TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አ.ሳ.ቴ.ዩ~የአስክሬን ምርመራ ውጤት🔝

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሞተው የተገኙት የ3 ተማሪዎች #አስክሬን_ምርመራ ውጤት ይፋ ተደርጓል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦርደዴ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት 7 ሰው ሞተ!

ከሀረር ወደ ኢዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ልዩ ስሙ ቦርደዴ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በአካባቢው በተፈጠረ ግጭት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ምንም ዓይነት መኪና እንዳያልፍ ተዘግቷል፡፡

ከሀረር ወደ አዲስ አበባ ፣አዳማ እንዲሁም ሌሎች አካቢዎች ለመሄድ የተሳፈሩ ተጓዦች ከማለዳው 2 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ መዘጋቱን እና በረሀ ላይ መሆናቸውን መንቀሳቀስም እንዳልቻሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ጥቆማውን የሰጡ ግለሰቦች እንዳሉት ከቦርደዴ - አዋሽ መግቢያ ድረስ መኪኖች መንቀሳቀስ ባለመቻለቸው ተሰልፈው መቆማቸውን እና ይህ ነው ብሎ የተፈጠረውን ችግር ያስረዳቸውም ሆነ መፍትሄ የነገራቸው አካል እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡ መንገዱ የተዘጋውም በግጭት ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ወደ አሰብ #አስክሬን ጭኖ የሚያልፍ መኪና ማየታቸውንም አክለዋል፡፡

የሚመለከተው አካል ጉዳዩን አጣርቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸውና የተፈጠረውን ችግር እንዲያስረዳቸውም ጠይቀዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም ቢሆኑ ግጭት መፈጠሩን ያረጋገጡልን ሲሆን ተፈጠረ ባሉት ግጭትም 7 ሰዎች ሞተዋል፤ 3 ሰዎች ደግሞ በህይወት እና በሞት መካከል ናቸው ብለዉናል፡፡ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ... የተኩስ ልውውጡ የነበረው ከሚሊኒየም አዳራች በሰንሻይን በኩል ወደ ቦሌ መድኃኒዓለም በሚያስወጣው መንገድ ነበር " - የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ቦሌ በፖሊስ እና ፋኖ አባላት መካከል የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚሊኒየም አዳራሽ ጎን በሰንሸይን ቪላ ቤቶች አድርጎ ወደ ቦሌ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ወደ ሚያስወጣው መንገድ ላይ እንደነበር በአካባቢው የነበሩ…
#Update

በአዲስ አበባ ከተሞ ቦሌ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቀናት በፊት መገደላቸው የተነገረው የፋኖ አባላት ወላጆች የልጆቻቸው አስከሬን እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግረዋል።

ይህ የተናገሩት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጡት ቃል ነው።

ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለት የተገደሉት ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው ከሞቱ አራተኛ ቀናቸውን ቢያስቆጥሩም አስከሬናቸውን እስካሁን ማግኘት እንዳልቻሉ እናቶቻቸው ገልጸዋል።

እናቶቹ የልጃቸውን አስከሬን ለማግኘት እታች ላይ እያሉ እንደሆኑ አመልክተዋል።

እናቶቻቸው ምን አሉ ?

ወ/ሮ ሐረገወይን አዱኛ (የናሁሰናይ አንዳርጌ እናት) ፦

" ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አምርቼ ነበር። ጉዳዩን የሚያየው የፌደራል ፖሊስ ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አስከሬን እንዲሰኝ የማመልከቻ ደብዳቤ ያስገባሁ ሲሆን ይህ ነው የሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ አልተሰጠኝም።

' ይሄንን ጉዳይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነበር እኮ መመለስ የነበረበት፤ ለምንስ እዚህ ድረስ መጣችሁ ? ' ነው የተባልኩት።

ዛሬ ደግሞ እንደገና ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ሄጄ የሚሉኝን እሰማለሁ።

ከባድ ነው ለእናት፤ በጣም ከባድ ከሚገባው በላይ። አስከሬን ነው የጠየቅኩት፤ ግድ ስለሆነ ምላሹን ለማግኘት ያው በተስፋ እየጠበቅኩ ነው። ምላሹንም ከመልካም ነገር ጋር እጠብቃለሁ። "

 ወ/ሮ ኤልሳ ሰለሞንም (የአቤነዘር አባተ እናት) ፦

" ልጄ በተገደለ ማግስት ነው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት አስከሬን ለማግኘት ውጣ ውረድ ገጥሞኛል።

ያሳዝናል ፤ ህጻን ነው ደግሞ። አንድ ልጄን ምን ላድርግህ ? ከባድ ነው።

ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አቅንቼ ኃላፈውን እና ኮሚሽነሩን አግኝቼ ማናገር ባልችልም በዚያው የሚሠሩ ሠራተኞች ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራል ፖሊስን ነው የሚል ምላሽ ነው የሰጡኝ።

የፌደራል ፖሊስ ትላንት ምላሽ አልሰጠኝም ዛሬ ተመልሼ እሞክራለሁ።

ጳውሎስ ሆስፒታል አምርቼ የልጄ ስም ዝርዝሩ ውስጥ እንዳለ ከተነገረኝ በኋላ ከፖሊስ ትዕዛዝ ማምጣት እንዳለብኝ ተገልጾልኛል። "

ፖሊስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

ወላጆቻቸው የልጆቻቸውን #አስክሬን እስካሁን አለመቀበላቸውን በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ተጠይቀው ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃው እንደሌላቸው እና ይሄን የሚመለከተው የፀጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይል ወይም የፌደራል ፖሊስን እንደሆነ ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጄላን አብዲ ደግሞ ፥ " ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሆነ " ገልጸዋል።

የፋኖ አመራር ነው የተባለው ናሁሰናይ አንዳርጌ እንዲሁም እንዲሁም አቤነዘር ጋሻው ባለፈው ሳምንት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደላቸውን ሌላኛው የፋኖ አባል ሀብታሙ አንዳርጌ ምንም ሳይሆን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia