TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢራቅ

የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ።

በአዲሱ ሕግ ፦

➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤

➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤

➡️ " ሆን ብለው " እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የሕጉ ዓለማ ፥ " የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው " ተብሏል።

ረቂቁ መጀመሪያ ላይ ግብረሰዶማውያን #በሞት እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ መሻሻሉ ነው የተሰማው።

የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ " አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል።

#አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል ሕጉን ፤ " ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው " በማለት ሕጉን ተቃውማለች።

" ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል" ብላለች።

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጮች #ቢቢሲ እና #ሮይተርስ መሆናቸውን ይገልጸል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዟል " - የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት " ለሁለተኛ ጊዜ በጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ እንዲሆን እያደረገው " ነው ሲል ገለጸ።

የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዘዋልም ብሏል።

ማህበሩ ምን አለ ?

- በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ ይዘዋል።

- እነዚህ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸው በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው። እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

- የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ የቦንዳ ልብሶች ተሞልተዋል።

- የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር በተለያዩ መንገዶች የሚገቡ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋ እና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በ ' ኢትዮጵያ አየር መንገድ ' በኩልም በተለያዩ ሁኔታዎች ይገባሉ።

- ሀገሪቱ በአማካኝ 54 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጨርቃጨርቅ አልባሳት ያለ ክፍያ (በዜሮ ወጪ) ድንበር አቋርጠው ይገባሉ። በዚህም ኢትዮጵያ በዓመት ከታክስ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ይደርስባታል።

- በህገወጥ መንገድ የሚገቡ ልብሶች የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪውን መፈታተናቸውን ቀጥለዋል ፤ ለኪሳራ እንዲዳረጉም እያደረጉት በመሆኑ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዎችን ያቀረብን ቢሆንም ምላሽ አላገኘንም።

ምንጭ ፦ የካፒታል ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢራቅ የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ። በአዲሱ ሕግ ፦ ➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ ➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤ ➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤…
" ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " - ሞህሰን አል-ማንዳላዊ

የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ።

እንዲሁም፦

- ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

- ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ

- ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች

- ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል።

" በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

#Iraq

@tikvahethiopia
24 - ሰዓት የሚሰሩ ሁለት ቅርንጫፎች እንዳሉን ያውቃሉ?

ሕብረት ባንክ በስካይ ላይት ሆቴል ውስጥ ስካይ ላይት ንዑስ ቅርንጫፍ እንዲሁም በሒልተን ሆቴል ውስጥ ሒልተን ቅርንጫፎች ላይ የ24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በእነዚህ ቅርንጫፎቻችን ፀሀይ አትጠልቅም!

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!


ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
    ቴሌግራም- https://t.iss.one/HibretBanket
    ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
    ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#HibretBankCustomerWeek
በአዲስ አበባ ከተማ ከትላንት ለሊት አንስቶ ከበድ ያለ ዝናብ ሲጥል ነበር።

ዛሬ ንጋት ላይ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ደግሞ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከራይተናል " - ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች። የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ስደተኞች/ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን " የሩዋንዳ እቅድ " የተሰኘውን ረቂቅ…
" ... ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅዱ ገና ከአሁኑ ተጽእኖ እያሳደረብን ነው " - አይርላንድ

ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ #ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ #አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ መሆኑ ተነግሯል።

ይህን ተከትሎ የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀምሯል።

የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል።

የሀገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80% የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ መሆኑን ገልጿል።

የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች።

ለዚህም ፤ የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖች ኪራይ መፈጸሙ እና ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሰራተኞችም መሰልጠናቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#EU #Visa

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ጣለ።

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ፦

- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ፤

- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከ2 ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ ተነግሯል።

በተጨማሪ መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቆዩትን ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ ነው ተብሏል።

ገደቡ እንከመቼ እንደሚቆይ የተባለ ነገር የለም።

https://www.consilium.europa.eu/en/press/press-releases/2024/04/29/ethiopia-council-restricts-visa-provision/

@TikvahethMagazine @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል። " በሁሉም ክልሎች ያሉ…
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የ25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የቤት ዕቃዎቻችንን ገዝተው ቤትዎን ያድምቁ!

የዘመናዊነት ተምሳሌት!


አድራሻችን

1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282


👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture

👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736

👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
 
በመቐለ እና በዙሪያዋ በሚገኙ 18 አከባቢዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት (እስከ ሚያዚያ 25) የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል። 

የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጠው በጥገና ምክንያት መሆኑን ገልጿል።

አገልግሎቱ ከሚቋረጥባቸው አከባቢዎች 11 በመቐለ ፤ቀሪዎቹ 7 ደግሞ ከመቐለ ውጭ የሚገኙ መሆናቸው ተመላክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

አቶ መልካሙ ፀጋዬ በአቶ ጣሂር መሀመድ ምትክ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ተነግሯል።

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ፥" ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር የሆኑትን አቶ መልካሙ ፀጋዬ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በማድረግ ሹመዋል " ሲል አሳውቋል።

በዚህ ኃላፊነት ቦታ የነበሩት አቶ ጣሂር መሃመድ ከቦታው ተነስተዋል። ለምን በእሳቸው ምትክ ሌላ አዲስ ሰው እንደተሾመ / ከቦታው እንደተነሱ ፣ ለሌላ ሹመት እና ኃላፊነት ታጭተው እንደሆነ በግልጽ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
" የተጠየቀው የህክምና ወጪው በመንግሥት የሀኪም ደመወዝ እና በቤተሰቦቼ አቅም የሚቻል አይደለም " - ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ

ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ላጋጠመው የጤና እክል መታከሚያ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩት ጠየቀ።

ዶክተሩ 2015 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ሙያ ትምህርት ነው የተመረቀው።

ከተመረቀ በኃላም ለ6 ወራት በጠቅላላ ሀኪምነት ወገኑን ሲያገለግል ቆይቷል።

በድንገት ግን ሚዛኑን ስቶ መውደቅ እና ሌሎችም ምልክቶችን በማሳየቱ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ምርመራ ካደረገ በኋላ ' የጭንቅላት እጢ ' እንዳለበት ተነግሮታል። የናሙና ምርመራ ተደርጎ ' GradeIII Astrocytoma ' እንዳለበት ተገልጾለታል።

" ትልቅ ቦታ ደርሼ ማየት ለሚመኙት ቤተሰቦቼና ከኔ በታች ላሉት እህት ወንድሞቼ ዜናው በጣም ትልቅ ዱብዳ ነው የሆነባቸው " ያለው ዶክተር ይስሃቅ " የጥቁር አንበሳ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ ህክምና ማድረግ እንዳለብኝ ወስነዋል " ሲል ገልጿል።

ለህክምናው ወጪው እስከ 👉 2.3 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግም እንደተነገረው አስረድቷል።

ይህን ከፍተኛ ወጪ በመንግስት ሰራተኛ የሀኪም ደሞዝም ሆነ በቤተሰቦቹ አቅም የሚቻል ባለመሆኑ ሁላችሁም የቻላችሁትን እንድትረዱት ተማጽኗል።

ዶ/ር ይስሃቅ " በየሃይማኖታችሁ ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ እንዲረዳኝ በጸሎታችሁ አስቡኝ " ሲልም ጠይቋል።

ከዶክተሩ የተላከ የህክምና ማስረጃን መመልከት የቻልን ሲሆን ወላጅ እናቱን ብርሃኔ በየነን በስልክ ቁጥ ር +251911353752 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

እገዛ ለማድረግ የምትፈልጉ ፦

ዶክተር ሳምሶን ይስሃቅ በየነ
ንግድ ባንክ ፦ 1000139965691
አዋሽ ባንክ ፦ 013201172039000

ብርሃኔ በየነ ሚደቅሳ (እናት)
ንግድ ባንክ ፦ 1000549927681
አዋሽ ባንክ ፦ 01347903970500

GoFundMe👇
https://gofund.me/618fc8ee

@tikvahethiopia