነት ነው ፤ በተግባር ግን የህወሓት ስም ፣ አርማ ፣ ሎጎ እና የድርጅቱ ሃላፊነት በመጠቀም ህዝብ በማድናገር ላይ ተጠምደዋል " ብሏል የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን መግለጫ።  

" ከጉባኤ በመሸሽ ሁሉም አይነት ክህደት በድርጅቱ ላይ ፈፅመህ ስታበቃ እኔ ህወሓትን ነኝ የሚል የከሰረ የማደናገር  ፓለቲካ ማራመድ ህጋዊ ፣ ፓለቲካዊ ፣ ሞራላዊ እና ታሪካዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል ሆኖ አግኝተነዋል " ሲል አክሏል።

" የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከድርጅቱ የተባረሩት አካላት #ከያዙት_ፓለቲካዊ_ስልጣን_እንዲነሱ ፤ በህወሓት ስም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን " ብሏል።

ቁጥጥር ኮሚሽኑ ፥ " ህዝብ በማድናገር ላይ ይገኛሉ " ሲል ክስ ያቀረበባቸው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን የህወሓት ቡድን " ህዝብ እንዲታገላቸው " ሲል ጥሪ አስተላልፏል። 

" ህወሓት ለ2 እንደተከፈለ ተደርጎ የሚቀርበው ተረክ ከህወሓት አልፎ ህዝብ ስለሚጎዳ በፍጥነት መታረም አለበት " ብሏል።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት  መስከረም 23 /2017 ዓ.ም ባወጣው  መግለጫ  " የህወሓት ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Mekelle

° " መንግስት ቃሉና መመሪያው ማክበር አለበት " - የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች

° " ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም " - የትግራይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ


በመላ ትግራይ በተለይ በመቐለ የሚገኙ የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ከቤት መስሪያ ቦታ ጋር በተያያዘ ከአንድ ሳምንት በላይ ወደ ክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት ምላሽ ለማግኘት ቢመላለሱም ሰሚ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

ትላንት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት የተሰባሰቡት የ 3043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ለጥያቄያቸው ምላሽ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀርተዋል።

በቦታው የተገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮችና ጥያቄና የክልሉ መንግስት ምላሽ ተመልክቷል።

60,860 አባላት ያቀፉት 3,043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበራት ከጦርነቱ በፊት ተደራጅተው ህጋዊ እውቅና በማግኘት ለቤት መስሪያ የሚሆን ገንዘብ በባንክ ሲቆጥቡ መቆየታቸው ይናገራሉ።

ማህበራቱ ቢያንስ በአንድ ቤተሰብ 5 አባላት ቢኖሩ መንግሰት ቃሉ እንዲጠብቅ እየቀረበለት ያለው ጥያቄ የ300 ሺህ ሰዎች መሆኑን ጠቁመዋል።

ተወካዮቹ ፤ " እኛ በሦስተኛ ዙር የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር ስንደራጅ በክልሉ መመሪያ 4/2011 መሰረት ከኛ በፊት በሁለት ዙር እንደተስተናገዱት 70 ካሬ ለቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጠን ተሰማምተን ነው " ብለዋል።

የክልሉ አስተዳደር ግን ከጦርነቱ በኋላ ጥያቄያቸውን ላለመለስ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለቱ እንዳሰዘናቸው በአደባባይ ወጥተው ገልፀዋል።

" የክልሉ አስተዳደር በመመሪያ 4/2011 የገባው ቃል ይተግብር " ተወካዮቹ ፥ በሚሰጣቸው 70 ካሬ ቦታ ቤት ለመስራት እንጂ ኮንደሚንየም ማለትም የጋራ መኖሪያ ቤት ለመስራት ቃል እንዳልፈፀሙ አስረድተዋል።

የማህበራቱ አመራሮች ከቀናት በፊት ለጥያቄያቸው ተገቢ ምላሽ ለማግኘት ለክልሉ ምክትል ጊዚያዊ አስተዳደር ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ጥያቄ አቅርበው ከክልሉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በመነጋገር መልስ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ቢሆንም አስከ አሁን የተሰጣቸው ምላሽ እንደሌለ ተናግረዋል።

ከአንድ ሳምንት በፊት የክልሉ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃድቕ ለድምፂ ወያነ ትግራይ ጉዳዩ በማስመልከት በሰጡት ማብራርያ ፤ ማህበራቱ ከጦርነቱ በፊት ለእንያንዳንዱ አባል 70 ካሬ መሬት ለቤት መገንብያ እንዲሰጥ በሚፈቅደው መመሪያ መደራጀታቸው አምነዋል።

"ይሁን እንጂ ከአሁን በኋላ ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም ፤ ስለሆነም ማህበራቱ የሚሰጣቸው ቦታ G+4 ወደ ላይ የሚገነባ የጋራ መኖሪያ አፓርታማ ነው " ብለዋል።

የማህበራቱ ተወካዮች በቢሮ ሃላፊዋ መልስ እንደማይስማሙ ገልጸዋል።

ለፍትሃዊ ጥያቄያቸው ፍትሃዊ ምላሽ ለማግኘት በማለምም ትላንት ቅዳሜ ቀኑን ሙሉ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት ጠብቀው የሚያናግራቸው የመንግስት የስራ ሃላፊ ባለመገኘቱ ነገ ሰኞ ጥያቄቸውን በሰላማዊ ሁኔታ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርዓት አልበኝነት ለመቆጣጠር " የጥፋት ሃይል " ሲል በስም  ባልገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።

" ህግና ስርዓት ለማስክበር የተጀመሩ ጥረቶች በማጠናክር የህዝቡ ስጋት ከግምት ያስገባ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 27/2017 ዓ.ም ያወጣውን የመንግስታዊ ስልጣን ሹም ሽር የነቀፈው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " ቡድኑ ወደ ስርዓት አልበኝነት ለመሸጋገር የሚያስችለው ግልፅ  መንግስታዊ ግልበጣ ማካሄዱን አውጇል " ሲል ከሰዋል።  

" ቡድኑ የመንግስት ስልጣን እንዴትና በምን ሁኔታ እንደሚያዝ ተደብቆት ሳይሆን ከዛሬ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ለማሳካት ሆን ብሎ ያደረገው ነው " ብሏል የጊዚያዊ አስተዳደሩ። 

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህንን ስርዓት አልበኝነት በትእግስት አያልፈውም " ብሎ " የጥፋት ሃይል " ሲል በገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል ብሏል።

" በሂደቱ ለሚፈጠር ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በጉባኤ ያልተሳተፉ 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች በጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች ለመተካት " ወሰኛለሁ " የሚል መግለጫ ዛሬ መስከረም 27/2917 ዓ.ም ማውጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ታፍኖ ከተወሰደ ከ5 ቀናት በኋላ ተገድሎ አስክሬኑ ወንዝ ተጥሎ ተገኝቷል " - የትግራይ ነፃነት ፓርቲ

የትግራይ ነፃነት ፓርቲ የአመራር አባሉ ታፍኖ ከተወሰደ በኃላ ተገድሎ አስከሬኑ ወንዝ ተጥሎ እንደተገኘ ገለፀ።  

ፓርቲው ታፍኖ የተወሰደውን የአመራር አባሉን ላለፉት ከ5 ቀናት ሲፈልግ የቆየ ቢሆን ተገድሎ አስክሬኑ ወንዝ ተጥሎ ማግኘቱ አሳውቋል።

የፓርቲው ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደጀን መዝገበ " አሰቃቂ ድርጊቱ የተፈፀመው በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ነው " ብለዋል።

ተገድሎ የተገኘው የፓርቲው አመራር አባል በወረዳው የፓርቲው አስተባባሪ መሆኑን ገልጸው ፥ " ታፍኖ ከተወሰደ ከ5 ቀናት በኋላ ተገድሎ ሬሳው በወንዝ ተጥሎ ተገኝቷል ይህ ጭካኔ የተሞላበት አረመንያዊ ድርጊት ነው " ሲሉ አውግዘውታል። 

ሊቀ-መንበሩ በዞኑ የሚገኙ አባላቱ " ' ፓርቲው መደገፍ ህወሓት መቃወም አቁሙ አለበለዚያ ትገደላላችሁ ' የሚል ማስፈራርያ ደርሶዋቸዋል " ሲሉ ' ህወሓትን ክሰዋል።

ህወሓት ለቀረበበት ክስ እስካሁን የሰጠው መልስ የለም። 

" ተግባሩን የህወሓት አባላት ነው እየፈፀሙ የሚገኙት " በማለት ያቀረቡትን ክስ ያጠነከሩት የፓርቲው ሊቀመንበር " በ19 የፓርቲው አባላት አፈና ፣ ደብደባና ግድያ ደርሷል " ማለታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
🔈 #የሰራተኞችድምጽ

" የምንሰራው ስራና የሚከፈለን ወርሃዊ ደመወዝ አይመጣጠንም ፤ ድካማችንን የሚመጥን ክፍያ አናገኝም " - ሰራተኞች

በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራው ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ድርጅት አንዱ በሆነ መስፍን ኢንዳትሪያል ኢንጅነሪነንግ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የመብት ጥያቄ እንዳላቸው ገለጹ።

ሰራተኞች ዛሬ ስራ በማቆም ወደ ትእምት ( ትግራይ መልሶ ግንባታ) ዋና ቢሮ በመጓዝ " የመብት ጥያቂያችን ይመለስ " ብለዋል።

ብዛታቸው ከ150 በላይ የሆኑ ሰራተኞቹ ፦

➡️ የሚሰሩት ስራና የሚከፈላቸው ወርሃዊ ደመወዝ እንደማይመጣጠን፤

➡️ በድርጅቱ በቀን አስከ 20 ሰዓታት የሚሰሩ ሰራተኞች ቢኖሩም የሚያከፈላቸው ከፍያ እጅግ አነስተኛ መሆኑ፤

➡️ ደርጅቱ አትራፊ ቢሆንም ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ፤

➡️ ከጥቅማጥቅም ፣ ያልተከፈለ ውዙፍ ደመወዝና የሰራተኛ ቅጥር ጋር የተያየዘ ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።

" ለረጅም ጊዜ የመብት ጥያቄያችንን የሚመጥን አስቸኳይ መልስና መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

ለሰራተኞቹ ዘግይተው መልስ የሰጡት የትእምት የሰው ሃይል አስተዳደር ተኽለወኒ ገ/መድህን ፥ " ቀጣዩ አርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ከትእምት ኢንደውመንት አመራሮች በጋራ በመሆን ጥያቄያችሁ እናደምጣለን " በማለት ሸኝተዋቸዋል።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪነንግ በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራ ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ካምፓኒዎች አንዱ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM