TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
“ 1.2 ቢሊዮን የምስኪን ሕዝብን ገንዘብ 4 ዓመታት ሙሉ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ እየተጠቀመበት ነው። በውላችን መሠረት መኪና አላስረከበንም ” - የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት በስራቸው ከ2,800 በላይ አባላት ያሏቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሕጋዊ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ከ3 ዓመታት በፊት " ከኦክሎክ ትሬዲንግ/ኃላ/የተ/የግ/ ማኀበር " መኪና እንዲቀርብላቸው ቢዋዋሉም መኪናው ሳይቀርብ የውል ገደቡ እንዳለፈ፣…
#ቅሬታ

“ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው #የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው ? ”- እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናት

2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር አማካኝነት መኪና ለማስመጣት ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ ከ40 በላይ በሆኑ ማኀበራት ሥር የሚገኙ ከ2 ሺህ 800 በላይ ቆጣቢዎች፣ ውል የገባላቸውን መኪና አስመጪ ማኀበሩ በውሉ መሠረት መኪናውን እንዳላቀረበላቸው ገልጸዋል።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንዱ ቆጣቢ፣ “ እኔ በሥነ ስርዓት መረጃ አለኝ። በእኛ ስም እየመጣ እየተሸጠ ነው። ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ ” ሲሉ ኦክሎክ ጀነራል ቲሬዲንግን ኮንነዋል።

ሌሎች ቅሬታ አቅራቢዎች በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

➡️ አንድ ቅሬታ አቅራቢ፣ “ ገንዘባችንን ሰጥተን ለማኝ እየሆንን ነው። ገንዘባቸውን ከፍለው እንደገና የጥበቃ ሰራተኛ ሆነው ተጠግተው መኪና ያገኙ ራሱ አሉ ” ብለዋል።

➡️ ሌላኛው አባት በበኩላቸው፣ “ መኪናውን የሚጠብቁ ሁለት ልጆች አሉኝ። ገናኮ ለየትኛው እንደምሰጥ እያሰብኩ ነው ያለሁት” ሲሉ የነበራቸውን ተስፋ አስረድተው፣ “ ጎዳና ላይ ከምታድር ድሃ መቀነቷን ፈትቶ እንደመውሰድ ነው። ችግር ካለ ስብስቦ ሊጠይቀን ይችል ነበር። ግን በስማችን መነገድ ነው የፈለገው ” ብለዋል።

➡️ ሌላኛዋ ቆጣቢ በበኩላቸው ፦

“ ውላችን ከ3 እስከ 6 ወራት፣ ካልሆነ ደግሞ እስከ 1 ዓመት ነበር፣ 60 ሺሕ ከፍለን የሚለው። 25 በመቶ መኪናው አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ገንዘብ እንከፍላለን የሚል ነው ውላችን ላይ የነበረው። 60 ሺሕ ከፍለን እያለ 2013 ዓ/ም ላይ 25 ፐርሰንት ክፈሉ ተብሎ የመኪናውን ዋጋ 25 በመቶ ስንከፍል፣ እኔ ተመዝግቤ የነበረው መኪና 520 ሞዴል ነበር። የመኪናው ዋጋ 520 ሺሕ ብር ነበር። 

በመካከል 25 በመቶ ክፈሉ ‘የቻንሲና የሞተር ቁጥር መጥቷል’ ተብሎ ተከፈለ። ነገር ግን ‘ይህን መኪና ፋብሪካው ማምረት ስላቆመ 690 ሺሕ የሚመረተውን መኪና ቀይሪ’ ተብዬ 690 ሺሕ ብር የመኪናውን 25 ፐርሰንት 2013 ዓ/ም ኀዳር ወር ከፍዬ እየጠበኩ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ።

በ2014 ዓ.ም ከ2,800 በላይ አባላት በተገኙበት ኦሮሚያ የባህል አዳራሽ ተሰብስቦ ‘ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የመጣሁ ነኝ መኪናችሁን 1 ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ተውስዳላችሁ። እንባችሁ ታብሷል ” ያላቸው አካል እንደነበር ገልጸው፣ ምንም መፍትሄ ስላልተገኘ፣ መንግሥት ይዳኘን " ሲሉ ጠይቀዋል።

➡️ አንዲት እያለቀሱ ቅሬታቸውን ያቀረቡ እናት በመጀመሪያ የነበረውን ውል መሠረት በማድረግ ተስማምተው እንደገቡ ገልጸው፦ “ ሁለት ወራት ጠበቁና 35፣ ‘45 ፐርሰንት ጨምሩ’ አሉን። ያን አድርገን ሳንጨርስ (ተበድረን ያስገባነውን ጉድ) መልሰው ሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ‘400 ሺሕ ብር ጨምሩ፣ አበዳሪ ተገኝቷል በሁለት ወራት ውስጥ ገጣጥመን እናስገባለን’ አሉ። እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባፈልጎ ነው?። አልገባኝም። #መንግሥት_ይዬን ። ” ሲሉ እያለቀሱ ቅሬታ አቅርበዋል።

➡️ ሌላኛው ቆጣቢ በበኩላቸው፣ “ ትዳራችንን ልናፈርስ ጫፍ ላይ ደርሰናል። አብዛኞቻችን ደግሞ የተሸወድነው የመንግሥት ባለስልጣንና ባንክ ቁጭ አድርጎ ቃል ሲገባልን ነው ” ነው ያሉት።

#TikvahaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia