TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የትምህርት ፍኖተ ካርታ⬇️

በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የቀረበውን ጥናታዊ ምክረ ሀሳብ ከቋንቋ ጋር ማገናኘት ተገቢ እንዳልሆነ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ ሳይሆን ከመጪው ዓመት ጀምሮ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ #ፈተና አይኖርም ብሎ ተማሪዎችን ማዘናጋትም አይገባም ብሏል ቢሮው።

ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተገኙበት ለመጪው 15 ዓመት የትምህርት ሴክተሩ የሚመራበት ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ለውይይት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ በሰጡት መግለጫ ረቂቅ ፍኖተ ካርታውን ተከትሎ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጠው ትምህርት 6ኛ ክፍል ላይ ሊቆም ነው የሚሉ አሉባልታዎች በስፋት እየተደመጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመሆኑም የጥናት ምክረ ሃሳቡ ”በዚህ ቋንቋ ይሰጥ ይህ ቋንቋ ይቅር” የሚል ነገር ስለሌለው ከቋንቋ ጋር ማያያዙ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

የቀረበው ፍኖተ ካርታ ወደፊት ሲጸድቅ በአንደኛና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት በኦሮምኛ ቋንቋ መማሩ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

በፍኖተ ካርታው የቋንቋ ጉዳይ ትኩረት እንደተሰጠው የገለጹት ኃላፊው አንድ የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ አንድ አገራዊ ቋንቋና አንድ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ለሁሉም መሰጠት አለበት የሚለው ነው #እንደሐሳብ የተነሳው ብለዋል።

እነዚህ ቋንቋዎች እነማን ናቸው? የሚለው ጥያቄ ወደ ፊት የሚታወቅ እንጂ በቀረበው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ የተገለጸ አለመሆኑን ህዝቡ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባው ዶክተር ቶላ ገልጸዋል።

የጥናት ቡድኑ ያቀረበው አዲሱ ፍኖተ ካርታ በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ላይ ውሎ የአስረኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ያስቀራል የሚሉ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የቀረበው ረቂቅ ጥናት ዓላማው ምክረ ሃሳብ ማቅረብ እንጂ የተወሰነ ጉዳይ እንዳልሆነ የገለጹት ዶክተር ቶላ ”ገና ሰፊ ወይይት ይፈልጋል፣ ስምምነት ላይ ከተደረሰም በኋላ ሰፊ የቅድመ ዝግጅትና የሙከራ ጊዜ ያስፈልገዋል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ የቀረበው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ከቋንቋ ጋር የተገናኘ ነገር የለውም ማለታቸው የሚታወስ ነው።

በአዲሱ ፍኖተ ካርታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ሲሆን ዝቅተኛ መካከለኛ ደግሞ 7ኛና 8ኛ ክፍል እንዲሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ስር ይጠቃለላል እሱም ገና ለውይይት እየቀረበ ነው።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሲቪል ሠርቪስ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ #ፈተና ሊሰጥ ነው፡፡ የቀድሞው አስተዳደር በሀሰተኛ ሠነድ የተቀጠሩ ሠራተኞች ራሳቸውን እንዲያጋልጡ ማስታወቂያ አስነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ ይሕ ግን እምብዛም አዋጪ አልሆነም፡፡ አዲሱ አስተዳዳር በስሩ የሚገኙ አንድ መቶ አምስት ሺህ ሠራተኞች እንዳስፈላጊነቱ ፈተና ተሰጥቷቸው፣ በሚመጥናቸው ሥራ እንዲመደቡ ይደረጋል ብሏል፡፡

©ዋዜማ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሠላም_ይስጠን!

ሠላም ይስጠን እግዜር ገናና
#ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለሁ እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል ባ'ይኔ

እንደው አንዳንዴ ይገርማል
አረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል
እንዴት ተንዶ ፍቅራችን
ማነው ያራራቀን ከእውነት ቃል
በጊዜ አስታከን በዘመን
ራስን መውደድ አስቀድመን
ይቅርታ ራቀ ካ'ፋችን
ስናይ እየተጠማ ልባችን

አንቃን...

ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሠላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቀን ወዳጅ አ'ርገህ አንቀን
አንቃን

የት ይደረሳል
ምን ይወረሳል
ይብቃን
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚህ #ፈተና
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና
.
.
ሠላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለሁ እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል ባ'ይኔ

በሀሜት በወሬ ታጅበን
በግላዊ ምቾት ተከበን
በዚች ጊዜያዊ ከንቱ ዓለም
ዘላ'ለም ቋሚ ግን አንድ የለም
ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን
ክፋት ምቀኝነትን መርጠን
ዘመን አለፈ ስንኖር
የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን

አንቃን
ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሠላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቀን ወዳጅ አ'ርገህ አንቀን
አንቃን
የት ይደረሳል
ምን ይወረሳል
ይብቃን
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
#እግዚኦ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚህ ፈተና
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
#እግዚኦ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

ድምፃዊ #ጎሳዬ_ተስፋዬ
#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiop
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "

@tikvahethiopia
" ... ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ ነው የሚል ግምገማ የለንም " - የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል።

ዜጎች ፤ የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶችን ከመንግስት ተቋማት ማግኘት #ፈተና_እንደሆነባቸውም ተቋሙ ገልጿል።

የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ የሆኑት ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሠጡት ቃል ፤ " እንደ አጠቃላይ እንደ ሀገር የመልካም አስተዳደር ችግሩ እየሰፋ ተፈጥሮውም Complex (ውስብስብ) እየሆነ ነው የመጣው ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ ነው የሚል ግምገማ የለንም ፤ ይሄንን መንግስትም የሚያውቀው ጉዳይ ነው " ብለዋል።

" የመንግስት ተቋማት የተቋቋሙለት የሚቋቋሙበት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ነው " ያሉት ዶ/ር እንዳለ " ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጡ ከዜጎች የሚሰበሰብ ታክስ አለ፣ ከዜጎች ከሚሰበሰብ ታክስ ነው እያንዳንዱ የመንግስት ተቋም የሚተዳደረው ፣ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዙ የሚከፈለው ፤ ነገር ግን #ከህብረተሰቡ_በሚሰበሰበው_ታክስ ፣ ህብረተሰቡ ከሚያወጣው ወጪ አንፃር አገልግሎት እየተሰጠነው የሚል አጠቃላይ ግምገማ የለንም " ሲሉ ገልፀዋል።

ይህ ችግር ለዜጎች ሰፋ ያለ አገልግሎቶችን መስጠት በሚጠበቅባቸው የመንግስት ተቋማት የሚብስ ሲሆን ከተማ አስተዳደር፣ ወረዳ እና ቀበሌ ዋና ዋና ተጠቃሽ ናቸው።

ዶ/ር እንዳለ " በተለይ የከተማ አስተደሮች አካባቢ ፤ በተለይ ማዘጋጃ ቤቶች አካባቢ፣ ሰፋፊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አካባቢ እንደ #ወረዳ#ቀበሌ#ከወሣኝ_ኩነት ጋር ተያይዞ መሰረታዊ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለ መንግስትም ያምናል የኛም ግኝት ያን ያመለክታል " ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፥ " በፌዴራል መስሪያ ቤቶች የመልካም አስተዳደር ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው ? " የሚለውን ካሉት 22 ሚኒስትር መ/ቤቶች ሰፋፊ አገልግሎት በሚሰጡ 15 መ/ቤቶች በቅርብ ቀን ጥናት በማድረግ ለህዝብ እናሳውቃለን ሲል ለሬድዮ ጣቢያው አሳውቋል።

#credit_ሸገር_ኤፍ_ኤም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ' ፈተና አለ ' ተብለን ስንገላታ ከዋልን በኃላ ' ቀርቷል ' አሉን " - የመንግሥት ሰራተኞች " ፈተናው በመሰረዙ #ይቅርታ እንጠይቃለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለመንግሥት ሰራተኞች ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና አለመሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። ቅሬታቻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የአስተዳደሩ ሰራተኞች " ፈተና አለ " ተብለው ቀኑን ሙሉ ሲንከራተቱ…
#AddisAbaba #ፈተና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦

" የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና
* ለአመራሮች ፣
* ለባለሙያዎች
* ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት ሰጥቷል።

ሆኖም ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ #ይቅርታ ጠይቋል።

ቀጣይ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ምዘና ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ #በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል። "

@tikvahethiopia