TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የልጆቻችንን አእምሮ እንዲበርዙ መፍቀድ የለብንም ” - ስፔንሰር ኮክስ

የአሜሪካ ሀገር " ዩታህ ግዛት " በታዳጊዎች ፌስቡክ፣ ቲክቶክ እና ኢነስታግራምን የመሰሉ ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ ገደብ ጣለች።

ይህ በማድረግ አሜሪካ ውስጥ የመጀመሪያዋ ግዛት ሆናለች።

ትላንት ሀሙስ በፀደቀው ደንብ መሰረት ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጆቹ #ኢኒስታግራም#ፌስቡክ እና #ቲክቶክ ከመክፈቱ በፊት የወላጅ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል።

የፀደቀው ደንብ ምን ይዟል ?

- የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎች ለልጆች አገልግሎቱን ከማቅረባቸው በፊት #የወላጆችን ይሁንታ ማግኘት ይኖርባቸዋል።

- ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጆቹ #ኢኒስታግራም#ፌስቡክ እና #ቲክቶክ ከመክፈቱ በፊት የወላጅ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል።

- ኩባንያዎች መተግበሪያዎቻቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ አዳጊዎች ያለ ወላጅ ይሁንታ እንዳይከፍቱ ያደረጋሉ።

- ኩባንያዎቹ የአዳጊዎቹን የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ ታሪክ፣ የለጠፏቸውን እና በግል #የተጻጻፏቸውን_መልዕክቶች ሁሉ ለወላጆች መስጠት ይገደዳሉ።

- የማኅበራዊ ሚዲያ አቅራቢ ኩባንያዎች የልጆቹን ፍላጎት እና ምርጫ መሠረት አድርገው #ማስታወቂያ በልጆቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ሰሌዳቸው ላይ እንዳይለቁ ይገደዳሉ።

- ታዳጊዎች ማኅበራዊ ትስስር መድረኮችን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋት 12፡30 ድረስ መጠቀም እንዳይችሉ ይደነግጋል።

ሕጉ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ከሚቀጥለው ዓመት መጋቢት ጀምሮ ነው።

ይህን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በልጆች #የአእምሮ_ጤና ላይ ከፍ ያለ መረበሽን እያደረሱ መሆኑ ከተደረሰበት በኋላ ነው ተብሏል።

የዩታህ ግዛት ገዢ ስፔንሰር ኮክስ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፤ “ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የልጆቻችንን አእምሮ እንዲበርዙ መፍቀድ የለብንም ” ሲሉ ጽፈዋል።

ከዩታህ በተጨማሪ ተመሳሳይ ሕጎች በቴክሳስ፣ በኦሃዮ፣ በአርካንሳስ፣ በኒው ጀርሲ እና በሊዊዚያና ግዛቶች እየተረቀቁ ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

Credit : #BBC

@tikvahethiopia
👍1.58K114👎46🙏21🤔12🕊9😱6🥰3