TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጋብቻ

እየተጠናቀቀ ባለው በ2015 ዓ/ም የጋብቻ ፍቺ የፈፀሙ እና የተመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ባለትዳሮች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር #በእጥፍ እንደበለጠ ታውቋል።

የአ/አ ሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በሰጡት ቃል፤ " በ2015 ዓ/ም በጀት አመት 4,696 ሰዎች ፍቺ አስመዝግበዋል ፤ አምና መጥተው ያስመዘገቡት 2,937 ሰዎች ነበሩ " ብለዋል።

ምዝገባው ነው የጨመረው እንጂ ፍቺው ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል ሲሉ ዳይሬክተሩ አክለዋል።

የፍቺ ሁኔታ ከእጥፍ በላይ ጭማሪ ቢያሳይም ሂደቱ ፍርድ ቤትን ጨምሮ በተለያየ መንገድ የሚከናወን በመሆኑ ትክክለኛውን ቁጥር ለማውቅ አዳጋች እንደሆነ አቶ ዮሴፍ ገልጸዋል።

" ፍ/ቤት ላይ የሚፈፀመውን ፍቺ እዛው ወቅታዊ ምዝገባውን የማከናወን ስራ በዚህ አመት አቅደን አልተሳካም ሚቀጥለው አመት እየተነጋገርን ነው ፍርድ ቤት ሆነን ምዝገባ የሚከናወንበት ሁኔታ ይመቻቻል ብለን እንጠብቃለን። " ብለዋል።

" በዚህ መንገድ ትክክለኛውን ዳታ ፍቺ እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ ነው የሚለውን ውሳኔ ለመስጠት እንችላለን " ያሉት አቶ ዮሴፍ " አሁን ላይ ግን የኛ ምዝገባ ሰው ፍልጎ ፍቺውን በተለያየ አግባብ ለንብረት ክፍፍል ፣ ከመታወቂያ ዲጂታላይዝ መደረግ ጋር ተያይዞ የጋብቻ ሁኔታ ፍቺ የማስባል እና ሌሎች ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ... በዛ ምክንያት እኛ ጋር ምዝገባው ከአምና ከፍ ብሏል የሚል ድምዳሜ ነው የያዝነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#ቪኦኤ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋብቻ እየተጠናቀቀ ባለው በ2015 ዓ/ም የጋብቻ ፍቺ የፈፀሙ እና የተመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ባለትዳሮች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር #በእጥፍ እንደበለጠ ታውቋል። የአ/አ ሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በሰጡት ቃል፤ " በ2015 ዓ/ም በጀት አመት 4,696 ሰዎች ፍቺ አስመዝግበዋል ፤ አምና መጥተው ያስመዘገቡት 2…
#ጋብቻ

አሳስቢውን የጋብቻ ፍቺ ለመግታት ወደ ጋብቻ ከማምራት በፊት የጋብቻን መርህ ፣ ዓላማ ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል ሲሉ የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪ ባለሞያው ተናገሩ።

የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪ አቶ ይመስገን ሞላ ትዳራቸውን ለማትረፍ ምክር ፈልገው የሚመጡ ቤተሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

የጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪው ምን አሉ ?

" የችግሩ አይነት እየበዛ እየጨመረ መጥቷል። በዚህም ቢሯችን የምናስተናግደው እንኳን አብዛኛው ችግር ሲገጥማቸው ለምክር የሚመጡ ናቸው ለመገንባት ከሚመጡ ይልቅ።

በሀገራችን ምክንያት ተብለው የሚሰጡ አሉ፦
- የመጀመሪያው በወሲብ አለመጣጣም ይባለል ፣
- በገንዘብ እጥረት ይባለል አብዛኛው የሚፋታው ግን ገንዘብ ሲያገኝ ነው፣
- የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት / የጓደኛ ጠልቃ ገብነት ይባለል ይህም ቢሆን የግንኙነቱን ስስ መሆን ያሳያል፣
- የኮሚኒኬሽን ችግር ይባላል ፣
- አሁን እየጨመረ የመጣው የእምነት ጉዳይ ይነሳል በሁለቱ መካከል አለመተማመን አለ ምክንያት የሚባሉት እነዚህ ናቸው።

ለእኔ ግን ከዚህም በላይ ተጨማሪ ምክንያቶች አሉ ፦
- ያለን መንፈሳዊ እሴት መበላሸት አንድ ነገር ነው ፤
- በጾታዊ አክራሪነት የመጣው የወንድ እና የሴት ፆታ መገፋፋት ፣ አለመቀባበል በሁለቱ መካከል ያለው መተባበር ሳይሆን መፎካከር ስላለ፣ እንደ ባል እና ሚስት ሚናቸውን አለማወቃቸው ምክንያት ናቸው።

መጋባት ይፈልጋሉ ተዋደን ይሆናል ብለው መዋደድ ግን የጋብቻ መሰረት አይደለም ወይም ፍቅር ስላለ ጋብቻ መሰረት አያገኝም ውጤታማም አይሆንም። የጋብቻ መርህ አላማ፣ የጋብቻን ምንነት መረዳት ይጠይቃል። የነዚህ ሁሉ ድምር ውጤቶች ጋብቻ እንዳይፀና ቤተሰብ እንዲፈርስ ያደርጋል።

ወደ ጋብቻም ወደ ቤተሰብም የገቡ ሰዎች አስበው አይገቡበትም፤ ገብተው ምን እንደሚያደርጉ፣ ከመግባታቸው በፊት ምን መዘጋጀት እንዳለባቸው ስለማያውቁ ጋብቻው እንዳይዘልቅ ቤተሰብም እንዲፈርስ ዋነኛ ምክንያት ይሆናሉ። "

ባለሞያው ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ወደ ትዳር የሚገቡ #ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው ከጋብቻ በፊት ስልጠና የመውሰድ ልምድም እያደገ ነው ብለዋል። ይህ ፍቺን ለመቀነስ ሚና እንዳለው ጠቁመው ከምንም በላይ ግን ቤተሰብ ልጆችን ሲያሳድግ አርያ መሆን አለበት ብለዋል።

ባለሞያው ፦

" ጋብቻ ብዙ ጊዜ እኛም ሀገር አይተን እንደሆነ ስመረቅ፣ ቤት ስገዛ ፣ስራ ስይዝ ብለው condition ያስቀምጣሉ ጋብቻ ግን Condition ሳይሆን Qualification ነው የሚጠይቀው። የበቃች ሚስት የበቃ ባል ለመሆን እራሱን አስቀድሞ ማዘጋጀት አለበት።

ለምሳሌ ፦ ባልነት ለበሰለ ወንድ ነው ኃላፊነት ለመሸከም ለበቃ ወንድ ነው ሚስትነትም እንደዛው ስለዚህ ከመዋደድ ያለፈ የመጋባት ምክንያትና ኃላፊነት የመወጣት አቅም ይጠይቃል። አንድ ወንድ ባል የሚሆነው ብስለቱና ብቃቱ ነው ወንድነቱ ብቻ ባል አያደርገውም። ስለዚህ ይህን ለማድረግ በግል እራስን መገንባት አለበት።

ወላጆች ልጆቻቸውን ለራሳቸው ጥሩ ልጅ፣ ለዛ ቤት ደግሞ ጥሩ ባልና ሚስት እንዲሆኑ፤ ሲወልዱ ጥሩ አባት እና እናት እንዲሆኑ ሞዴል መሆን አለባቸው።

አሁን የሚታየው የጋብቻ መፍረስ፣ የፍቺው ብዛት፣ የልጆች መጎዳት ትላንት ያልተሰራው ስራ መዘዝ ነው። ነገም እንደዚያ ይቀጥል ከተባለ ዛሬ እያንዳንዳችን የራሳችንን ቤት ጠብቀን ልጆቻችንን ለጋብቻ ማብቃት (የራሳችንን ጋብቻ በመጠበቅ)፣ ልጆቻችን እንዲሰለጥኑ ማድረግ ጋብቻን አውቀው እንዲኖሩ ማድረግ መፍትሄ ነው " ብለዋል።

ፁሁፍ በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት።
Credit፦ ቪኦኤ (አስማማው አየነው)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba #ጋብቻ #ፍቺ #ልደት #ሞት

በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት አፈፃፀም ከባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ቁጥር የላቀ የኩነት እና የዲጂታል ምዘገባ መመዝገቡን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ኤጀንሲው ፤ ከ393 ሺህ በላይ የዲጂታል ምዝገባ እና ከ210 ሺህ በላይ የኩነት ምዘገባ መደረጉን ነው የገለጸው።

ከተመዘገበው ጠቅላላ ኩነት ፦

181 ሺ 983 ልደት፣
16,933 ጋብቻ
2,813 ፍቺ
8,761 ሞት ሲሆን ከዚህም ውስጥ በአንድ ዓመት ገደብ ውስጥ የተመዘገበው ፦
* አዲስ ጋብቻ 5,171
* በፍርድ ቤት በተከናወነ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ የተመዘገበ ፍቺ 1,296
* ሞት 2,312 መሆኑ ታውቋል።

ከ2015 ዓመት በንፅፅር ሲታይ ፦ አዲስ ልደት በ65%፣ ፍቺ በ106.7% እንዲሁም ሞት በ25.29% ጭማሪ ብልጫ ያሳየ ሲሆን ጋብቻ በ5% የቀነሰ መሆኑ ተገምግሟል።

በነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ ለ393,303 ነዋሪዎች በአዲስ፣ በምትክ፣ በእርማት እና በእድሳት የመታወቂያ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 311 ሺ 446 (93%) የዲጂታል  መታወቂያ መሆኑ በአፈፃፀሙ የተሻለ አድርጓታል።

በተጨማሪም በዚሁ ዘርፍ 76,299 የያላገባ  ማስረጃ እንዲሁም 15,369 የመሸኛ (Clearance ) አገልግሎት በከተማዋ ተሰጥቷል።

ከተመዘገበው ኩነት ትንተና በዕድሜ ሲታይ ፦

ልደት
6% ከ1 ዓመት በታች፣
28% ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት፣
26% ከ6 ዓመት እስከ 17 ዓመት እንዲሁም
40% ከ17 ዓመት በላይ መሆናቸው ትንተናው ያመላክታል፡፡

ጋብቻ
72.8% የሚሆነው ተገቢ ከ18 - 40 ዓመት
27.2% የሚሆነው ከ41 በላይ መሆኑ ትንተናው አሳይቷል።

ሞት
0.01% ከተወለደ ከ28 ቀን እስከ 1 ዓመት የተከሰተ ሞት፣
0.6% ከተወለደ ከ2 ዓመት እስከ 17 ዓመት የሞተ፣
22.9% ከተወለደ  ከ18 ዓመት እስከ 40 ዓመት የሞተ፣
28.5% ከተወለደ ከ41 ዓመት እስከ 60 ዓመት የሞተ፣
35% ከተወለደ 61 ዓመት እስከ 80 ዓመት የሞተ፣
12% ከተወለደ 81 ዓመት እስከ 100 ዓመት የሞተ፣
0.9% ከተወለደ ከ100 ዓመት በላይ የሞተ መሆናቸው ያመላክታል፡፡ 

በስድስት ወራት አፈፃፀም በከተማው የዲጂታል ምዝገባ እና ልደት ምዝገባ የተሻለ አፈፃፀም የታየባቸው መሆኑ ተነግሯል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ምንም እንኳን የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም ፤ አገልግሎቱን በጥራት ከመስጠት አንፃር የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ከአፈፃፀሙ እኩል ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የቀሪ ወራት አቅጣጫ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia