TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባልደራስ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሩ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በባህር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

ፓርቲው አመራሩ በአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ነው ያመለከተው።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከጥቂት ወራት በፊት ከረጅም ጊዜ እስር መለቀቃቸው የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#ባልደራስ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ማሳለፉን ፓርቲው ገልጿል።

ፓርቲው አመራሩ ለ40 ቀናት በግፍ እንደታሰረበት ገልጾ በ100 ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ እንደተወሰነለት አመልክቷል።

የአቶ ስንታየሁ ቸኮልን ፤ መፈታት እውን ለማድረግ ፓርቲው የዋስትናውን ገንዘብ/ ክፍያ ለማስፈፀም በሂደት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጉባኤው በተያዘለት እቅድ መሰረት ይደረጋል " - ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንቱ አቶ አምሀ ዳኜው መፈታታቸውን አሳውቋል። " አቶ አምሀ ዳኘው ከነበሩበት አፈና ተለቀዋል " ሲል ፓርቲው ገልጿል። ፓርቲው ትግሉን እንደሚቀጥል እና የነገው ጉባኤ በተያዘለት እቅድ መሰረት የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል። የባልደራስ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አምሀ…
#ባልደራስ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርግ መከልከሉ አስታውቋል።

ፓርቲው ምንም እንኳን አዲስ አበባ በሚገኘው " ጋምቤላ ሆቴል " ጉባኤ ለማድረግ ፍቃድ ቢያገኝም በፀጥታ እና ደህንነት ኃይሎች በተፈጠረ ጫና ጉባኤውን ማድረግ ሳይችል መቅረቱን ገልጿል።

ፓርቲው ለሆቴሉ ክፍያ ለመፈፀም ከከንቲባ ፅ/ቤት የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ የተፃፈ የፍቃድ ወረቀት ለሆቴሉ ቢያሳይም ቀደም ብሎ " ከኦሮሚያ ፖሊስ መጥተው ስብሰባው እዚህ እንዳይካሄድ አስፈራርተውኛል " ስትል ምክትል ስራ አስኪያጇ መናግሯን ገልጿል።

" ማስፈራራት ህጋዊ አይደለም፣ ተቀባይነትም የለውም ፤ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ህጋዊ ወረቀት አለን ፤ ከምርጫ ቦርድም ህጋዊ ወረቀት ይዘናል አስተናግዱን " በሚል ፓርቲው ለሆቴሉ ጥያቄ ቢያቀርብም ምክትል ስራ አስኪያጇ ከኦሮሚያ ፖሊስ ባለፈው የደህንነት ኃይሎችም እየመጡ እያስፈራሩኝ ስለሆነ ክፍያ መፈፀም አትችሉም የሚል ምላሽ እንደሰጠች ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወኪሎች በስፍራው ተገኝተው የነበረውን ሁኔታ መታዘባቸውን ፓርቲው ገልጿል።

ባልደራስ ፓርቲ ትላንትም ምክትል ፕሬዜዳንቱ ታስረው መለቀቃቸውን አስታውሶ ዛሬ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ የምስክር ወረቀት እንዳያገኝ ከፍተኛ ጫና ስለተደረገበት ጉባኤውን ማድረግ አለመቻሉን አሳውቋል።

ጫና ሲደረግ የነበረው ትላንትን ጨምሮ ጉባኤውን ለማድረግ በነበረው ሂደት ውስጥ እንደሆነ የገለፀው ባልደራስ " እንዲህ ታፍነን አንቀጥልም እንዲህ ያሉ አፈናዎችን ሰብረን ለመውጣት ትግላችን ይቀጥላል ፤ በዚህ ተሰናክሎ እና ተደናቅፎ የሚቀር ኃይል የለም " ብሏል።

ፓርቲው ዛሬ የተከላከለውን ጠቅላላ ጉባኤውን በመመካከር በቀጣይ ቀስ ብሎ እንደሚያደርግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ባልደራስ

ከዚህ ቀደም ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ ተከልክሎ እንደነበር የገለፀው ባለደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዛሬ ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጓል።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ፥ አቶ አምሃ ዳኜው ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።

አቶ አማሃ ዳኜው ፤ ፓርቲውን በም/ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ ነበሩ። ዛሬ በአብላጫ ድምፅ አቶ ለቀጣይ 3 አመታት በፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ #ሀገራዊ_ፓርቲ ለመሆን ውሳኔ አሳልፏል።

ባልደራስ ፓርቲ ፤ ምንም እንኳን ኢትዮጵያዊ ሀሳቦችን እያነሳው የታገልኩኝ ቢሆንም ባለኝ ፍቃድ መሰረት ግን መንቀሳቀስ የቻልኩት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው ብሏል።

የዛሬው ጉባኤ ፓርቲው ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን የሚያስፈልጉ ቅድመ ተግባራትን እያከናወነ እንዲቆይ እና ከወራት በኋላ በሚደረገው ጉባኤ ወደ ሀገር አቀፍነት እንዲያድግ ያለ ተቃውሞ እና ድምፀ ታቅቦ መፅደቁ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላላ ጉባኤው ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ከውህደት-መለስ አብሮ እንዲሰራ ፈቅዷል።

ነገር ግን ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት የፓርቲው ምክር ቤት እንዲወስን ጉባኤው ፍቃድ ሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት መርምሮ እና አጥንቶ ለፓርቲው ምክር ቤት እንዲያቀርብ፤ እንዲሁም ም/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ የሚያቀርብለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንዲያፀድቅ ወስኗል።

መረጃው ከፓርቲው ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia