TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና📌ቦሌ መንገድ በሚገኘው የፓርላማ አባላት መኖሪያ አፓርታማ አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ #የተኩስ ልውውጥ የነበረ ሲሆን፣ የቦሌ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱና የሰው #ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመታሰቢያ መርሃ ግብር ...

እሁድ ሚያዚያ 1 በቆቦ አካባቢ በተከሰተው ግጭት በሥራ ላይ ህይወታቸውን ላጡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሁለት የሥራ ባልደረቦች የመታሰቢያ መርሃግብር ተካሄደ።

በግጭቱ ህይወታቸው ያለፉት አቶ ቾውል ቶንጎይክ እና አቶ አማረ ክንደያ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙበት ወቅት በመከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ክልል ልዩ ኃይል መካከል በነበረ #የተኩስ_ልውውጥ ተመተው ህይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስታውሳለች።

አደጋው በተፈጠረበት ወቅት ቆቦ የሚገኙ የካፑቺን አባቶች በቦታው በመድረስ የሟቾቹን አስከሬን ወደቤታቸው በመውሰድ እና በማዘጋጀት ወደቤተሰቦቻቸው እንዲላክ ማድረጋቸውን ከቤተክርስቲያኗ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ሚያዝያ 1 ቀን /2015 ዓ/ም ባስተላለፉት መልዕክት " ይህ ግጭት፣ ሰቆቃ፣ ስደት እና የእርስ በእርስ ጦርነት ሊቆም ይገባል። ችግሮችንም ሰከን ባለ መልኩ በውይይት ብቻ ልንፈታ ይገባል። ባለፉትም የነበሩትን ግጭቶች እና ጦርነቶች የፈታናቸው በውይይት ነው " ብለዋል። 

ብፁዕ ካርዲናል ለሟች ቤተሰቦች ሁሉ መጽናናትን እንዲሰጣቸው ተመኝተው ለሞቱት ነፍሳቸውን በአብርሃም በይሳቅ በያዕቆብ አጠገብ እንዲያኖር ጸሎታቸውን አቅርበዋል።

ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የካቶሊክ ተራዕዶ ድርጅት አቶ ቾውል እና አቶ አማረ  የመታሰቢያ መርሃግብር አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ያካሄደ ሲሆን በዕለቱም የሟቾቹ ቤተሰቦች በተገኙበት የመታሰቢያ ጸሎት በብጹዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን መሪነት ተካሂዷል።

በተጨማሪም ድርጅት ከ4 አመት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መከስከት ምክንያት ህይወታቸውን ያጡትን አራቱን ሠራተኞቹን በማስታወስ ጸሎት ተደርጓል።

ምንጭ፦ የአትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን

@tikvahethiopia