TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን አስተዳደር በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል፣ በዞኑ ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተገልጿል።

በዞኑ አስተዳደርና በታጣቂዎች መካካል የሚደረገው ንግግር " ጥሩ ደረጃ " ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ያሏቸውን ጥያቄዎች በሽማግሌዎች በኩል በደብዳቤ አቅርበው ሁለቱም አካላት በተነሱ አጀንዳዎች ላይ መስማማታቸው ታውቋል፡፡

በቅርቡ አዳዲስ አመራሮች የተሾሙለት ካማሺ ዞን፣ አዲሶቹ አመራሮች ያዋቀሯቸው የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ወደ የሚገኙበት ያሶ ወረዳ ሄደው ታጣቂዎቹን ማነጋገራቸው ተገልጿል፡፡

ከዞኑ አስተደዳር የተላኩት እነዚህ ልዑካን ከታጣቂዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በታጣቂዎቹ በኩል የተወከሉ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችን ይዘው ወደ ካማሺ ከተማ መመለሳቸው ተሰምቷል፡፡

በሁለቱም በኩል ያሉ ልዑካን ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ይዘው የመጡትን የውይይት ሪፖርት በተመለከተ፣ ከዞኑ አመራሮች እንዲሁም በዞኑ ከሚገኙና ከክልሉ የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ጻፊዮ ፤ ከውይይቱ በኋላ በሁለቱም ወገን ያሉ ሽማግሌዎች ተመልሰው ወደ ታጣቂዎቹ ዘንድ መሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡

በካማሺ በተደረገው ውይይት ላይ ታጣቂዎቹ ለሰላም ፍላጎት እንዳላቸው በሽማግሌዎቹ በኩል መግለጻቸውን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፣ ታጣቂዎቹም ሆነ የክልሉ መንግሥት ባሏቸው አጀንዳዎች ላይ መግባባት እንዳለ ገልጸዋል፡፡

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባን ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-02-09

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን አስተዳደር በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል፣ በዞኑ ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተገልጿል። በዞኑ አስተዳደርና በታጣቂዎች መካካል የሚደረገው ንግግር " ጥሩ ደረጃ " ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ያሏቸውን ጥያቄዎች በሽማግሌዎች በኩል በደብዳቤ አቅርበው ሁለቱም አካላት በተነሱ አጀንዳዎች…
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍

የካማሺ ዞን ታጣቂዎች ያናሷቸው ጥያቄዎች ምንድናቸው ?

የካማሺ ዞን ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ዓለሙ በሽር  ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ በእስር ላይ ያሉ አባሎቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የዞኑ አስተዳደሮች ይሄ ጥያቄ በዞኑ የሚመለስ እንዳልሆነ አስረድተው፣ በጉዳዩ ላይ ከበላይ አካላት ጋር ንግግር በማድረግ መልስ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።

ሌላው በመተከል ዞን የሚገኙና ከክልሉ ውጪ ያሉ የፀጥታ ኃይሎች እንዲወጡ ታጣቂዎቹ ጠይቀዋል።

ኮሎኔል ዓለሙ በሽር ፥ " የሌሎቹን አላውቅም፤ የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ሠራዊትን ግን ማስወጣት አይችሉም፣ ይኼ አይመለስላቸውም እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

በተጨማሪም ታጣቂዎቹ " በክልሉ ውስጥ ድርሻ ይኑረን " የሚል ጥያቄም አንስተዋል።

የካማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ጻፊዮ ፤ ታጣቂዎቹ ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ በካማሺ ዞን ደረጃ ሚስተናገዱትን እንደሚመለሱ በክልል ወይም በፌዴራል ደረጃ የሚመለሰውን ደግሞ የዞኑ አስተዳደር ለበላይ አካላት እንደሚያስታውቅ ስምምነት ላይ መደረሱን ለጋዜጣው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍 የካማሺ ዞን ታጣቂዎች ያናሷቸው ጥያቄዎች ምንድናቸው ? የካማሺ ዞን ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ዓለሙ በሽር  ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ በእስር ላይ ያሉ አባሎቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የዞኑ አስተዳደሮች ይሄ ጥያቄ በዞኑ የሚመለስ እንዳልሆነ አስረድተው፣ በጉዳዩ ላይ ከበላይ አካላት ጋር ንግግር በማድረግ መልስ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።…
#Update

#BenishangulGumuz , #Kamashi📍

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጫካ ያሉ ታጣቂዎች ፤ ትጥቃቸውን በሚፈቱበት አካሄድ ላይ ከተወካዮቻቸው ጋር ውይይት ሊደረግ መሆኑ ታውቋል።

የክልሉ መንግስት የተሃድሶ ስልጠና ሃሳቡን ያቀረበው፤ ከጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ታጣቂዎች ጋር ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 10 ቀን 2014 በይፋ ዕርቅ መፈጸሙን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

በጉሙዝ ባህል መሰረት የተከናወነው የዕርቅ ስነ ስርዓት የተካሄደው በካማሺ ዞን፤ ካማሺ ከተማ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽና በካማሺ ወንዝ ዳርቻ ነው።

በዕርቅ ስነ ስርዓቱ ላይ የምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ የክልሉ ም/ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እና የጉህዴን ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉደታ ተገኝተው ነበር።

በካማሺ ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው ዕርቅ ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ነበር።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት እና በጉህዴን አመራሮች መካከል ዕርቅ መውረድ ተከትሎ፤ በጫካ የነበሩ አማጽያን ከእነ ትጥቃቸው ወደ ካማሺ ከተማ ሲገቡ መመልከታቸውን አንድ የከተማውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ ድረገፁ አስነብቧል።

የታጣቂዎቹን ወደ ከተማ መግባት የካማሺ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ቦካ አቦሴም አረጋግጠዋል።

ታጣቂዎቹ ለጊዜው የካማሺ ዞን ባዘጋጀላቸው ማረፊያ እንደሚቆዩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊው ገልፀው ፤ በየትኛው የከተማው አካባቢ እንደሚቆዩ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ያንብቡ ፦ telegra.ph/Ethiopia-Insider-03-20

Credit - Ethiopia Insder

@tikvahethiopia