TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዛሬ ውይይት‼️

በየቤታችሁ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ተወያዩ!!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍፁም ባልተለመደ መልኩ በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች ግጭቶችን እያስተዋልን ነው። አንዳንዶቹ ከተማዎችማ ጭራሽ በግጭት ስማቸው ተነስቶ የማያውቅ እና በአስተማማኝ ሰላማቸው የተመሰከረላቸው ናቸው። ግጭቶቹን ከጀርባ ሆኖ የሚመራ አካል እንዳለም መንግስት በተደጋጋሚ ገልጿል። ግጭቶቹ ካለፉ በኃላም ዜጎች ድጋሚ ተመሳሳይ ነገር እንዳይከሰት ዘውትር እንደሰጉ ነው።
.
.
ዛሬ የምንወያየው ግን አሁን አሁን እየተስተዋለ ያለውን የሞራል ዝቅጠት ነው። ግለሰቦች በተጣሉ ቁጥር #ብሄራቸው ምንድነው?? ምን እና ምን #ብሄር ነው የተጣሉት? ተብሎ መጠየቅ ተጀምሯል። ይህ በእንዲህ ከቀጠለ ሀገሪቷን የማትወጣው ችግር ውስጥ እንከታታለን። ግለሰቦች እንደግለሰብ መፈረጅ እና መዳኘት ሲገባቸው የብሄር ተወካይ አድርጎ እርስ በእርስ ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም።

እናተስ በዚህ ጉዳይ ምን ትላላችሁ??
@tsegabwolde @tikvahethiopia