TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቴዎድሮስ በእስር ላይ ይገኛል‼️

#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ቴዎድሮስ አዲሱ ከሀምሌ 28-30 ቀን 2010ዓ.ም በጀጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ስላላጠናቀቀ እና በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ #ፍትሃዊ አለመሆኑንና የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን በማመን መዝገቡ እንዲዘጋ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በ80 ሺህ ብር ዋስ #እንዲወጣ ፈቅዶ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ግለሰቡ በሌላ ወንጀል ከቀድሞው የሱማሌ ክልል ምክትል የትምህርት ቢሮ ኃላፊና ከኒያላ ኢንሹራንስ የጅጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር #በተጭበረበረ የኢንሹራንስ ዋስትና አፈጻጸም የቅድመ ክፍያ ቦንድ ከኢንሹራንስ እንዲጻፍ በማድረግ በውሉ ላይ ከተጠቀሰው ቅድመ ከፍያ ላይ ብር 15,306,303.3 ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ወጪ በማድረግ የወሰደ በመሆኑ ለትምህርት ቤቱ መፀሐፍቱን ሳያቀርብ ገንዘቡን ከጥቅም ተጋሪዎች ጋር በመከፋፈል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በቴዎድሮስ አዲሱ ላይ #በከባድ የሙስና ወንጀል የጀመረውን ምርመራው ለማከናወን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት ተጠርጣሪው በእስር ቤት እንዲቆይ እና ለየካቲት 5 ቀን 2011 እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...በመጠለያው ውስጥ የሚገኙት ወገኖች እንኳን ለራሳቸው ለሌላው የሚተርፉ አርሶ አድሮች ነበሩ " - አቶ መላኩ አለበል

ዛሬ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ እና አካባቢው ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች በቦታው በመገኘት ድጋፍ አደረጉ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በቻግኒ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ ለሆኑ ተፈናቃዮች የሚውል 2800 ኩንታል ስንዴ አስረክበዋል።

አቶ መለኩ አለበል ፥ "በመጠለያው ውስጥ የሚገኙት ወገኖች እንኳን ለራሳቸው ለሌላው የሚተርፉ የነበሩ አርሶ አድሮች ናቸው፤ ነገር ግን የነሱ ባልሆነ ጅንዳ የተለያየ ፍላጎት ባላቸው ሃይሎች የተሳሳተ ስሌት ለችግር ተጋልጠዋል" ብለዋል።

መንግስት ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው ለመመለስ የተጠናከረ ሥራ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በመጠለያው ውስጥ ለሚገኙት ዜጎች ከተለያዩ ወገኖች የሚመጣውን ርዳታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት #ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በፍጥነት እንዲያከፋፍሉ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

አቶ መላኩ አለበል በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ተዟዙረው ተመልክተዋል፤ አሉብን ያሏቸውን ችግሮችም ጠይቀው መረዳታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በድረገፁ አስነብባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ምሽት ለግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ስልክ ደውለው ነበር። ስልክ የደወሉላቸው አል ሲሲ ድጋሚ የግብድ ፕሬዜዳንት ሆነው በመመረጣቸው " እንኳን ደስ አልዎት " ለማለት ነው ተብሏል። በዚህ የስልክ ውይይታቸው ፤ " በቀጠናው ያሉ የጋራ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ጥረቶችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ…
ℹ️ ግብፅ በፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ቃል አቀባይ በኩል ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጻለች።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሞሀሙድ ፤ ትላንት ምሽት ወደ አል ሲሲ ስልክ ደውለው #ከሁለት_ሳምንት በፊት ላሸነፉት ምርጫ " እንኳን ደስ አልዎት " ብለዋል።

የስልክ ውይይቱን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ ሁለቱ መሪዎች ፦
- የሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን፤
- ታሪካዊ ግንኙነታቸውን መሰረት በማድረግ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጎልበት መወያየታቸውን ገልጸዋል።

አል ሲሲ ፤ ግብፅ ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት መግለፃቸው ተነግሯል።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከአል ሲሲ በተጨማሪ ለኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ስልክ ደውለው ነበር።

ከኳታሩ ኤሚር ጋር ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጥቅሞችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተሰምቷል።

ትላንት ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የቀጠናውን ጉዳይ የሚከታተሉ ምሁር ፤ የግብፅ እና ሶማሊያ የስልክ ውይይት ምንም ይሁን ምን የኢትዮጵያ #ፍትሃዊ የሆነውን የባህር በር ጥያቄ ማንሳትን እንደ ክፉ ነገር ፣ ጎረቤቶችን ለመጉዳት አድርገው የሚያዩ ኃይሎች ስላሉ ሁሉንም ነገር በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ በአይነ ቁራኛ መከታተል ይገባል ሲሉ አሳስበው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መቐለ

" ዲግሪ ለመያዝ 8 ዓመታትን መማር #ፍትሃዊ አይደለም " - ተማሪዎች

ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ በኃይል እንዲበተኑ ተደርገዋል።

ተማሪዎቹ ምንድነው ጥያቄያቸው ?

" አንድ ዲግሪ ለመያዝ 8 (#ስምንት) ዓመታትን መማር  #ፍትሃዊ አይደለም " ያሉት ተማሪዎቹ " ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የምንለይበት ምክንያት የለም ፤ የመውጫ ፈተና መፈተን አለብን " ብለዋል።

" ተመርቀን ወጥተን ስራ መስራት ፤ ህይወትን ማሸነፍ ባለብን በዚህ እድሜያችን የመጀመሪያ ዲግሪ ለማግኘት 8 ዓመታት መጠበቅ የለብንም ፣ የወጣትነት እድሜያችን ያሳስበናል ፤ ብንጮህ ብንጮህ ሰሚ አላገኘንም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በዚህ ዓመት መመረቅ ሲገባን ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ትማራላችሁ እያሉን ነው ይሄ በፍፁም የማንቀበለው ነው " ብለዋል።

ዛሬ ተማሪዎቹ ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በመነሳት የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ ወደ ከተማ ለማምራት ሲሞክሩ በፓሊስ እንግልትና ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።

የትራፊክ ፖሊስ አባላት ሰልፉን ለማደናቀፍ መንገድ ሲዘጉ ፤ ታጣቂዎች ሰልፈኛ ተማሪዎች ሲደበድቡ ታይተዋል።

ጥያቄ  ካነሱ ሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል ሶስት ሴት ተማሪዎች በፓሊስ #ሲደበደቡ መመልከቱን ህሉፍ በርሀ የተባለ የአይን እማኝ ገልጿል።

ከዛሬው ሰልፍ ጋር በተያያዘም አንድ የፖሊስ አባል አንዲት #ሴትን እያንገላታ #ገፍትሮ መሬት ላይ ሲጥላት የሚያሳይ ቪድዮ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ስልፍ በማስመልከት የዩቨርስቲው አስተዳደር እና የትምህርት ሚንስቴር እንዲሁም የከተማው ፖሊስ እስከ አሁን ያሉት ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተቋማቱ የሚሉት ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia