TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅማ የቲክቫህ ቤተሰቦች...

"ዛሬ በጅማ ከፍተኛ ተቃውሞ ነበር፤ አክቲቪስትና የOMN ዳይሬክተር ጀዋር መሀመድ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ነው በሚል የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ደምፃቸውን #በሰላማዊ መንገድ ነው ያሰሙት። በአሁን ሰዓት በከተማው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ይታያል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...በምርጫው ዕለት በአገሪቱ ደም ለማፋሰስ የሚፈልጉ ኃይሎች ነበሩ ነገር ግን ሴራቸው ከሽፏል" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫውን #በሰላማዊ መንገድ በማከናወን በእለቱ ደም ለማፋሰስ ያቀዱ ኃይሎችን ሴራ አክሽፏል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

ቃል አቀባዩ ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

አምሳባሳደሩ በምርጫው ወቅት እና ከምርጫ በኋላ በአገሪቱ ደም እንዲፋሰስ የሚፈልጉ ኃይሎች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

በምርጫው እለት የነበረውን ሂደት በርካታ አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በስፋት ሽፋን የሰጡት መሆኑንም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫው ታማኝና ሰላማዊ እንደነበር ማረጋገጡንም አክለው መናገራቸውን ኢዜአ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት #በሰላማዊ_መንገድ ለመፍታት ሰላማዊ ድርድሮች እንዲጀመሩ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀመጠ።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አስታወቁ።

ዶ/ር ጌዲዮን ፓርቲው ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ ዉሳኔ አሳልፏል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተካሄደው ጦርነት መንግሥት ተገዶ የገባበት መሆኑን ገልፀው ፤ መንግሥት ይህንን ለመፍታት እየሠራ ስለመሆኑም አስረድተዋል ።

ፓርቲዉ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዳይኖር ታሳቢ በማድረግ #ለሰላም_ቅድሚያ_ይሰጣል ነው ያሉት።

ዶክተር ጌዲዮን እንዳሉት ፓርቲዉ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የሰላም አማራጩ፡-

1. ሕገ መንግሥታዊ እና ሕጋዊነትን የሚያስከብር መሆን አለበት፡፡

2. የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ መሆን አለበት፡፡

3. በሀገር ዉስጥ መፍታት ካልተቻለ #በአፍሪካ_ሕብረት ጉዳዩ መታየት እንዳለበት በሥራ አስፈጻሚ እና በማእከላዊ ኮሚቴ ዉይይት ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል።

በተጨማሪም ትንኮሳዎች ካሉ ሕግ አስከባሪዉ አካል እርምጃ እንዲወሰድ ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል። ሕዝቡም ለዚህ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት ይደረጋል ያተባለው የኢጋድ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የአባል ሀገራት መሪዎች ናይሮቢ እየገቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። ናይሮቢ ከደረሱ መሪዎች መካከል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳኑ ወታደራዊ አስተዳደር መሪ እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ይጠቀሳሉ። ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር…
#SUDAN #ETHIOPIA

የኢትዮጵያ እና የሱዳን ጉዳይ !

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸው ገለፁ።

ኬንያ ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሃን ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " ሁለቱ ሀገራት በሰላማዊ መንገድ ሊሠሩባቸው የሚችሉ በርካታ የትብብር መሠረቶች እንዳሏቸው አረጋግጠናል " ብለዋል።

" ያለን ትሥሥር ከየትኛውም መከፋፈል የሚበልጥ ነው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ሁለታችንም ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮችን #በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ENDF የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ለህ/ተ/ም/ቤት እንዲላክ ተወሰነ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አሁን በሥራ ላይ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል። የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ውሳኔ ካሰለፈባቸው ጉዳዮች አንዱ የመከላከያ…
" ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን "

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፦

" በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩት ግጭቶች #በሰላማዊ_መንገድ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በተደራጀ ኃይል ውስጥ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ፣ በአገሪቱ የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲሳተፉ ለማስቻል ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለም/ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ "

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ባለፈው ሳምንት ህዳር 27 ቀን 2015 እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቢዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሰነድ ፈረመዋል።

ስምምነቱ ዋነኛው ተግባር ምንድነው ? ፋይዳውስ ? ስለ ስምምነቱስ በጋራ ምን አሉ ?

" የትብብር ስምምነቱ ፓርቲዎቻችን በሚከተሉት አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራና በትብብር እንዲሠሩ ማዕቀፋዊና ሞራላዊ ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡

በሀገራዊ መግባባት፣ በምርጫ፣ በሰላም ማስፈን እና መሰል ጉዳዮች  ላይ የጋራ አቋሞችን በማራመድ #በሰላማዊ_መንገድ በትብብር #እንታገላለን፡፡

በተለይ በየዕለቱ ለሚሞተው እና በድርሱልኝ ሲቃ ለሚቃትተው ወገናችን ድምጽ በመሆን ከገባበት ችግር እንዲላቀቅ መሥራት ከግንባር ቀደም ተግባሮቻችን ዋናው ነው፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OLF50

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አለው ?

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፤ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ አማካኝነት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው  መግለጫ ወቅት ፓርቲው መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ ስለሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) የታጠቀ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው እንደሆነ ማብራሪያ ሰጥቷል።

አቶ ዳውድ ኢብሳ ምን አሉ ?

" የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር አሁን ላይ ግንኙነት አለው ወይ ለሚለው፤ ያ ሰራዊት የፖለቲካ ጥያቄ ያለው ሰራዊት ነው፡፡

አባላቶቹን ለምን እንደሚታገል አስተምሮ ነው ወደ ጦር የሚያሰማራው፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ደግሞ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ይህን ትግል #በሰላማዊ መንገድ እያካሄደ ነው፡፡

ይህ መንግስት አለመግባባቱ በተፈጠረ ጊዜ ኦነግን ገመድ ውስጥ አስገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን ነው የጠየቀው፡፡ ትጥቅ አልፈታም ያለው ያ ሰራዊት የኔ ነው ወይስ አይደለም እንድንል፡፡

በወቅቱ ከአባገዳዎች ጋር ሆነን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ባደረግነው ጉባኤ መንግስት ስምምነቱን አፍርሷል ብለን በማመናችንና ጦሩን ማስገባት ስርዓት ስላለው እኛ በወቅቱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ለአባገዳዎች ሰጥተን ነው ከመሃል የወጣነው፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከጦሩ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡

ያን ተከትሎ በምርጫ ቦርድ በሕጋዊ መሰረት ብንንቀሳቀስም ይሄው ቤት ውስጥ እስከመታገት የሚደርስ ጫና ደርሶብናል፡፡ የኦነግ እንቅስቃሴ ግን በተለያየ መንገድ ቀጥሏል እንጂ አይገታም፡፡

አሁንም የምንጠይቀው መንግስት ሰላም እንዲወርድ ተቀምጦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ግደታውን ይወጣ።

በኦሮሚያ ለሁሉም ዜጋ እኩል ክብር እንዲሰጥና መከባበር እንዲሰፍን እንጠይቅላለን። "

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ አቋሙ ምንድነው ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ለማፍረስ ይቋምጣሉ " ያላቸውን በስም ያልጠቀሳቸውን ኃይሎች ዓላማ ለማክሸፍ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ይህንን የገለፀው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ነው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በስም ያልገለፃቸውና በአማራ ክልል ውስጥ ይገኛሉ ያላቸው ' ፅንፈኛ ' ሲል የጠራቸው ኃይሎችና አጋሮቻቸው " ትግራይ ላይ አሰበዉት የነበረውን የጥፋት አላማ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዳከሸፈባቸው በአደባባይ የሚያማረሩበት ፤ ብሎም ከፌዴራል መንግስት ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ የገቡበት ሁኔታ ሲፈጠረ ፀረ ፕሪቶሪያና ፀረ ትግራይ አቋማቸውን በግልፅ በማራገብ ላይ ይገኛሉ " ብሏል።

" ይህን እንቅስቃሴ እንመራለን የሚሉ አመራሮችም ሆኑ አጋሮቻቸው እንዲሁም ያሰማሯቸው የሚድያ አፈቀላጤዎችና የርእዮተ አለም መሪዎች ፣ መከላከያ ሰራዊቱ በመውሰድ ላይ ያለውን እርምጃ ‘የህወሓት ቀጥተኛ ተሳትፎ አለበት’ በሚል በሬ ወለደ ጩኸት እየደረሰባቸው ላለው ሽንፈት የትግራይን ህዝብ ሰበብ ለማድረግ  ሲዳክሩ ይሰማሉ " ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ " የፌዴራል መንግስት በነዚህ ሀይሎች ላይ እየወሰዳቸው ላሉ እርምጃዎች የትግራይንም ሆነ የሌላውን ወገን የተለየ ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለን አናምንም " ያለ ሲሆን " ይሁንና ግን ፀረ ሰላም አቋማቸውን ለማራመድ እስኳሁን ሲረጩት የነበረውን መርዝ  አልበቃ ብሎ የትግራይን ህዝብ በትልቁ በትንሹ ቋሚ ስራ አድርገውት ይገኛሉ " ብሏል።

ይህ ዘመቻ በፍፁም አሸናፊ ሊያደርግ አይችልም ፤ በህዝቦች መካከል ሊኖር የሚገባውንም ሰላማዊ ግንኙነት በእጅጉ የሚጎዳ ነው ሲል አሳስቧል።

" አሁንም ቢሆን መላው የትግራይ ህዝብ ሁሉም ችግሮች #በሰላማዊ_መንገድ እንዲፈቱ ያለው ቁርጠኛ አቋም እንደተጠበቀ ነው " ያለው ጊዜያዉ አስተዳደሩ " የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማፍረስ የሚቋምጡ ፅንፈኛ ሀይሎችና የቅርብም የሩቅም አጋሮቻቸው በህዝባችን ላይ የሚያደርጉትን ዘመቻ ለማክሸፍ ከፌዴራል መንግስት እስካሁን ድረስ እያደረግነው የመጣነውን አበረታች ግንኙነት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል " ሲል አቋሙን ገልጿል።

(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #USA

ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መካከል የስልክ ውይይት ተደረገ።

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ማት ሚለር እንዳሳወቁት ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ወቅትም ፤ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ ፣ የሰብአዊ ሁኔታ ቁጥጥር ተሻሽሎ ስለሚቀጥልበት አሠራር ላይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪ አንተኒ ብሊንከን፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ " አሳስቦኛል "  ሲሉ ተናግረዋል።

በሁለቱ ክልሎቹ ያሉትን ችግሮች #በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ የፖለቲካ ውይይትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነትን አጽንዖት ሰጥተውበታል።

እውነተኛ ፣ ታማኝ እና ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትሕ ሒደትን ለመፍጠር እየተከናወነ ያለውን ሥራ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመልካም እንደተቀበሉት ተጠቁሟል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ስለሚታየው የጸጥታ ተግዳሮት፣ እንዲሁም አንዲት፣ ሰላማዊት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ያላቸውን የጋራ ግብ አስመልክቶም እንደተወያዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#መልዕክት

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዜዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ፦

" . . . በዓለማችን #የሰላም ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስናከብር እግዚአብሔር በራሱና በሰው ልጆች መካከል፤ እንዲሁም በሰው ልጆች መካከል የነበረውን ጥል አስወግዶ ሰላምን ለማውረድ ያደረገውን ማሰብ ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን ምሳሌነት ለመከተል መወሰንን ይጨምራል፡፡

በተለይም በአሁኑ ጊዜ  በአገራችን የሚታዩት ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ተወግደው ሰላም እንዲሰፍንና አገራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ መላው የአገራችን ሕዝቦችና ሕዝበ ምዕመኑ እንደወትሮው የእግዚአብሔር አምላካችንን ጣልቃ ገብነት ተግተው መለመንና አቅም የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች ለሚነሱ  አዳዲስ ግጭቶችም ሆነ ለሰነበቱት አለመግባባቶች ዋነኛ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው #በሰላማዊ_መንገድ  ተቀራርቦ መመካከርና መነጋገር ብቻ እንደሆነና የትጥቅ ፍልሚያ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችል ታምናለች፡፡

የሰው ልጆች አብረው በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ የሰላም ወንጌልን ትሰብካለች፡፡ ከሰላም እጦት የተነሳ የሚፈጠረውን ሞትና እንግልት ትቃወማለች፤ በበኩልዋም ችግሮች ሲፈጠሩ ለእርቅና ለሰላም ጥረቶች የምትጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆንዋንም በየጊዜው ስትገልጽ  ቆይታለች፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱም ራስዋ በየጊዜው በተለያዩ ታጣቂ ኃይላት መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ቀጥታ ተጠቂ የሆነችባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡

ለዚህም በቅርብ ጊዜ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጸሎት ላይ በነበሩ ንጹሐን ምዕመናኖቻችን ላይ  የደረሰው የጅምላ ግድያ በማሳያነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ በጊዜው ድርጊቱን ከመቃወምና ከማውገዝ ባሻገር ሁኔታውን አስመልክቶ ክትትል እንዲደረግና ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ጥሪ ማድረግዋ የሚታወስ ነው፡፡

አያይዛም እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ላንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ የትጥቅ ፊልሚያዎችን አቁሞ ለሰላማዊ ምክክር ዕድል መስጠት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነም አስታውሳለች፡፡

አሁንም ይህንኑ ጥሪ ደግማ ደጋግማ ማሰማትዋን ትቀጥላለች፤ ምዕመናንዋንም በዚሁ መስመር በጸሎት በማትጋት ላይ ትገኛለች፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም፤ እርሱ የምህረት ፊቱን ይመልስልናል፤ ሰላሙንም በእርግጥ ይሰጠናል፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia