TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማስጠንቀቂያ‼️

‹‹ከሸዋ ሮቢት እስከ ሃርቡ ከተማ ባለው ዋና መንገድ ግራና ቀኝ አምስት ኪሎ ሜትር ድረስ ከፌደራል እና ከክልል የፀጥታ ኃይል ውጭ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል፡፡››
.
.
በሰሜን ሽዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከሰሞኑ የተከሰተውን የሰላም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከፌደራል ልዩ ኃይል እና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል የተውጣጣ ጥምር የፀጥታ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ትላንት #በከሚሴ ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ጥምር የፀጥታ ኃይሉ ዕቅድ አዘጋጅቶ እና በሁለቱም ዞኖች በሚገኙ እና የፀጥታ ስጋት ባለባቸው 10 ወረዳዎች ከሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ11ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ሰኢድ ትኩየ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት እንዳስታወቁት የጥምር ፀጥታ ኃይሉ ዕቅድ ስኬታማ እንዲሆንና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የመላ ሕዝቡ የጋራ ትብብር ያስፈልጋል፡፡ ‹‹ችግሩ ከተከሰተ በኋላ የተለያዩ የፀጥታ ኃይሎች በመግባታቸው በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም ቢኖርም አሁንም ድረስ ግን ሕዝቡ ስጋቶች አሉበት›› ያሉት ብርጋዴል ጄኔራል ሰኢድ የፀጥታ ዕቅዱ ዓላማዎችም ሕዝቡን ወደነበረበት ሰላሙ መመለስ፣ ተጎጅዎችን ማቋቋም፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር እና አጥፊዎችን በመለየት ለሕግ ማቅረብ እንደሆኑም አስታውቀዋል፡፡

እንደ ብርጋዴል ጄኔራል ሰኢድ ገለፃ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ መንገዶችን ሙሉ በሙሉ ክፍት ማድረግ፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቦታቸው መመለስ፣ የግጭቱን አስተባባሪዎች መለየትና ለሕግ ማቅረብ እና ጠንካራ የነበረውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ወደ ነበረበት መመለስ ዕቅዱ የሚመልሳቸው ግቦች ናቸው፡፡ በዕቅዱ ከጥምር የፀጥታ ኃይሎች ውጭ መሣሪያ ይዞ የመንቀሳቀስ ክልከላም ተደርጓል፡፡ ‹‹ከሸዋ ሮቢት እስከ እስከ ሃርቡ ከተማ ድረስ ባለው ዋናው መንገድ ግራ እና ቀኝ 5 ኪሎ ሜትር ድረስ ከፀጥታ ኃይሉ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው›› ተብሏል፡፡ ይዞ በሚገኝ ማንኛም አካል ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም ተገልጿል፡፡

ጥምር የፀጥታ ኃይሉ ለፀጥታ ስጋት ይሆናሉ ያላቸውን 12 የሚደርሱ ቦታዎች በሁለቱም ዞኖች ለይቷል፡፡ በነዚህ ኬላዎች ላይም ጊዜያዊ እና ቋሚ ፍተሻ ይደረጋል፡፡ ከክልል እና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ውጭ በየትኛውም አካባቢ በግልም ሆነ በቡድን የሚደረግ ፍተሻ የተከለከለ መሆኑን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
50 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ...

#በከሚሴ እና #አጣዬ አካባቢዎች ከወራት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭት በወንጀል የተጠረጠሩ 50 ሰዎች ከሕገ-ወጥ መሳሪዎች ጋር መያዛቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ከኮሚሽኑ እና ከሕግ አካላት የተውጣጣ የመርማሪ ቡድን ተዋቅሮ ጉዳዩን ከቦታው ሲያጣራ መቆየቱንም የኮሚሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር #ሰይድ_አህመድ ተናግረዋል፡፡

የምርመራ ቡድኑ በአጣራው መሠረትም በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች የተደራጀ ወንጀል ሲፈፅሙ ቆይተዋል ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡

የምርመራ ቡድኑ በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ጨምሮ ሌሎችንም በቁጥጥር ስር አውሎ ለሕግ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በተጠቀሱት አካባቢዎች ከወራት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭት ከ4 ዓመት ህጻን እስከ 94 ዓመት አዛውንት ህይዎት ማለፉንም ረዳት ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል፡፡

በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ወንጀል የፈፀሙ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia