TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የገቢዎች ሚኒስቴር🔝

ከላይ የምትመለከቱት #በታክስ_ኦፕሬሽን #ደረሰኝ_ባለመቁረጥ የተያዙ የ65 ድርጅቶች ዝርዝር ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነጋዴዎች #ደረሰኝ #መርካቶ

" ደረሰኝ መቆረጥ አለበት በዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር የለውም " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ በተለይ በግዙፉ የገበያ ማዕከል ' መርካቶ ' በንግድ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ነጋዴዎች ሱቅ የመዝጋትና ስራ የማቆም እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ሰሞነኛውን የመርካቶ ገበያ ሁኔታ በተመለከተም ነጋዴዎቹ ከከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተቀምጠው ነበር።

በውይይቱ በነጋዴዎቹ በኩል በርካታ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ተነስተው ነበር። ለተነሱት ጥያቄዎች የመንግሥት አካላት ምላሽ ሰጥተዋል።

ነጋዴዎች ሃሳባቸው ፣ ጥያቄያቸው፣ ቅሬታቸው ምንድነው ?

➡️
ደረሰኝ መቁረጥ ፣ ግብር መክፈል ለሀገር ወሳኝ ፤ ለራስም ይጠቅማል። ግን አከፋፈሉ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።

➡️ እኛ ስንገበያይ
ደረሰኝ እናገኛለን ወይ ? አንዳንድ ምርት የሚነሳው ከገበሬ ነው። ከገበሬ ነጋዴ ይሰበስባል ይከፍላል፣ ተረካቢው ይረከባል ይከፍላል፣ ተጭኖ ይመጣል እኛ እንረከባለን ይሄ ሁሉ ይከፍላል ብዙ ነገር ነው ያለው። የቆረጠው ይቆርጥልናል የሌለውን ንግድ ፍቃድ እናያይዛለን። እንዲህ ስንሰራ ነው የቆየነው።

➡️ ሁሉም እየመጣ ባለድርሻ ነኝ ይላል። መርካቶ እንደምንታመስ ያውቃል ሌባው ይገባና " ሄደህ 100 ሺህ ብር ከምትቀጣ ለኔ ይሄን ስጠኝ " ይላል።

➡️ እቃው በደላላ ነው የሚመጣው ፤ ድሮ አስመጪ በእያንዳንዱ ሱቅ ሄዶ እቃ ይበትን ነበር አሁን ግን አስመጪው ለደላላ፣ ለቤተሰብ ፣ ለዘመዱ ፣ ለጎረቤት፣ ለጓደኛ ነው የሚሰጠው። እቃው ይመጣና በተለያየ መጋዘን ይቅመጣል ከዛ በስልክ ነው ልውውጥ የሚደረገው ነጋዴው ደላላውን '
ደረሰኝ ስጠኝ ' ካለው ነገ እቃ አይሰጥም።

➡️ ቁጥጥር እየተባሉ የሚመደቡ ሰዎች ባጅ የላቸው፣ ምናቸውም አይታውቅ፣ ሱቅ የሚገቡት እንደ ሌባ 3 እና 2 እየሆኑ ነው ስለዚህ ህጋዊ ይሁኑ ህገወጥ ምናቸው ይለያል ?

➡️ ባልተማከለ ሲስተም ውስጥ ነው ያለነው።
ደረሰኝ አልቆረጣችሁም በሚል መቶ ብር አትርፈን 100 ሺህ ብር ነው የምንጠየቀው።

➡️ እስቲ ኢንዱስትሪውን ተቆጣጠሩ
ደረሰኝ ቼክ ይደረግ የሚወጣው አንደርኢንቮይስ ከሆነ በምን አግባብ ነው ነጋዴው የሚጠየቀው ?

➡️ "
ደረሰኝ ቁረጡ ደረሰኝ ቁረጡ " ሲባል ሌላ ነገር ነው የሚመስለው ደረሰኝ ይዞት የሚመጣው ገንዘብ ነው። መጀመሪያ የንግድ ስርዓቱ መስተካከል አለበት።

➡️ ለ100 ሺህ ብር ቅጣት በዚህ ፍጥነት ከተሰራ ነጋዴውን ለማገዝ በገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠቱን ዕድሎች ተፈጻሚ ለማድረግ ለምን አልተቻለም ?

➡️ አሰራሩ እኮ ብዙ ነው። አልታየም። እንደ ከተማ አንድም አስመጪ የለም። አስመጪዎቹ ' መርካቶ መጥተን አንሸጥም ጅግጅጋ መጥታችሁ ግዙ ' ይሉናል። በደረሰኝ ስንት ስቃይ ነው ያለው። እዛ ተኪዶ ነው ሚገዛው ? እሺ እዚህ ስናመጣ ገቢዎች ላይ ብዙ ነገር አለ ፤ ደረሠኝ ይጥላሉ፣ ' አንቀበልም ' ይላሉ የት እንሂድ ?

➡️ አሰራሩ ላይ ትልቅ ችግር አለ።

➡️ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ አስመጪዎች
ደረሰኝ ይሰጣሉ ወይ ? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው።

ለነጋዴዎች ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ምን መለሱ ?

🔴 የገቢዎች የቁጥጥር ሰራተኞችን በተመለከተ መታወቂያ አላቸው፣ 3 እና 4 ሆነው ነው የሚገቡት። መታወቂያ የሌለው ካለ ህገወጥ አጭበርባሪ ነው ተከላከሉት።

🔴 " የገቢዎች ሰራተኛ ነን " ብለው ሲያጭበረብሩ የተያዙ ሰዎች አሉ።

🔴 ለገቢዎች ሰራተኞች መታወቂያ ተሰጥቷል። መታወቂያ ማሳየት አለባቸው። እናተም ጠይቋቸው።

🔴
ደረሰኝ ላለመቁረጥ የሚሰጡትን ምክንያቶች በጋር እየተነጋገርን እንፈታለን እንጂ ደረሰኝ መቁረጥ እንዲቆምላችሁ የምትጠይቁትን ጥያቄ መንግስት መመለስ አይችልም። ይሄን በግልጽ እወቁት።

🔴 በገቢዎች ውስጥ ያሉ ችግሮች ይታወቃሉ መፈታት አለባቸው። ከብልሹ አሰራር፣ ከሌብነት ጋር በተያያዘ የተነሱ ችግሮች ይታረማሉ።

🔴 ቫትን በተመለከተ በአዲሱ አሰራር 7 ሺህ ብር ነው የቀን ግምቱ የተቀመጠው። ቀደም ሲል ቫት የነበረ ወደ ታች ሊወርድ አይችልም። በቀን 7 ሺህ ብር የሚሸጥ ሰው ምን ያክል ነው የሚለውን እናተው ታውቃላችሁ። ቅድሚያ እየተሰጠ ያለው ቫት ውስጥ መግባት እያለበት ቫት ውስጥ ያልገባው ነጋዴ በተለይ መርካቶ እሱ ባለመግባቱ በሚሸጠው እቃ ላይ የዋጋ ልዩነት እየመጣ ስለሆነ ቫት ውስጥ መግባት ያለበትን ቫት ውስጥ እያስገባን ነው።

🔴 ቫት ውስጥ የነበረ ነጋዴ ልወርድ ይገባል ብሎ ተጨባጭ ማስረጃ ካቀረበ ይታያል። አሁን ባለው የዋጋ ንረት እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እንጂ እላይ የነበረው ወደ ታች አይወርድም።

🔴 የቁጥጥር ስርዓቱ እየጠበቀ ነው የሚሄደው።

🔴 እኛ ስለትላንቱ አለነሳንም አሁን ግን መርካቶ የሚደርገው ግብይት በደረሰኝ እና በደረሰኝ ብቻ መሆን አለበት። ይህን የሚያደርገውን ነጋዴ እንደግፋለን።

🔴 ነጋዴው በህጋዊ መንገድ ይጠቀም አልን እንጂ ነጋዴውን የሚያስቀይም ፣ የሚያሳድድ እርምጃ ለመውሰድ የሚፈልግ አካል የለም።

🔴 መርካቶ የሚደረገው እንቅስቃሴ በክልል ጥያቄ ያስነሳል። መረካቶ
ደረሰኝ ስለማይቆረጥ የንግዱ ማህበረሰብ ክልል ሄዶ ሲነግድ ደረሰኝ አቅርቡ ሲባል " ያለ ደረሰኝ ነው የገዛነው እዛ ደረሰኝ አልተቆረጠም " የሚሉ አሉ።

🔴 የዚህ አመት እቅዳችን ግዙፍ የሆነ ገቢ ለመሰብሰብ አቅደናል። ይህን የምናደርገው የታክስ ቤዛችንን በማስፋት፣ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ በመቀየር ነው።

🔴 ኢ-መደበኛ እናሳድዳለን አላልንም ግን ወደ መደበኛ ይግባ እያልን ነው።

🔴 ብዙዎቻችሁ (ነጋዴዎች) ያነሳችሁት ጥያቄ
ደረሰኝ እንዳይቆረጥ የሚጠይቅ ዝንባሌ አለው። " ደረሰኝ አያስፈልግም " አትሉም ግን ጅምላውን፣ አከፋፋዩን ፣ አምራቹን ቅድሚያ ስጡ ነው የምትሉት። ጅምላውም ላይ፣ አከፋፋዩም ላይ ፣ አምራቹም ላይ እንሰራለን ቸርቻሪም ላይ እንደዛው ይሰራል። ሁሉም ደረሰኝ መቁረጥ አለበት።

🔴
ደረሰኝ ለመቁረጥ የማይስችል ሁኔታ ካለ ማስረዳት ነው እንጂ " ደረሰኝ አንቆርጥ " የሚል እሳቤ ተቀባይነት የለውም።

🔴 በደረሰኝ መቆረጥ አለበት ምንም አይነት ድርድር የለውም በዚህ ጉዳይ። እኛ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ እናስገባለን።

🔴 አቤቱታ ካላችሁ በማንኛውም ጊዜ አቅርቡ። ገቢዎች አካባቢ ያለውን ነገርም እንፈትሻለን።

#AddisAbaba #Merkato

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ደረሰኝ

🔴 " ከዛ ቤት የሚወጣ እቃ ደረሰኝ አያውቅም ይሄንን ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም። ቻይኖቹን ፈርታችሁ ይሁን ምን ይሁን እኛ አይገባንም " - የውይይት ተሳታፊ

🟠 " የ1 ሚሊዮን ብር እቃ ገዝታችሁ የ300 ሺህ ብር ደረሰኝ ነው የሚፅፉት (ይህ ምሳሌ ነው) " - የውይይት ተሳታፊ

🔵 " ከቻይኖች (ከፋብሪካዎች) ጋር የተነሳው ጉዳይ ከፌዴራልም ጋር በነበረን መድረክ ተነስቷልግብረኃይልም ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል " - የአ/አ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

👉 " ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈጽማችሁ የምትገኙ ከሆነ በ100 ሺህ ብር ቅጣት ብቻ አናልፍም ! "

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም የተነሳ ከአሰራር ጋር ተያይዞ ከነጋዴዎች በኩል አንዳንድ ቅሬታዎች መደመጣቸው አይዘነጋም።

በተለይ ታች ያለው ነጋዴ " ጉዳዩ ስር የሰደደ ነው ከላይ ጀምሮ መጥራት አለበት። መቼ ፋብሪካዎች፣ አስመጪዎች ፣ አምራቾች አከፋፋዮች ደረሰኝ ይሰጡናል ፤ ዝም ብለው አይደል የሚያወጡት መጀመሪያ እነሱን መቆጣጠር አለባችሁ " የሚሉ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር።

ከቀናት በፊት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢንያም ምክሩን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ከአስመጪዎች እና አከፋፋዮች ጋር ውይይት ተካሂዶ ነበር።

አንድ የውይይቱ ተሳታፊ " እኛ ፎሬይን ዳይሬክት ኢንቨስትመንት አይተግበር እያልን አይደለም ነገር ግን ዱከም ኢንዱስትሪ ዞንን ዞር ብላችሁ ያያችሁትም አይመስለኝም ፤ እኔ አሁን አሁንማ የሌላ ሀገር እየመሰለኝ መጥቷል። እሱ ቦታ ከዛ ቤት የሚወጣ እቃ ደረሰኝ አያውቅም ይሄንን ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም። ቻይኖቹን ፈርታችሁ ይሁን ምን ይሁን እኛ አይገባንም " ብለዋል።

" ግራ እየገባን ነው እኛ ሀገራችን ነው ብንሰርቅም እዚሁ ነው የምንጥለው የሆነ ሰዓት መገኘታችን አይቀርም እነሱ ግን ሀገራቸው አይደለም ሰርቀው ይዘውት ነው የሚሄዱት " ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላ ተሳታፊው " በኢስት ኢንዱስትሪ ዞን ያለው ነገር ግልጽ ነው ይሄ ለናተ ተደግሞ መነሳትም ያለበት ነገር አይደለም ፤ የ1 ሚሊዮን ብር እቃ ገዝታችሁ የ300 ሺህ ብር ደረሰኝ ነው የሚፅፉት (ይህ ምሳሌ ነው)" ብለዋል።

" በአንድ ደረሰኝ ከ20 እና 30 በላይ መኪና ይመላለሳል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ኢንቨስትመንቱ ሁሉም ነገር እንዳለ ሆኖ ግን ሀገራችን ላይ እናተ በአቅማችሁ ደረጃ ማኔጅ ማድረግ የማትችሉትን ነገር ነው መሰለኝ እየፈቀዳችሁ ያላችሁት ለፎሬይን ኢንቨስትመንት ምክንያቱም ከውጭ ፌሬይን ኢንቨስትመንት ይግባ ሲባል ያንን ማኔጅ ማድረግ እንችላለን ወይ ? የሚለው ጥያቄ አብሮ መመለስ አለበት ካልሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል እንደ ሀገር ። እዛ ላይ የሚመለከተው አካል ይስራበት " ሲሉ አክለዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ የከተማው ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ቢንያም ምክሩ ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር።

" የተነሳው ትክክል ነው እኛም እናውቀዋለን " ብለዋል።

" ከቻይኖች ጋር የተነሳው ጉዳይ ከፌዴራልም ጋር በነበረን መድረክ ተነስቷል። ከዚህ ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚፈታ በክብርት ሚኒስትሯ የሚመራ የፌዴራል ገቢዎች ፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ኦሮሚያ ክልል መንግሥትን ያቀፈ አንድ የጋራ ቅንጅት የሚመራበት ማንዋል ፀድቆ ወደ ስራ ተገብቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ የኢስት ኢንዲስትሪ ዞንና ሌሎች ጋር የተገናኙ ወደ ከተማው የሚገባ ምርት በሸገር ከተማ ዙሪያ የሚመረቱ ነገር ግን ያለደረሰኝ ከፋብሪካ የሚወጡትን እዛ ያለው አዲስ የተቋቋመው ግብረኃይል ይከታተለዋል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊው በመርካቶም ሆነ በሌላ የከተማው አካባቢ የሚካሄደው የደረሰኝ ቁጥጥሩ ወቅታዊ ሳይሆን በዘላቂነት የሚሰራበት ነው ብለዋል።

ከአሰራር ጋር በተያያዘ ያሉት ችግሮች እንደሚፈቱ ቃል ገብተው ለአስመጪና አስከፋፋዮች ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ኃላፊው ፤ " ከዚህ በኃላ በግልጽ ልንነግራችሁ የምንፈልገው አስመጪ እና አከፋፋይ የሆናችሁ ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈጽማችሁ የምትገኙ ከሆነ በ100 ሺህ ብር ቅጣት ብቻ አይደለም የምናልፈው " ብለዋል

" በቀጥታ የኦዲት ምርመራ (Investigation Audit) ውስጥ ነው የምንገባው ይህ ደግሞ በጣን ክፉኛ ይጎዳችኋል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" መርካቶ ውስጥ ያለ ድረሰኝ ግብይት ሙሉ ለሙሉ መቆም አለበት " ያሉም ሲሆን ከጊዜ ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ " ለዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ የለም ቁጥጥራችን ይጠናከራል "  ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia