TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" 38 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸው አልፏል " - በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ #የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸውን እንዳጡ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል። ትላንትና ሰኞ በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ " #ጎዶሪያ " በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስልሳ (60) ኢትዮጵያውያን…
" የ5 ሕፃናት እና ሴቶችን ሕይወት ጨምሮ 16 ዜጎቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል " - በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

በጀልባ መገልበጥ አደጋ #የ16_ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሲጠፋ አብረው የተሳፈሩ 28 ዜጎችን እስካሁን ማግኘት አልተቻለም።

ትላንት ምሽቱን ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ " አራ " ከሚባል ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ " ጎዶሪያ " በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ እስካሁን ድረስ የ5 ሕፃናት እና ሴቶችን ሕይወት ጨምሮ 16 ዜጎቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል።

እስካሁን አብረው ተሳፍረው የነበሩት ውስጥ 28 ፍልሰተኞችን ማግኘት እንዳልተቻለ እና 1 ሴትን ጨምሮ 33 ፍልሰተኞች በሕይወት ተርፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው።

ከ2 ሳምንት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በደረሰ አደጋ የ38 ፍልሰተኛ ዜጎች ሕይወት አልፎ ነበር።

ከጅቡቲ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው የዜጎችን ሕይወት እያሳጣ እንደሆነ በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

በዚህም ዜጎች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለከፋ አደጋ እየዳረጉ ይገኛሉ ብሏል።

ዜጎች #በህገወጥ_ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ እና የፍትህ አካላትም ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ከገጠራማ የአገራችን አካባቢዎች ዜጎቻችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia