TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion አቶ መልካሙ ፀጋዬ በአቶ ጣሂር መሀመድ ምትክ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ተነግሯል። የአማራ ብልፅግና ፓርቲ፥" ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር የሆኑትን አቶ መልካሙ ፀጋዬ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በማድረግ ሹመዋል " ሲል አሳውቋል። በዚህ ኃላፊነት ቦታ የነበሩት…
#Update

የአብን አባሉ አቶ ጣሂር መሐመድ " በግል ምክንያት " ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊነት መልቀቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ተናግረዋል።

" ከባለፉት ሶስት፣ አራት ወራት ወዲህ አንስቶ ከኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር በዝርዝር ንግግር አድርጌያለሁ " ያለቱ አቶ ጣሂር " የክልሉ መንግሥት ጥያቄውን ተቀብሏል " ብለዋል።

" ትንሽ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረብኝ በቤተሰብ እና በራሴ ጉዳይ ነው የለቀቅሁት ከክልሉ አመራሮች ጋር በመነጋገር ከፓርቲያችን ሰው ተክተን ነው የወጣሁት " ሲሉ ገልጸዋል።

በአቶ ጣሂር መሐመድ ምትክ ሌላኛው የፓርቲው አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ ናቸው በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አረጋ ከበደ የተሾሙት።

@tikvahethiopia
ቴሌብር ሱፐርአፕ ከአዲስ ተጨማሪ ስጦታ ጋር ቀረበልዎ!

💰የ 15 ብር ስጦታ
🌐 የ100 ሜባ ስጦታ

የሞባይል ጥቅል ሲገዙ 10% ተጨማሪ ስጦታን ጨምሮ አሁን ደግሞ የአየር ሰዓት ሲገዙ እስከ 25% ተጨማሪ ያገኛሉ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ https://onelink.to/fpgu4m አውርደው በርካታ ጉዳዮችን በአንድ መተግበሪያ ይከውኑ!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
ወዳጅ ዘመድ ለበዓል የሚልክላችሁን ገንዘብ ከ900 በላይ ቅርንጫፎች እንዲሁም 24 ሰዓት በሚሰሩት 31 የቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከላት ይቀበሉ።

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
" ነገሩ ሁሉ በጥድፊያ ነበር የሆነው #በፌስቡክ የተለቀቀውን ፎቶ እንኳን መነሳቴን አላውቅም " -  ወ/ሮ አማረች ያዕቆብ

ከወር በፊት በመንግሥት የኮሚኒኬሽን ገጾች ፣  በመንግሥት ሚዲያዎች እና ከነዚህ በወሰዱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች አንዲት ሰራተኛ " መድሃኒት ሰርቃ ልትወጣ ስልት እጅ ከፍንጅ ተይዛ በቁጥጥር ስር ዋለች " የሚል ዜና መሰራጨቱ ይታወሳል።

ይህች ግለሰብ ወ/ሮ አማረች ያዕቆብ ትባላለች።

በወላይታ ዞን ፣ አባላ አባያ ወረዳ ከምትሰራበት የህክምና ተቋም ተረኛ ሆና ለሊት አድራ ልትወጣ እየተዘጋጀች በነበረበት ወቅት መድሀኒት ጠፋ ተብሎ ሲፈለግ ቆይቶ በመጨረሻ እርሷ ትያዛለች።

" መድሃኒቱ ግን የእርሷ ባልሆነ ጋወን ውስጥ መገኘቱን " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጻለች።

ወ/ሮ አማረች ፥ " መድሀኒት ስትሰርቅ እጅ ከፍንጅ ተያዘች " ተብላ በጥድፊያ ለእስር እና ለእንግልት መዳረጓን አስረድታለች።

ይህ ሳያንስ የመንግስት ኮሚኒኬሽኖች ገጾችና የመንግስት ሚዲያዎች ዜናውን በማህበራዊ ገጾቻቸዉ ማራገባቸዉ ለከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት እንደዳረጋት ተናግራለች።

በመጨረሻ በእስር ቤት ውስጥ እያለች የደረሱላት የጠበቆች ቡድን እውነቱን አውጥተው ነጻ እንዳደረጓት ገልጻለች።

" እነሱ ባይደርሱልኝ ኖሮ ባልሰራሁት ወንጀል ወደ ወህኒ ልወርድ ነበር " ያለችው ወ/ሮ አማረች " ጉዳዩን አሁን ላይ ሳስበው ህልም መስሎ ነው የሚታየኝ " ብላለች።

በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን የሰጡት የጠበቆች ቡድን አባሉ ጠበቃና የህግ አማካሪዉ አቶ መብራቱ ኮርኪሳ ፥ " በደንበኛችን ላይ የቀረበዉ የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ #ነጻ_ተብላ_የመገመት መብቷን ከመጣስ ባለፈ ሁኔታዉን ለማጣራት ስንሞክርም ብዙ የሚያጠራጥሩ መረጃዎች ልናገኝ ችለናል " ብለዋል።

በዚህም በወላይታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተበዳዩዋን የዋስ መብት ከመጠየቅ አንስቶ " በነጻ በእስር እስክትወጣ ድረስ ታግለናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላዉ የጠበቆች ቡድን አባሉ የህግ ጠበቃ እና መምህሩ አቶ አበባየሁ ጌታ ፤ " ክሱን ያቀረበባት አቃቤ ህግ ያቀረባቸዉ ምስክሮች በሰጡት ቃል ወንጀሉን እንዳልፈጸመች ማረጋገጡን ተከትሎ ፍ/ቤቱ በነጻ አሰናብቷታል " ብለዋል።

አሁን ላይ ነጻ ብትወጣም የደረሰባት የስም ማጥፋት ከፍተኛ የስነልቦና ጫና እንዳሳደረባት ጠቁመዋል።

ከዚህ በኋላ የሚቀረዉ በሚዲያ የጠፋዉን ስሟን የመመለስና ለደረሰባት ጉዳት ካሳ የመጠየቅ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ይህም በግለሰቧ ፍላጎት የሚመሰረት ነው ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#አዲስአበባ #መታወቂያ

“ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” - CRRSA

ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት በቅርብ ጊዜ መሰጠት ይጀመራል ተብሎ ነበር።

ነገር ግን እስካሁን አገልግሎቱ አልጀመረም።

ነዋሪዎችም መቼ እንደሚጀምር ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቼ ነው አገልግሎቱ መስጠት የሚጀምረው ? ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ አለማየሁን ጠይቋል።

እሳቸውም በሰጡት ምላሽ፣ “ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” ብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዝርዝር ምን አሉ ?

➡️ ከመሸኛ ጋር ተያይዞ ፣ ከክፍለ አገር ለሚመጡ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎቱ #ዝግ አይደለም።

- በሕመም፣
- በትምህርት እድል፣
- ተጋቢዎች ሆነው ከሌላ ቦታ ሲመጡ እዚህ (አ/አ) አንዱ ተጋቢ ካለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ከሆነ፣
- በሥራ ዝውውር ከሆነ እነዚህ ሁሉ አልተከለከሉም። የተፈቀዱ አገልግሎቶች ናቸው።

➡️ የተከለከለው፣ ያለ ምክንያት ዝም ብሎ ለሚመጣ ነዋሪ ነው። ያለ ምክንያት ስንል በእርግጥ በምክንያት የሚመጣ አለ። ግን አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ ነዋሪ አገልግሎት ቁጥጥር ለማበጀት የተደረገ ነው።
 
ኃላፊው በሰጡት ቃል ፥ " መሸኛ አስገብተው መረጃዎችን እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቀናል " ብለዋል።

በጣም ባጠረ ጊዜ እንደሚጀመር አመልክተዋል።

" የገጠመን አንዱ ትልቅ ፈተና የነበረው (ለ15 ቀናት አካባቢ) አዲስ መዝጋቢ መመዝገብ ከባድ ሆኖብን ነበር፣ ቴክኒካል ችግር ተከስቶ። እሱን ፈትተናል " ያሉት አቶ ዮናስ " በዚህ ምክንያት አዲስ ተመዝጋቢ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የነበሩ ተገልጋዮች ቁጥራቸው ከፍ (አገልግሉቱን በመቋረጡ) ስላለ እሱን ማቅለል ስላለብን ነው። እሱን እንዳቀለልን እንጀምራለን " ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት…
#AddisAbaba

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይን) ከሚሰጥባቸው ከተሞች አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎ የፈተና ቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፤ " የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማው በኦንላይን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው " ብለዋል።

ለፈተናው ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፖችና ታብሌቶችን ጨምሮ ሌሎች ግብአቶችን የማሟላት ስራ ተጀምሯል ተብሏል።

የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከወዲሁ እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

ሙሉ በሙሉ ፈተናው በኦንላይን ባይሰጥም  በተመረጡ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቀሩት ተማሪዎች በተለመደው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በወረቀት ይፈተናሉ።

እስካሁን በየትኞቹ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን ይወስዳሉ የሚለው አይታወቅም። በምን አግባብ ተማሪዎቹ እንደሚመረጡም ለጊዜው በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የ25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የቤት ዕቃዎቻችንን ገዝተው ቤትዎን ያድምቁ!

የዘመናዊነት ተምሳሌት!


አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282

👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EU #Visa #ETHIOPIA

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታውቃለች።

የአውሮፓ ህብረት ይህንን አቋሙን እንዲያጤነው ጠይቃለች።

ብራስልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ምን አለ ?

- የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ያስተላለፈው የእግድ ውሳኔ በህብረቱ አባል አገራት ለመኖር ህጋዊ ፍቃድ የተነፈጋቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በክብር፣ በስርዓት እና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ እንዲመለሱ ለማድረግ ሁለቱ ወገኖች በቅርበት እየሰሩ ባለበት ወቅት ነው።

- ውሳኔው ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስና ከማህበረሰቡ ጋር መልሶ ለማዋሃድ በኢትዮጵያ እና በህብረቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር ያላገናዘበ ነው።

- ውሳኔው ማንነትን ለማረጋጋጥ የሚደረገውን አድካሚ ሂደት ከግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም።

- ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከህብረቱ አባላት አገራት ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን የቅበላ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ላይ እንቅፋት የሚፈጥር ነው።

የአውሮፓ ኅብረት ም/ ቤት ከሰሞኑ በኅብረቱ ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህ ዕገዳ መሠረት ፦

➡️ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም፤

➡️ ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉም፤

➡️ የዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ሀገራት ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ ተላልፏል።

የእገዳ ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግስት በአውሮፓ ያሉ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩትን ዜጎቹን ለመመለስ / ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ በመሆኑ የተላለፈ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

የመረጃ ምንጮች ቢቢሲ/ በቤልጂየም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የአውሮፓ ኮሚሽን ድረገጽ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ ላይት " ጥያቄ ቀረበበት። አዲሱ መተግበሪያው ' ቲክቶክ ላይት ' በፈረንሳይ እና ስፔይን አገልግሎት የጀመረው ቲክቶክ በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ያለውን ግምገማ በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲያቀርብ ዛሬ የአውሮፓ ኮሚሽን ጠየቀ። ከዋናው ቲክቶክ መተግበሪያ አነስ ብሎ የወጣው የቲክቶክ መተገበሪያ ተጠቃሚዎች #ተከፍሏቸው የቪዲዮ ምስሎችን እንዲመለከቱ…
#TikTok #EU

" የቲክቶክን አደጋ በትክክል እናውቃለን " - ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን

' ቲክቶክ ' አውሮፓ ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተሰማ።

ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ' ቶክቶክ ' በመላ ሀገሪቱ እንዲታገድ አልያም ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ ሕግ ማውጣቷ ይታወቃል። ለዚህም የሰጠችው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

አሁን ደግሞ መተግበሪያው የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተነግሯል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ለኮሚሽኑ የ2024 ምርጫ በተደረገ አንድ ክርክር ላይ ' ቲክቶክ ' በአውሮፓ ሀገራት የመታገድ ዕጣፋንታው ዝግ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ይህን ያሉት የአሜሪካ ' ቲክቶክ ' ን የማገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሷን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው።

ቮን ደር ሌየን ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም በተቋሙ ስልኮች ላይ መተግበሪያው እንዳይሰራ ያደረገ የመጀመሪያ ተቋም መሆኑን አስታውሰዋል።

" የቲክቶክን አደጋ በትክክል ምንእንደሆነ እናውቃለን " ሲሉ አክለዋል።

ምንም እንኳን የአውሮፓ ኮሚሽን አውሮፓ ሀገራት ውስጥ ' ቲክቶክ ' ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ቢሰጥም ልክ እንደ አሜሪካ በፍጥነት ተመሳሳይ መንገድ ይከተል እንደሆነ ለመደምደም ገና ነው ተብሏል።

የአውሮፓ ኮሚሽን በቅርቡ ከዋናው ቲክቶክ አነስ ብሎ የተዘጋጀው ' ቲክቶክ ላይት (ተጠቃሚዎች ተከፍሏቸው ቪድዮ የሚያዩበት) ' በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ጥያቄ ማንሳቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia