TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

" ኢንፎኔት ኮሌጅ " ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን ሙሉ የትምህርት ማስረጃ እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያስረክብ የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳሰበ።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ " ኢንፎኔት ኮሌጅ " በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በቴ/ሙ ዘርፍ እውቅና ፍቃድ በማግኘት ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ነገር ግን ኮሌጁ በባለስልጣኑ የእውቅና ፍቃድና እድሳት መመሪያ መሰረት ህጋዊ የቤት ኪራይ ውል ማቅረብ ባለመቻሉ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ #ፍቃድ_የሌለውና ፍቃዱም በባለስልጣን መ/ቤቱ #መሰረዙን ሚያዝያ 12/2014ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ እንዳሳወቀው አመልክቷል።

" ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና እየሰጠ አለመሆኑን " በቀን 11/11/2015 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ ቁጥር ኢንፎ/2910/15 ገልፀውልናል " ያለው መ/ቤቱ  ኮሌጁ ቀደም ሲል እውቅና ፍቃድ በነበረው ወቅት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን ሙሉ የትምህርት ማስረጃ እስከ ነሐሴ 17 / 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያስረክብ ቀነ ገደበ አስቀምጠናል ብሏል።

ኮሌጁ በተቀመጠው ጊዜ ይህን መፈፀም ካልቻለ በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርገውም ባለስልጣን መ/ቤቱ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ፈተናው በ3 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ16 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ነገ አርብ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም. ለፈተና ይቀመጣሉ። ይህን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ11ዱ…
#Update

" ' ፈተና አለ ' ተብለን ስንገላታ ከዋልን በኃላ ' ቀርቷል ' አሉን " - የመንግሥት ሰራተኞች

" ፈተናው በመሰረዙ #ይቅርታ እንጠይቃለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለመንግሥት ሰራተኞች ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና አለመሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል።

ቅሬታቻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የአስተዳደሩ ሰራተኞች " ፈተና አለ " ተብለው ቀኑን ሙሉ ሲንከራተቱ ከዋሉ በኃላ " ፈተናው ቀርቷል " መባላቸውን ገልጸዋል።

ሰራተኛው ይሰጣል የተባለውን ፈተና ሲጠባበቅ ከዋለ በኃላ አንድም ግልፅ ምክንያት ሳይነገር አመሻሽ ላይ " ቀርቷል " መባሉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

" ለተፈጠረው መጉላላትና የስነልቦና ጉዳት ማነው ተጠያቂው ? " ሲሉም ጠይቀዋል።

ፈተናው ለምን እንደቀረ በይፋ የተሰጣቸው ማብራሪያ እንደሌለ ሰራተኞቹ አክለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ለ " ካፒታል ጋዜጣ " ቃላቸው የሰጡ የመንግሥት ሰራተኞች በመፈተኛ ቦታቸዉ ተገኝተው ሳይፈተኑ ለረዥም ሰዓታት በፌዴራል ፖሊስ መጠበቃቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ 4 እና 5 ኪሎ ለመፈተን ወደ ተቋሙ ከ6:30 ጀምሮ በተመደቡበት መፈተኛ ክፍል ቢደርሱም እስከ ቀን 11:30 ድረስ ከፌዴራል ፖሊስ በስተቀር ማንም ፈታኝ ባለመምጣቱ ከረዥም ሰዓታት እንግልት በኃላ እንዲበተኑ ተደርገዋል።

በቅርቡ ለሚተገበረዉ የሰራተኞች ድልድል ሲባል ከ14 ሺህ በላይ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች ለፈተና እንደሚቀመጡ መነገሩ ይታወቃል።

- የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር፣ 
- ቤቶች ልማት እና አስተዳደር፣
- ትራንስፖርት፣
- ፐብሊክ ሰርቨሲ እና ሰው ሀብት ልማት፣ 
- ፕላን እና ልማት፣ 
- ሥራ እና ክህሎት፣
- ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮዎች
- ቤቶች ኮርፖሬሽን ጨምሮ አጠቃላይ ከ13 ሺህ በላይ ሰራተኞች ፈተናዉን አልወሰዱም።

በወቅቱ ረዥም ሰዓታት ፈተናዉን በመጠባበቃቸዉ ምክንያት የጩኸት ድምፅ ያሰሙ ሰራተኞች ለእስር መዳረጋቸውን እና የተለያዩ እንግልቶች እንደደረሰባቸው ለጋዜጣው ተናግረዋል።

በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ፈተናው ወደሌላ ቀን መራዘሙን እንደሰሙ ሰራተኞቹ ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ መሆኑ መነገሩ ይታወሳል።

ተጨማሪ . . .

የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ምዘና ፈተናውን እንደሚያዘጋጁ ከተገለፁት ሁለት ተቋማት አንደኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው #መሰረዙን በደብዳቤ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ፦
* ለአመራሮች፣
* ባለሙያዎች
* ሰራተኞች ፈተና እንዲሰጥ ኃላፊነት እንደተሰጠ አስታውሷል።

ሆኖም በተከሰተ " የፈተና ቴክኒካዊ ችግር " ምክንያት በ12/04/2016 ዓ.ም ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ፈተና መሥጠት እንዳልተቻለ ከይቅርታ ጋር ገልጿል።

የተዘጋጀው ፈተና ደህንነት ችግር ያላጋጠመው መሆኑን ግን አመልክቷል።

በማንኛውም በጋራ በመስማማት ቀን ይሄንኑ ፈተና ለመሥጠት እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባገኘው መረጃ አስተዳደሩ ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቅርብ ያሳውቃል።

@tikvahethiopia