TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update 10ኛ ክፍል⬇️

በ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት እስከ #አርብ ድረስ ይፋ እንደሚሆን የሀገር ዓቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

የተማሪዎችን እርማት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ መረጃውን በአጭር ጽሁፍ እና በድረ-ገጽ በጥራት ለማሰራጨት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው እስካሁን ውጤት በየትኛውም የውጤት ማሳወቂያ ዘዴ እንዳላወጣና ተማሪዎች በኤጀንሲው ስም በሚወጡ #የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳይታለሉም አቶ አርአያ አሳስበዋል፡፡

ውጤቱን ይፋ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውንና እስከ መጪው አርብ ድረስ ውጤቱ እንደተለመደው በኤጀንሲው ድረ-ገፅና በአጭር የፅሁፍ መልእክት ይፋ ይደረጋል፡፡

ተማሪዎች የለፉበት ውጤት እንዳይሳሳት በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሪክተሩ የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤትን ተማሪዎች #በትእግስት እንዲጠባበቁም ጠይቀዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ ከነገ በስትያ አርብ #አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ ቀደም ሲል ተነግሮ ነበር፡፡ ይሁንና ስብሰባው ወደ ቀጣዩ ሰኞ መዛወሩን የጨፌ ኦሮሚያ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ደምሴ ዛሬ ለሸገር FM 102.1 ተናግረዋል፡፡ ስብሰባው የተላለፈው ከ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ በኋላ እንዲካሄድ ታስቦ ነው ብለዋል፡፡ አስቸኳይ ስብሰባው በተለየ ምክንያት ^ካልተራዘመ በስተቀር ለአንድ ቀን እንደሚካሄድ አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡ #በአዳማ በሚገኘው ጨፌ አዳራሽ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ አባላት ከመስከረም 25 ከሰዓት አንስቶ ከተማዋ #እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል፡፡ የሶስተኛውን አስቸኳይ ስብሰባ አጀንዳዎች በተመለከተ የፊታችን #አርብ መግለጫ እንደሚሰጥ አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡

📌ሸገር FM 102.1 ሌሎች ምንጮች ግን በአስቸኳይ ስብሰባው ሹመቶች ይኖራሉ ብለውኛል ሲል ዘግቧል።

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ #ባምላክ_ተሰማ የ2018 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልሱን የዋንጫ ጨዋታ የፊታችን #አርብ በቱኒዚያው ኤስፔራንስ እና በግብፁ አል ሃህሊ መካከል ቱኒዝ ላይ የሚደረገው ከባዱን ፍልሚያ በመሀል ዳኝነት እንዲመሩት ካፍ ወስኗል። አርቢተር ባምላክ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ VAR -ቪዲዮ ህግ ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አርቢትር ይሆናሉ።

ምንጭ፦ ethio kickoff
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አርብ_ምንጭ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተሳተፉ ነው። በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ200 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዝግጅቱ ተጠናቆ ዜጎች በየአቅራቢያቸው የዛፍ ችግኞችን በመትከል ላይ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተሳትፈዋል፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ በመላ አገሪቱ እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አርብ_ምንጭ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተሳተፉ ነው። በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ200 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዝግጅቱ ተጠናቆ ዜጎች በየአቅራቢያቸው የዛፍ ችግኞችን በመትከል ላይ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተሳትፈዋል፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ በመላ አገሪቱ እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የነዳጅ እጥረት ለስራችን እንቅፋት እየሆነ ነው " -የባጃጅ አሽከርካሪዎች በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጓጎለ መሆኑን አመልክተዋል። ለአብነት ከቡሌሆራ፣ ሀዋሳ፣ ወልቂጤ፣ አሶሳ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ ፣ አሳስ፣ አዶላወዮ፣ ሻኪሶ፣ አሳሳ ከሚገኙ አሽከርካሪዎች የመጡ መልዕክቶች ነዳጅ ለማግኘት አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ…
" የቤኒዚን አቅርቦት ችግርን በጥቂት ቀናት ለመፍታት እየተሰራ ነው " - የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን

በአዲስ አበባ የተፈጠረውን የቤንዚን አቅርቦት ችግር በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።

የኢትየጵያ ነዳጅ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለችግሩ መከሰት የተለያዩ ምክንያቶችን አንስቷል ፦

1ኛ. የዩክሬን – ሩስያ ጦርነትን ተከትሎ የተፈጠረውን ዓለማቀፋዊ ችግር ፤

2ኛ. የጅቡቲ መንገድ መበላሸቱና ከጅቡቲ አዲስ አበባ ከ2 ቀን እስከ 2 ቀን ተኩል ይወስድ የነበረው መንገድ አሁን 4 ቀን ድረስ በመውሰዱ መዘግየት መፈጠሩ ነው።

የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን ከሎጂስቲክስና ከዓለማቀፋዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አሳውቋል።

ከባለፈው አርብ ጀምሮ 6 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን ከጅቡቲ በመጓጓዝ ላይ ነው ያለው ባለስልጣኑ እስከመጭው #አርብ ድረድ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ይፈታል ብሏል።

በጊዜያዊነት ችግሩን ለመቅረፍ ከመንግስት ቋት ቤንዚን እየቀረበ ነው ሲልም አሳውቋል።

ችግሩ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሌሎች ከተሞችም እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ቀጥሎ ለሁሉም ከተሞች መፍትሄ ይሰጣል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሀዋሳ ፣ ቡሌሆራ ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ አሶሳ ... በሌሎችም በርካታ ከተሞች የነዳጅ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ተፅእኖ እሳያደረ መሆኑን በተለይም ነዳጅ ለማግኘት ከለሊት ጀምሮ ተሰልፎ መጠበቅ ግድ እንደሚል መጠቆሙ ይታወሳል።

ሁኔታ በርካቶችን ከስራ እዲስተጓጎሉና ቀናቸውን ነዳጅ ለመቅዳት በመሰለፍ እንዲያሳልፉ እያደረጋቸው መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው አርብ ሀዋሳ ከተማ ላይ ተፈፅሟል ስለተባለ አንድ የወንጀል ድርጊት ጥቆማ ደርሶት ተመልክቷል። ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞበታል የተባለውን ክ/ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን አነጋግሯል። 👉 ተጎጂ የራስሰው ገዛኸኝ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፦ " ሀዋሳ ላይ ቀን ነው በሚባልበት 12:30 የምናሽከረክረውን ' ላንድሮቨር…
#Hawassa

የራስሰው ገዛኸኝ የተባሉ ግለሰብ ሀዋሳ ላይ የተደራጀ ዝርፊያ እና ሳንጃ በማውጣት የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈው አሰራጭተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህ መልዕክት በውስጥ ደርሶት ተመልክቷል። የሀዋሳ ፖሊስንም ስለጉዳዩ ደውሎ ጠይቋል።

" በሀዋሳ ከተማ ላይ የተደራጀ የዝርፊያ እና የግድያ ሙከራ ተፈፅሞብናል " ያሉት የራሰው ገዛኸኝ ፅፈው ባሰራጩት ፅሁፍ መሰረት ፦

- ድርጊቱ የተፈፀመው ሀዋሳ፣ በተለምዶ ከአቶቴ ወደ ፉራ በሚወስደው መንገድ " ቦሌ መንደር " አካባቢ በሚገኘው የትራፊክ መብራት ጋር ነው።

- ቀኑ 12/04/2016 ዕለተ #አርብ ከምሽቱ 12:30 ላይ ነው።

- ሲያሽከረክሩት የነበረው ላንድ ሮቨር መኪና ሲሆን ውስጥ እንግዶቻቸው ከሆኑ 3 የመንግስት አካላት ጋር ሆነው ሲጓዙ ነበር።

- በተለምዶ " ቦሌ መንገደር  " የትራፊክ መብራቱ ጋር ሲደርሱ የሚያሽከረክሩት መኪና ከጎን በኩል በከፍተኛ ምት ይመታባቸዋል። አደጋ ያደረሱ ስለመሰላቸው መኪናውን ዳር በማስያዝ ያቆማሉ።

- በመኪናው ውስጥ ከነበሩት አንዱ ከመኪና ፈጥነው በመውረድ የተመታውን መኪና ዙሪያውን ቢመለከቱም የደረሰ አደጋ የለም። ግን ሰዎች ተሰብስበዋል።

- የወረደው ሰው ከመኪናው ኃላ የተሰበሰቡ ወጣቶች የደረሰውን ግጭት ምንነት እየጠየቃቸው በነበረበት ወቅት የራስሰው ገዛኸኝም ከመኪናቸው ወርደው ወደ ወጣቶቹ በመሄድ ምን ተፈጠረ ? ማለት ጥያቄ ይጀምራሉ።

- በዚህ ሁኔታ አስፓልቱ ዳር ከሚገኝ 2 ፑል ቤት አንድ ግሮሰሪ ተጨማሪ ወጣቶች ወጥተው ከበባ ያደርጋሉ፤ ወዲያው አንድ ወጣት በተለምዶ በአከባቢው አጠራር " ባንጋ " የተባለ የሚጠራውን ሳንጃ ይዞ ማሳደድ ይጀምራል።

- በተፈጠረው ሁኔታው #ተደናገጠው ቢያፈገፍጉም ወጣቱ ሊተዋቸው ባለመቻሉ ወደ መኪናው ለመግባት ሲሞክሩ እዛው ጋር የነበሩት ሌሎች ወጣቶች በሩን እንዳይገቡ ይይዙታል።

- ሁኔታው በተደራጀ መልኩ #ዘረፋ መሆኑ ስለገባቸው በሳንጃው ላለመወጋት ይሸሻሉ።

- በዚህ መካከል ከመኪና ውስጥ ያልወረዱት ሰዎች መኪናውን ሎክ ለማድረግ ቢሞክሩም ሌሎች ወጣቶች ከኃላ በር በመክፈት፦
* ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣ
* ከአንድ ፕሮግራም ቀረፃ እየተመለሱ በመሆኑ ብላክ ማጂክ ካሜራ ፣
* መቅረፀ ድምፅ የያዘ ቦርሳ ይዘው ተሰውረዋል።

- አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ዘራፊዎቹ ከአከባቢው መሰወራቸውን ተመልክተው " ስፍራውን ቶሎ ለቃችሁ ካልሄዳችሁ አሁን ከመጡ #ይገሏችኋል " በማለት አከባቢውን ለቀው እንዲሸሹ ያስፈራሯቸዋል።

- በተጠና ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የዘረፋ ኦፕሬሽን በመሆኑ ከአከባቢው ለመሄድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው የፓሊስ አካል እስኪመጣ ጠበቁ።

- በዚህ መካከል አንድ የፓሊስ አባል ይመጣል። ቀርቦ ምንድነው ? ሲል ይጠይቃል። እነሱም የደረሰባቸውን የዘረፋ ወንጀልና የግድያ ሙከራ አስረድተው የህግ ከለላ ቢጠይቁም። ፓሊሱ " በቃ አሁን ከዚህ ሂዱ ልጆቹ ከላልታወቁ ምን ማድረግ ይቻላል ? " በማለት መልሷል።

- የፖሊስ አባሉ ቢያንስ እንኳን #ፓትሮል ደውሎ ኃይል እንዲያስጨምርላቸው ቢነግሩትም ፤ " እኔ የናንተ ጠባቂም ተላላኪም አይደለሁም " የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸዋል።

- ወደ አንድ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ዘንድ ደውለውም እንዲደርሱላቸው ፤  የደረሰባቸውን በደል ቢያስረዱም ከባለስልጣኑ ዘንድ ምንም አይነት እርዳታ አላገኙም።

- ወደ ተለያዩ የህግ አካላት በመደወል #ከ40_ደቂቃ በኃላ አንድ የፓሊስ ፓትሮል ሊመጣ ችሏል።

- የመጡት የፖሊስ አባላት ችግሩን ለመስማት የሞከሩ ሲሆን " የዘራፊዎችን ማንነት እና ስም " ከተፈራፊዎች ይጠይቃሉ። እነሱም መንገደኛ በመሆናቸው ገልጸው የዘራፊዎቹን ማንነት በስምና በአድራሻ ለይቶ ለፓሊስ መናገር የሚችሉበት መንገድ ስላልገባቸው ቢያንስ የተወሱ ወጣቶች የወጡበትን ግሮሰሪ እና ፑል ቤት አሳዩ።

- ከፍተኛ #ክርክር እና አለመግባባት ከተፈጠረ በኃላ የፖሊስ አባላቱ የተፈፀመውን ነገር የዕለት መዝገብ ላይ እንዲያስመዘግቡ በማለት ወደ ታቦር ክፍለ ከተማ ፓሊስ ማዘዣ ጣቢያ እንዲሄዱ አድርገዋል።

- ፖሊስ " የፑል ቤቱ ባለቤቶች  " አንዳንድ ነገር ሲናገሩ በመስማታቸው አስረዋቸዋል። ነገር ግን ዋናዎቹ የተደራጁትን የዘራፊ ቡድኖች የያዘም ሆነ በወቅቱ ለመከታተል የሞከረ አካል የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መልዕክት ከተመለከተ በኃላ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ፤ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ አሁን ላይ በከተማዋ ዉስጥ በተሰሩ በርካታ ስራዎች በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች በጅጉ የተሻለ ሰላም ያላት ከተማ ሀዋሳ መሆኗን ጠቅሰዋል።

ተፈፅሟል የተባለውን ጉዳይ በሶሻል ሚዲያ ሲያዩት #ማዘናቸዉን ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፤ ችግር ተፈጥሮ ከሆነ በተዋረድ ለሚመለከተዉ አካል ማቅረብ እንደሚቻልና በተለይ እንዲህ ያለዉን ጉዳይ እንኳን ፖሊስ የትኛዉም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ከማስቆም ወደኋላ እንደማይል ገለጸዋል።

አሁንም " ችግሩ ተፈጽሞብን ፍትህ አጣን " የሚሉ አካላት በየትኛዉም ጊዜ ማመልከት ቢፈልጉ ቢሯቸዉም ሆነ ስልካቸዉ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ብዙዎች ሰላሟን የሚመሰክሩላትን ሀዋሳ ከተማን በትንሹ መገመት አግባብ አይደለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተጎጅዎች እንዲያመለክቱና ቃላቸውን እንዲሰጡ የተደረጉበትን የታቦር ክ/ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ወንድዬ ከበደን አነጋግሯል።

እሳቸው በሰጡት ምላሽ በወቅቱ መኪናችን ተመታብን ያሉት አካላት ወደፖሊስ ጣቢያዉ በመምጣት ባስመዘገቡት መሰረት በአካባቢዉ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ተይዘዉ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢ/ር ወንድዬ ፤ የተጠቀሱት ንብረቶች መሰረቃቸዉን በወቅቱ አለመስማታቸውን እና አለመመዝገባቸዉን አስታውሰዉ አሁንም ቢሆን ጉዳዩን በአግባቡ ወደሚመለከተዉ የህግ አካል በማቅረብ በተያዘዉ ምርመራ እንዲካተት ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

ተጎጅዎች " በተደራጀ ዝርፊያ ጥቃት ተፈጽሞብናል " የሚሉት የተሳሳተ መሆኑን የሚያነሱት ኢንስፔክተሩ በወቅቱ ' ግጭት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ' ውስጥ በመግባታቸዉ ለስርቆት ተዳርገዉ ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጅ በከተማዉ የተባለዉ አይነት ዝርፊያ በፖሊስና በማህበረሰቡ ትብብር #ታሪክ_የሆነ ጉዳይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ከዓመታዊው #የቁልቢ_ገብርኤል የንግስ በዓል ጋር በተያያዘ #ከጨለንቆ እስከ #ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ እንዳያልፍ ክልከላ ተጥሏል።

ክልከላው እስከ ታህሳስ 19 (#አርብ) ከሰዓት ድረስ የሚዘልቅ ነው።

@tikvahethiopia
#አስቸኳይ

“ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት

በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ” በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የታጋቹ እናት ወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ በሰጡት ቃል፣ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እባካችሁ ልጄን ታደጉኝ ” ሲሉ እያለቀሱ ጠይቀዋል።

“ በሄደ በ17 ቀኑ ከሊቢያ ስልክ በጓደኛው አማካኝነት ተደወለልኝ። ስልኩን ሳነሳ ‘ሊቢያ ላይ ተይዟልና 950 ሺሕ ብር ተጠይቋል’ ብሎ ጓደኛው ነገረኝ ” ያሉት የታጋቹ እናት፣ “ ከዚያ ወዲያውኑ ደግሞ ሊቢያዎቹ እየገረፉት ምስል ላኩልኝ። አካውንትም ላኩልኝ ‘ገንዘብ ላኪ’ ብለው ” ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም፣ “ እንደገና ለ3ኛ ጊዜ መደኃኒት ሰጥተውት እንደ እብድ እያደረገው ቪዲዮ ላኩልኝ። እንደገና ለ4ኛ ጊዜ ደግሞ ወደ ታች #ዘቅዝቀው #እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ከዚያ ‘ተሽጧል 1.7 ሚሊዮን ብር አምጭ’ ብለው ደወሉ። ቪዲዮ እያሳዩም ‘1.7 ሚሊዮን ብር ታመጫለሽ አታመጭም?’ አሉኝ ” ብለዋል።

በዚህም “ እኔ የለኝም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉልበቴ ስለሆነ ለምኘ፣ እርዳታ አሰባስቤም እከፍላለሁ አልኳቸው። ለ5ኛ ጊዜ እንደገና #ፀጉሩን ላጭተው የሆነ #ውሻ አስመስለው ምስል ላኩልኝ። ከዚያ በኋላ በቃ ‘የጨመረሻ ቀን ብለው’ ደወሉ። ልጄም በጣም #እያለቀሰ ‘አስለቅቂኝ’ አለኝ። እነርሱም ‘ነገ #አርብ 1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን በፊት ለፊትሽ ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን ” አሉኝ ሲሉ አንብተዋል።

አጋቾቹ ‘ብር ላኪ’ ሲሏቸው ባለማወቅ የመፍትሄ መንገድ መስሏቸው የላኩትን አካውንት በሕግ እንዳሳገዱ፣ በዚህም አጋቾቹ የወጣቱን ስቃይ እንዳበዙት፣ ከታገተ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው፣ ገንዘቡ እስኪሟላ ተጨማሪ ቀን መጠየቃቸውን የገለጹት እናት፤ “ ፌደራልም ሊቢያና ሱዳን ድንበር ላይ የሊቢያ መግቢያ ላይ ነው የታገተው ብለው ነገሩኝ ” ብለዋል።

ወ/ሮ ገነት፣ ምርመራውን ይዞታል የተባሉ የፌደራል ፓሊስ አባል የአጋቹን አካል ቢደርሱበትም በሕግ በኩልም መፍትሄ እንዳላገኙ አስረድተዋል።

ያላቸው አሁናዊ የምርመራ ሂደትን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው መርማሪው የፌደራል ፓሊስ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ “ መልስ መሰጠት የሚችለው እንደ ተቋም ስለሆነ በተቋሙ በኩል ኦፊሻል ደብዳቤ ይዘው በአካል መጥተው አመራሮችን ማነጋገር ይችላሉ ” ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ሆኖም ስለጉዳዩ በደብዳቤ ጠይቀን ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

እናት አጋቾቹ ከጠየቁት ውስጥ እስካሁን የተሰበሰበው ወደ 350 ሺሕ ብር ብቻ እንደሆነ አስረድተው “ ሀዘን ላይ ነኝ። በቅርቡ ልጄ ሞቶብኛል። አሁን ደግሞ ይሄ ደረሰልኝ ብዬ፣ አሁን እንደዚህ ሆነብኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ረድቶኝ ልጄን እንዲያስለቅቅልኝ በትህትና እጠይቃለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000523577402 ሲሆን ሌሎችም የሂሳብ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል።

በስልክ ልታገኟቸው የምትፈልጉ 0916848184፣ 0911720985 ደውሉላቸው።

@tikvahethiopia