TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate ኦፌኮ እና ሰማያዊ ፓርቲ⬇️

ሰሞኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በአርማ እየተመካኘ እየተፈጠረ ያለው አምባጓሮ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖው ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከማምራቱ በፊት መንግሥት #አፋጣኝ #እርምጃ እንዲወስድ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠየቁ።

ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመግለጫቸው ላይ "ትናንት አስከፊውን አገዛዝ ከጫንቃችን አሽቀንጥረን ለመጣል ያደረግነው ብርቱ ተጋድሎ በጎመራ ማግሥት የለውጡን ሂደት መደገፍና አገሪቱን እንደ አገር የማስቀጠሉ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ሲገባ በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ የሚታዩት ግጭቶችና ሥርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በተለይ ሰሞኑን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው እሰጣገባ በብርቱ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል። ቢዚህም ሳቢያ በተፈጠረ ፉክክር "ትውልዱን ለግጭት ማነሳሳት ፍፁም ሊወገዝ የሚገባው እኩይ ተግባር ነው" ሲሉ አውግዘዋል።

ኦፌኮና ሰማያዊ በመግለጫቸው ላይ ጨምረውም "እያንዳንዳችን ፍላጎታችንንና ድጋፋችንን ለምንሻው አካል እየሰጠን አንዳችን የአንዳችንን ሃሳብም ሆነ መልካም ድርጊትን እያከበርን የተጀመረውን ለውጥና ሽግግር መደገፍ ወሳኝ ነው" ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በአርማ እየተመካኘ የሚፈጠር አምባጓሮ ባስቸኳይ እንዲቆምና ወጣቱ ትውልድ በፍቅርና በመቻቻል ዘመኑን እንዲዋጅ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአባገዳ መሪዎች ወጣቶችን #እንዲያረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia