TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድራማዊና አሳዛኝ ሂደቶችን አስተናግዶ ተጠናቋል አለ ፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ስፖርት ክለብ፤ ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁም ተከታዩን መረጃ አሰራጭቷል፦

"የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ሽሬን ገና በ5ኛው ደቂቃ መምራት ቢጀምርም በደጋፊዎቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት ውጥረት ላይ የገቡት ተጫዋቾቻችን በጥንቃቄ በመጫዎት መሪነታቸውን ቢያስጠብቁም በ70ኛው ደቂቃ #ጥፋት ተሰርቷል በማለት በፍፁም ጨዋታውን ካስጀመሩ በኃላ ፍፁም ቅጣት ምት የሰጡብን ሲሆን ከጎሉ መቆጠር በኃላ በደጋፊዎቻችን ላይ በደረሰው የድንጋይ ውርዋሮ ብዛት ያላቸው ደጋፊዎች #ጉዳት በማስታገሳቸው ጨዋታው ለበርካታ ደቂቃዎች ተቋርጦ የጀመረ ሲሆን በዛው 1ለ1 ተጠናቋል።"

በሌላ በኩል፦ ቡድኑ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው መረጃ እስካሁን ድረስ ደጋፊዎቼ ከስታዲየሙ #ሊወጡ አልቻሉም ብሏል።

የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ
🗞ቀን ሰኔ 30/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia