TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update በጎንደር ከተማ አስተዳደር በአጎራባች ወረዳዎች የሚስተዋሉ #የፀጥታ_ችግሮች ወደ ከተማው #እንዳይዛመቱ የሰላም ኮንፈረንስ ሊያካሂድ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ዘለቀ አለባቸው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቁት ዛሬ ከሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ጋር #የሰላም ውይይት ይካሄዳል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሎቄ🔝በዶክተር #ወላሳ_ላዊሶ የሚመራው የሲዳማ ምሁራን ቡድን ከዛሬ 17 ዐመታት በፊት ልዩ ስሙ #ሎቄ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ በመንግስት #የፀጥታ_ሀይሎች ህወይታቸውን ያጡ ዜጎች ቤተሰቦቻቸውን በአካል በመሄድ ጎብኝተዋቸዋል።

ፎቶ፦ ታሪኩ ለማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

ትናንትና እና ዛሬ በአማራ ክልል በሁሉም ቦታዎች የከተራ እና የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከብሯል፡፡ በዓሉ ያለምንም #የፀጥታ_ችግር መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በክልላችን በሁሉም ቦታዎች በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቋል ብለዋል፡፡

ፖሊስ እና የፀጥታ ኃይሉ ከሳምንት በፊት ዝግጅት እንዳደረጉ የተናገሩት ረዳት ኮሚሽነሩ በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ስጋቶች ቢኖሩም ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡

የፀጥታ ኃይሉ ወጣቶች የሃገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ከፖሊስ ጋር እጅ እና ጓንት ሆነው በመስራታቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ማመስገን ይፈልጋል ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡

ነገ የሚከናወነውን ቀሪ በዓልም በተመሳሳይ ዝግጅትና ጥበቃ ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የፀጥታ_ችግር

ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ  ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በመንግስት መ/ቤቶችና ተቋማት ላይ ጥፋት ሲያደርሱ እንደነበር አመልክቷል።

ባንኮችም ተዘርፈዋል።

በከተማው የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ እንደሆኑና ከአሶሳ-መንዲ የህዝብ ትራንስፖርት ሙሉ ለሙሉ እንደተቋረጠ በክስተቱ ንፁሃን ሰዎች እየተገደሉ ገልጿል።

መንዲ እና አካባቢው ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ያለው የኸው የቤተሰባችን አባል "ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ወደ ከተማ ዘልቀው ገብተው ጥፋት ያደረሱት" ሲል አስረድቷል።

ከአሶሳ ጋር የሚያገናኘውን ዋናውን አስፓልት በመቆረጡ ነዋሪው ትልቅ ስጋት ላይ እንደሆነ ገልጾ " የንፁሃን ደም ከመፍሰሱ በፊት መንግስት ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጥ  እንፈልጋለን " ብሏል።

"  ብዙ ዘመዶቼ እዛ ስላሉ እኔም ጨንቀት ላይ ነኝ " ሲል ሀሳቡን አጋርቷል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን የአስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደበላ ኦላና ደግሞ " ከሰኞ ጀምሮ እስከ ትላንት ማክሰኞ ድረስ የፀጥታ ኃይሉ እና ታጣቂዎች እየተዋጉ ነው " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

አቶ ደበላ በአካባቢው ከሰኞ ጀምሮ ተኩስ እንደነበርና #ከተማው ውስጥም ተኩስ እንደነበር አመልክተዋል።

ታጣቂዎቹ ወደ ከተማ ዘልቀው ሳይገቡ እንዳልቀረ ጥርጣሬ እንዳላቸውም ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#የፀጥታ_ጉዳይ

" የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባልን አመልክተናል " - አቶ ውብሸት አበራ

ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ እንደከፈቱ ተሰምቷል።

ለአል ዓይን ኒውስ የደራ ወረዳ፤ ጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፤ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው የኦነግ ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከባድ ጥቃት እያደረሱ ነው።

ነዋሪዎቹ በቅድሚያ ጥቃቱ በገጠር ቀበሌዎች ላይ መጀመሩን አመልክተው ማለዳ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጉንዶመስቀል ከተማ በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና የመንግስት እና የግለሰብ ንብረቶችም እየተዘረፈ ነው ብለዋል።

በጉንዶ መስቀል ከተማ ዙሪያ ላይ ባሉት ቀበሌዎች የሚኖሩ ዜጎችም መኖሪያ ቤቶች በታጣቂዎቹ እየተቃጠለ እና ከብቶቻቸው እየተወሰዱባቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል። በስፍራው ላይ የመንግስት የጸጥታ መዋቅር እንደሌለም አክለዋል።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ በሰጡት ቃል ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ደራ ወረዳ ዋና ከተማ ጉንዶመስቀል መግባታቸውን ገልጸዋል።

" ታጣቂዎቹ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በከተማዋ ባሉ ባንኮች፣ የመንግስት ተቋማት እና የግለሰቦችን ንብረት እየዘረፉ ነው " ያሉት አስተዳዳሪው የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባላቸው ማመልከታቸውን ለአል አይን ኒውስ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ይዘጋሉ።

የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል መንገዶች የሚዘጉት ለ " ፀጥታ ስራ ሲባል " መሆኑን ገልጾ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኞች ዝግ እንደሚደረጉ ነው ያመለከተው።

የጋራ ግብረ ሃይሉ ከቀናት በኋላ በአ/አ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚከናወነው #የአጀብ እና #የፀጥታ ስራዎች ምክንያት በማድረግ #ሁሉም_የፀጥታ_አካላት_የሚሳተፉበት ወታደራዊ የተግባር ልምምድ እንደሚከናወን አሳውቋል።

ለዚሁ ሲባል የሚከተሉት መንገዶች ለተሽከርካሪ እና ለእግረኞች ዝግ ይደረጋሉ ፦

🚘 ከጎተራ መሳለጫ ወይም ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ጎተራ መሳለጫ ጋር፤

🚖 ከቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሀር የሚወስደው ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መስቀለኛ  ላይ ፤

🚘 ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ቡልጋሪያ ማዞሪያ፤

🚖 ከሳር ቤት በአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ሳር ቤት አደባባይ፤

🚘 ከካርል አደባባይ በልደታ ፀበል ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት  ለሚመጡ ካርል አደባባይ፤

🚖 ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ፤

🚘 ከአብነት ወደ ጌጃ ሰፈር አብነት አደባባይ፤

🚖 ከሞላ ማሩ ወደ አብነት ፖሊስ ጣቢያ ለሚመጡ ሞላማሩ መስቀለኛ ፤

🚘 ከበርበሬ በረንዳ ወደ ቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ  ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤

🚖 ከተ/ሃይማኖት ወደ ጎማ ቁጠባ ተ/ሃይማኖት አደባባይ፤

🚘 ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ዝግ የተደረገ ሲሆን ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡ 

🚖 ከሽሮ ሜዳ ወደ 6 ኪሎ እና ወደ 4ኪሎ የሚያስኬደው መንገድ  ሽሮ ሜዳ ጋር የሚዘጋ ሲሆን ከ4 ኪሎ ወደ ቤተ መንግስት የሚወስደው መንገድ ዝግ ተደርጓል፡፡ 

🚘 ከቀበና ወደ 4ኪሎ ቀበና አደባባይ ፤

🚖 ከጀርመን አደባባይ እና ከሲግናል አካባቢ ወደ 4 ኪሎ ጥይት ቤት ለሚመጡ ጀርመን አደባባይ ፤

🚘 ከካዛንቺስ መናህሪያ ወደ 4ኪሎ እና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሴቶች አደባባይ፤

🚖 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ፤

🚘 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደበባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል መስቀለኛ ፤

🚖 ከቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ ወደ መስቀል ፍላወር ቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ፤

🚘 ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ አፍንጮ በር፤

🚖 ከፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው 6 ኪሎ ዝግ ይሆናል፤

🚘 ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው መንገድ 6 ኪሎ ቶታል ጋር ዝግ የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም ወደ 4 ኪሎ እና በቅርበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመጡ አቋራጭ መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።

በተጨማሪም #ለእግረኛ ተጠቃሚዎች፦

🚶መስቀል አደባባይ 4ተኛ ክፍለ ጦር ወይም ጥላሁን አደባባይ ዙርያ፣
🚶‍♂ኦሎምፒያ ዙርያ፣
🚶‍♂ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ ከቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከሀራምቤ ወደ መሰቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከትምህርት ሚኒስቴር በአራት ኪሎ ብሔራዊ ቤተ መንግስትና ወደ ቦሌ እንዲሁም ከቀበና ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ዝግ መሆኑ ተነግሯል።

ዝግ ሆኖ የሚቆየው ከለሊቱ 11፡ 00 እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ህብረተሰቡ #አማራጭ_መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ተላልፏል።

(የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል)

@tikvahethiopia
#የፀጥታ_ችግር

ዘላቂ ሰላም ያልተገኘለት እና ዛሬም ድረስ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው ቀጠና መፍትሄው ምንድነው ?

• ከ2010 ዓ/ም አንስቶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ንብረት ወድሟል። እርቅ ለመፈፀም ተሞክሮ ዘላቂ ሰላም አልመጣም።

• ከሰሞኑ በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል ፤ እርቅ ለመፈፀም ጥረት እየተደረገ ነው።

• ዛሬ ወደ ገበያ በሚያቀኑ ሰዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ ተጎድተዋል።

በደቡብ ክልል መን፤ በጉራጌ ዞን በመስቃን እና ማረቆ መካከል በተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግሮች እየተከሰቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ ንብረት ሲወድም ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ሲስተጓጎሉ ፣ የመንግሥት ስራም ሲበደል በአጠቃላይ በቀጠናው ከፍተኛ ተፅእኖ ሲደርስ ቆይቷል።

በአካባቢው ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም የዕርቅ ጥረቶች ተደርገውም ያውቃሉ።

ከሰሞኑን ደግሞ በዚሁ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ጉዳትም ደርሷል።

አንድ ስለ ጉዳዩ አውቃለሁ ያሉ የቤተሰባችን አባል ፤ " መስቃን እና ማረቆ ባንተ ወረዳ ይሄን ያክል ቀበሌ አለኝ አንተ የለህም የኔነዉ ያለኝ ባንተ ወረዳ እየተባባሉ ግጭት ከተጀመረ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ እስከ ዛሬዉ ቀን ሰዉ ከመሞትና ቤት ንብረት ከመቃጠልና ከመዘረፍ አልቆመም " ብለዋል።

እኚሁ የቤተሰባችን አባል ፤ በዞኑ እንዲሁም በክልሉ ያሉ አመራሮች ለችግሩ ምንም አይነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ እንዳልቻሉ ፤ ካቅማችን በላይ ነዉ ብለዉም ለከፍተኛ አካል ለፌደራል መንግስት የሰጡት / ያስረከቡት ነገር እንደሌለ አስረድተዋል።

ከሰሞኑንም በዚሁ ቀጠና ላይ የሰዎች ህይወት መቀጠፉን ንብረት መውደሙን አመልክተዋል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-29

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ሞተር ብስክሌት እስከ ረቡዕ ድረስ ታገደ።

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ፤ በከተማው ለሚገኙ የሞተር ብስክሌተኞች በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ከነገ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ እሮብ ነሀሴ 3/2015 ዓ.ም እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

ቢሮው ፤ ክልከላው በምን ምክንያት እንደተጣለ በግልፅ ያለው ነገር የለም።

ክልከላው #የፀጥታ እና #የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት መሆኑን የገለፀው ቢሮው ፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱና ልኡካቸው ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሁለቱም በኩል ያሉ ባለስልጣናት የንግድ ትብብርን በተመለከተና በድንበር #የፀጥታ እና #ደህንነት ጉዳዮች (በሶማሌ ክልል እና በሶማሌላንድ) ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እውን ያደርጋል የተባለለንትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤስአርቲቪ ሶማሊኛ ክፍል ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia