TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ባንኮች የአገሪቱ ባንኮች ከአሠራር ጋር በተያያዙ ክፍተቶች በተለያዩ ሥልቶች ለሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ፣ ይህ ሁኔታም በቀጣይ የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ውስጥ የበለጠ እንደሚጨምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ጤናማነትን በመገምገም አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ ምን ይላል ? ➡️
ባለፈው ማክሰኞ ሚያዚያ 8 ቀሲስ በላይ መኮንን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ቀሲስ በላይ መኮንን በ ' አፍሪካ ኅብረት ' ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብና ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።

የቀረበውን ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ የተጠራጠሩት የባንኩ ሠራተኞች ለአፍሪካ ኅብረት የሥራ ኃላፊዎች ስልክ በመደወል ለባንኩ ስለቀረቡት የክፍያ ሰነዶች እና #እንዲከፈል ስለተጠየቀው የገንዘብ መጠን በማሳወቅ የክፍያ ትዕዛዙን ትክክለኛነት እንደጠየቁ ለማወቅ ተችሏል።

የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ኃላፊዎች የተጠቀሰውን የክፍያ ሰነድ ምንም እንደማያውቁትና ኅብረቱም የተባለውን የክፍያ ትዕዛዝ እንዳልሰጠ አሳውቀዋል።

ይህን ተከትሎ የክፍያ ሰነዱን ይዘው ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለማዘዋወር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት ቅርንጫፍ በአካል የተገኙት ቀሲስ በላይ፣ የኅብረቱ የፀጥታ ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ካዋሉዋቸው በኋላ ለፌዴራል ፖሊስ አስረክበዋቸዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪውን ቀሲስ በላይ ሐሙስ ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቅርቧቸዋል።

ፌደራል ፖሊስ ለፍርድ ቤት ምን አለ ?

- ቀሲስ በላይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል እንደቀረቡ ገልጿል።

- ለ3 ግለሰቦችና ለ1 የግል ድርጅት የባንክ ሒሳቦች በድምሩ 6 ሚሊዮን 50 ሺሕ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ኅብረት የፀጥታ ሠራተኞች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው እንደሰጡ ተናግሯል።

- የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት ለችሎቱ በማስረዳት ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ ምን አሉ ?

የተባለውን ድርጊት እንደፈጸሙ ያመኑ ቢሆንም ፣ በወንጀል ድርጊት እንዳልተሳተፉ በመግለጽ ችሎቱ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤት ምን አለ ?

የግራ ቀኝ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ፣ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia