TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት በእስራኤላዊቷ ተማሪ አያ ናምኔህ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል። #RIP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#share #ሼር

የአርቲስት #ተዘራ_ለማ የቀብር ስነ ስርዓት - ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በ9፡ 00 ሰዓት ይፈጸማል። #RIP

ምንጭ፦ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RIP

ኤልያስ መልካ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ ጊታሪስት፣ ፒያኒስት ሲሆን፥ አዳዲስ ሙዚቀኞችን ለሀገራችን በማስተዋወቅና ችሎታቸውን ለይቶ በዚያ እንዲያልፉ በማድረግ ይታወቃል።

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተና ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል። ከዚያ በኃላ ከዜማ ላስታስና ከአፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋር የሰራበት ጊዜ ነበር ። ከ30 በላይ ሙሉ አልበሞችን ልዩ አድርጎም አቀናብሯል።

ከመሃሙድ አህመድ፣ ከኩኩ ሰብስቤ፣ ከፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ከአለማየሁ እሸቴ ጋር የሰራ ሲሆን፥ ቴዲ አፍሮ፣ እዮብ መኮንን፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ልኡል ሀይሉ ሀይሌ ሩትስ፣ ሚካያ በሃይሉ፣ ትግስት በቀለ፣ ቤሪ፣ ዳን አድማሱ ጥቂቶቹ ናቸው። “ሙዚቃ በኤልያስ መልካ ከነሙሉ ክብሯ ታልፋለች”ይላሉ ብዙ ድምፃውያን።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቢሾፍቱ በልምምድ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ በመነሳት በልምምድ ላይ እያለ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ኡኬ ደንካካ በተሰኘ ቦታ መከስከሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ያሚ ለዶቸ ቨለ አረጋግጠዋል። በአደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉንም አቶ…
#RIP

ሻለቃ ሰበሪ ቶፊቅ🕯ሻምበል ኃየሎም ተስፋይ!

#BISHOFTU

በአደጋው በደረደበት ወቅት ኢንስትራክተር አብራሪ ሻለቃ ሰብሪ ቶፊቅ ከተዋጊ ጄቱ ተስፈንጥሮ የወጣ ቢሆንም፣ ፓራሹቱ ሊዘረጋለት ባለመቻሉ ሕይወቱ እንዳለፈ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ሌላው በአደጋው ሕይወቱን ያጣው ሠልጣኝ አብራሪ ሻምበል ኃየሎም ተስፋይ ነው፡፡

ሻለቃ ሰብሪ በ1999 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ አየር ኃይል የበረራ ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማዕረግ እንደተመረቀና አየር ኃይሉን ከአሥር ዓመት በላይ እንዳገለገለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ድሬዳዋ ተወልዶ ያደገው ሻለቃ ሰብሪ በጂማ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ተማሪ የነበረ ቢሆንም፣ ለበረራ በነበረው ፍቅር የምሕንድስና ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አየር ኃይል የበረራ ትምህርት ቤት እንደገባ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በትምህርቱም በከፍተኛ ውጤት ያስመዘግብ እንደነበር ገልጸው፣ ሲመረቅ ከክፍሉ በአንደኛ ደረጃ እንዳጠናቀቀ ተናግረዋል፡፡ ሻለቃ ሰብሪ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበር፡፡

ሱኮይ 27 ተዋጊ አውሮፕላኖች የተገዙት በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ነበር!

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RIP

ከተማሪ አሌክሳንደር ተስፋዬ ሞት ጋር በተያያዘ እስካሁን ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘና ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራውን እያካሄደ እንደሚገኝ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነት እና የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አርማዬ አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ገልፀዋል። የተማሪዉ ስርአተ ቀብር በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት መፈፀሙ ተገልጿል፡፡

Via Ethio FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia