TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከተጠቀሱት የባንክ አማራጮች ወደ M-PESA በመላክ እስከ 50 ብር ስጦታ እንፈስ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
#ጠብታ_አንቡላንስ

በድንገተኛ እንዲሁም መጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዘርፍ የሚታወቀው ጠብታ አንቡላንስ በአዲስ አበባ ለሚገኙ 10 ትምሀርት ቤቶች በዚህ ዓመት የመንገድ ደኅንነት እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በሁለት ትምህርት ቤቶች ሥራውን በይፋ የጀመረው ተቋሙ ተማሪዎችን ስለድንገተኛ ህክምና ማስተማር እንዲሁም ሞያዊ ልምድ እና መነቃቃት በመፍጠር ማብቃትን ዓላማው አድርጎ የተቀረጸ ፕሮጀክት መሆኑን የጠብታ አንቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethmagazine/21985?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 480 ስደተኞች #በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ ተይዘዋል " - IOM ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 480 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መያዛቸው ተነግሯል። የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት/IOM ሰኞ'ለት ባወጣው መግለጫ 480 ስደተኞች በባህር ላይ ጠባቂዎች መያዛቸውን አስታውቋል። ድርጅቱ "ከመጋቢት 24 እስከ 30,2024 ውስጥ 480 ስደተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል " ነው ያለው። ከተያዙት…
#ሊቢያ #ግሪክ

እንደ ጣሊያን የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መረጃ ፥ ባለፈው ሳምንት የሜዲትሬንያን ባሕርን አቋርጠው ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በመሞከር ላይ የነበሩ ፍልስተኞች ጀልባቸው ተገልብጦ 1 ህጻንን ጨምሮ 9 ሰዎች ሞተው አስክሬናቸው ተገኝቷል።

15 የሚሆኑ ፍልሰተኞች የደረሱበት አይታወቅም። 22 ሰዎችን ደግሞ መታደግ ተችሏል።

ከላምፔዱሳ ደሴት 50 ኪ.ሜ. ላይ ማዕበል በማየሉ ነው አደጋው የደረሰው። ላምፔዱሳ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚሞክሩ ፍልሰተኞች የመጀመሪያ ማረፊያ ነች፡፡

በሌላ በኩል ፤ ባለፈው ሳምንት ግሪክ የ3 ታዳጊዎችን አስከሬን ስታገኝ ፤ 19 ፍልሰተኞችን ደግሞ ታድጋለች።

ፍልሰተኞቹ ይጓዙበት የነበረው ጀልባ ከቋጥኝ ጋራ በመጋጨቱ አደጋው ሊደርስ የቻለው።

ግሪክ ከአፍሪካ፣ እስያ እና መካከለኛው ምሥራቅ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚሹ ፍልሰተኞች አማራጭ ናት።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚዲያ የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) እንዴት አቀጣጠለ ? በ100 ቀናት ከ800,000 እስከ 1,000,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎች ባለቁበት የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው። እንዴት ? - ራዲዮ-ቴሌቭዥን ሊብሬስ ዴስ ሚልስ ኮሊንስ (RTML) እንዲሁም መንግታዊው ' ሬድዮ ሩዋንዳ ' በቱትሲዎች ላይ በመላ ሀገሪቱ ጥላቻ እንዲፈጠርና የሩዋንዳ…
#Kwibuka

" ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " - ፖል ካጋሜ

ከ30 ዓመታት በፊት በሩዋንዳ በ100 ቀናት ብቻ እስከ 1,000,000 ሚደርሱ ሰዎች የተጨፈጨፉበት የሩዋንዳ ዘር ፍጅት እየታሰበ ይገኛል።

የዘር ፍጅቱ የተፈፀመበትን 100 ቀናት ታሳቢ በማድረግ ከሚያዚያ 7 (እ.ኤ.አ) አንስቶ ለ100 ቀናት የዘር ጭፍጨፋው ሰለባዎች ይታሰባሉ ፤ ይህም ኪውቡካ /Kwibuka/ ይባለል።

ከሳምንት በፊት በኪጋሊ በነበረ ስነስርዓት ላይ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፤ ከዘር ፍጅቱ በህይወት የተረፉ ዜጎች ለብሄራዊ አንድነት ሲሉ ስላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

" እጅግ የሚከብደውን የእርቀ ሰላም ሸክም እናተ እንድትሸከሙ ጠየቅናችሁ እንሆ ለሀገራችን ስትሉ ይሄንን በየቀኑ ማድረጋችሁን ቀጥላችኃል ስለዚህ እናመሰግናችኃለን " ነው ያሉት።

ፖል ካጋሜ ፥ አሁንም ድረስ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት #የጎሳ_ፖለቲካ እየተባባሰ መሄዱን እና የብሄረሰብ ማጽዳት አደጋ መደቀኑን በማንሳት አስጠንቅቀዋል።

" ሩዋንዳ ውስጥ የደረሰው መከራ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል። ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " ብለዋል።

ሩዋንዳ መከራ ውስጥ በገባችበት ጊዜ በርካታ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ልጆቻቸውን ሩዋንዳ መላካቸውን እና እነዛም ወታደሮች ለሩዋንዳ እንደደረሱላት ገልጸዋል።

" ነገር ግን #በጥላቻም ይሁን #በፍራቻ ያልደረሰልን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ በወቅቱ በነበረው የሁቱ መንግሥት መሪነትና የሁቱ ብሄረሰብ አባላት በሆኑ ጽንፈኛ አክራሪዎች እንዲሁም በመንግሥት በሚደገፈው የ " ኢንተርሀምዌ '  ሚሊሻ አማካኝነት እስከ 1,000,000 ቱትሲዎች ፣ ለዘብተኛ ሁቱዎችና ትዋዎች ተጨፍጭፈዋል።

Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
AP / VOA

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Genocide

የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) እንዳይፈጸም በመከላከል እና ሲፈጸምም በማስቆም ላይ የሚሰራው ተቋም " የጄኖሳይድ ዎች " ባደረገው ምርምር የሰው ልጆች ልባቸው ሲደድር የሚጠናወታቸው የዘር ጭፍጨፋ አባዜ 8 ደረጃዎች አሉት።

እነዚህም #በተደራጀ እና #ተቋማዊ በሆነ መንገድ የሚፈጸሙት ናቸው።

ደረጃዎቹ :-

1ኛ. መከፋፈል (Classification) - እኛና እነርሱ ብሎ በመከፋፈል ለየት ይላሉ ተብለው ሚታሰቡትን የኅብረተሰብ ክፍሎች #በቀልድም_ጭምር በማንቋሸሽ በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት አለማክበር።

2ኛ. የሚታይ መገለጫ መስጠት (Symbolization) - ይህ የጥላቻ ግልጽ መገለጫ ሲሆን ይሁዲዎች በናዚ ጀርመን ቢጫ ኮከብ ያለበት ልብስ እንዲለብሱ እንደተደረገው ነው፡፡

3ኛ. ከሰው ክብር ዝቅ ማድረግ (Dehumanization) - ይህ ተግባር ከራስ የተለዩትን ሰብዓዊ ክብርም ሆነ መብት በመንፈግ ይፈጸማል፡፡ በሩዋንዳ አክራሪ ሁቱዎች የቱትሲ ዘውግ ተወላጆችን " #በረሮ#እባብ " ይሏቸው እንደነበረው መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሂደት ገዳዮቹ ' እየገደልን ያለነው ሰው አይደለም፤ ታዲያ ድርጊታችን ምኑ ላይ ነው ጥፋትነቱ ? ' እንዲሉ መንገዱን ይጠርግላቸዋል፡፡

4ኛ. ማደራጀት (Organization) - በጥላቻ ላይ የተመሠረቱ መንግሥታት አንድን ሕዝብ የሚያጠፋላቸውን ኃይል #ያሰለጥናሉ፡፡

5ኛ. በተቃራኒ ጎራዎች ማሰለፍ (Polarization) - ሕዝቡ በዘውጉ ከጨፍጫፊው እና ከተጨፍጫፊው ወገን ሚናውን እንዲለይ ይደረጋል፡፡ በብዛት ይህ የሚሆነው በጥላቻ ቡድኖች ውትወታ በመገናኛ ብዙሃን የጥላቻውን መርዝ በመርጨት ነው፡፡ አንዱን ዘውግ ከሌላው ለይቶ በማውጣት " ጠላት ነው " ብሎ ማወጅ ፤ ይህ የገዳዩን ዘውግ አባላት በቀላሉ ለማሳመንና ለህሊናው እንዲቀለው ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።

6ኛ. ዝግጅት (Preparation) - ሰለባዎቹ በልዩነቶቻቸው ተለይተው ይፈረጃሉ፡፡ የጭፍጨፋው ንድፍ አውጭዎች ሰዎችን በመኖሪያ አድራሻቸውና በሌሎችም መለያዎች ይፈርጁና ለፍጅት ያዘጋጇቸዋል፡፡

7ኛ. ፍጅት (Extermination) - በታቀደና ሆነ ተብሎ በተመቻቸ ዘመቻ የጥላቻ ቡድኖቹ ሰለባዎቻቸውን ይጨፈጭፋሉ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በዘር ፍጅት ማንነታቸውን መለየት እስኪከብድ ድረስ ተጨፍጭፈዋል፡፡

8ኛ. ክህደት (Denial) - ግድያውን የፈጸሙትም ሆኑ ቀጣይ ትውልዶች ምንም ዓይነት ጥፋት ያልተፈጸመ በማስመሰል ክህደት ይፈጽማሉ፡፡

ከዚህ የጭፍጨፋ ሂደት እንደምንረዳው የዘር ፍጅት በአንድ ሌሊት ያለምንም ዝግጅት ስለማይፈጸም ራሳችንን ከላይ ከተጠቀሱት በሌላው ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ከስተቶች ፈጽሞ ማራቅና የዕለት ከዕለት ድርጊቶቻችንን መገምገምም ያሰፈልገናል።

እነዚህን የዘር ፍጅት አመላካች ሂደቶች በማናቸውም ደረጃ በእንጭጩ መቅጨት ከተቻለ የከፋ እልቂትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ይችላል።

ሁቱትሲ
ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛና ስቲቭ ኤርዊን
በመዘምር ግርማ

#Rwanda2024 #Kwibuka #Remembering

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
2016 ዓ/ም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ራያ

“ ሕወሓት /TPLF ወረራ ፈጽሟል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ” - አቶ ሀይሉ አበራ

የትግራይ እና አማራ ክልሎች የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ አካቢዎች ሰሞኑን በተለይ ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአላማጣና አካባቢው ባለስልጣናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአላማጣ ከተማ እና ዙሪያው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የትግራይ ታጣቂዎች በስናይፐርና ሌሎች መሳሪያዎች የታገዘ ተኩስ ተከፍቶብናል ” ብለዋል።

አክለውም፣ “ ባለፈው ጦርነት በደረሰብን ሀዘን እንባችን አልደረቀም። መንግሥት ግን እስከመቼ ድረስ ነው የዚህን አካባቢ ችግር የማይቀርፈው ? ነው ወይስ ሕዝቡ እርስ በእርሱ እንዲተላለቅ ነው የፈለገው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

“ ወያኔ የኔ ናቸው የሚላቸው የአላማጣና አጠገቡ አካባቢዎች በሙሉ የአማራ እንጂ የትግራይ መሬት ሆነው አያውቁም። ደማችን ይፍሰስ እንጂ መሬታችንን አንለቅም። መንግሥት የትግራይ አመራሮችን ይዳኝልን ” ብለው፣ በንጹሐንና በንብረት ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረ፣ አሁን ግን ትክክለኛውን ቁጥር ለመግለጽ ለጊዜው እንደሚያስቸግር አስረድተዋል።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ የአላማጣና አካባቢው አመራር በሰጡት ቃል፣ “ ወያኔ ሰሞኑን በሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን ተቆጣጥሯቸው ከነበሩ ቦታዎች በተጨማሪ ተቆጣጥሯል። አርሚ 24 ነው ተኩስ የከፈተብን ” የሚል አጭር ቃሎ ሰጥተው ሁነቱን በሂደት እንደሚገልጹ ጠቁመዋል።

በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለግጭቱ ሁኔታ፣ የደረሰው ጉዳት ምን እንደሚመስል አላማጣ ከተማን በከንቲባነት እያስተዳደሩ ለሉትና የወሎ ራያ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለሆኑት አቶ ሀይሉ አዱኛ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፥ “ ሕወሓት ወረራ ፈጽሟል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል። ፍላጎታቸውን በኃይል ለመፈጸም እየሞከሩ ነው። ሂደቱ በዋነኝነት ይህን ነወሰ የሚመስለው። ዝርዝር ገለጻ ነገ እሰጣለሁ ” ብለዋል።

ዝርዝር ምላሻቸው ነገ ይቀርባል።

🔵 በትግራይ በኩል ምን ተባለ ?

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለው አባል ፥ በትግራይ በኩል ነዋሪዎችን እና የመንግስት ሰዎችን ስለ ሁኔታው ጠይቋል።

ዛሬ ከሰዓት ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፥ " የራያ ጨርጨር ፣ የራያ አላማጣ ፣ ኮረም ኦፍላና ዛታ አከባቢ ያሉ ቀበሌዎች ከታጣቂዎች ነፃ ሆነዋል " ብለዋል።

አጠቃላይ በርካታ ስፍራዎች ቦታውን ይዘው ከነበሩ ታጣቂዎች ነጻ ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።

በከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ምክንያት ከአካባቢው የወጡ ነዋሪዎችም አሉ ሲሉ ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን የፕሪቶሪያው ስምምነት ተከብሮ የአማራ ታጣቂዎች ከአካባቢው ሊወጡ የተፈናቀለው ህዝብም ወደ ቦታው ሊመለስ ይገባል ብለዋል።

ትናንትና ወደ ራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ካልኣዩ ግደይ ደውለን የነበረ ሲሆን መጠነኛ ግጭት እንደነበረ ተናግረዋል።

ዛሬ በሰጡት ቃል ደግሞ ፥ " በወረዳው በአማራ ታጣቂዎች ሰር የነበሩት ሁለት ቀበሌዎች ነፃ ወጥቷል " ብለዋል።

ሌሎች የክልሉን ኃላፊዎች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

የትግራይና አማራ ክልሎች ይገባኛል በሚያነሱበት በራያ አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የግጭት ሁኔታዎች ይታዩ እንደነበር በሁለቱም በኩል ያሉ የመንግስት አካላትን በማነጋገር መረጃ ማድረሳችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዲሱን የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ደንበኞች እንዴት ወደ አዋጭ አካውንት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ?
ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
#BankofAbyssina #mobilebanking #boamobile #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#ራያ “ ሕወሓት /TPLF ወረራ ፈጽሟል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ” - አቶ ሀይሉ አበራ የትግራይ እና አማራ ክልሎች የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ አካቢዎች ሰሞኑን በተለይ ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአላማጣና አካባቢው ባለስልጣናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የአላማጣ ከተማ እና ዙሪያው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የትግራይ…
#Update #Raya

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " በደቡብ ትግራይ እና በሌሎች በኃይል በተያዙ የትግራይ ግዛቶች የተፈጠረው ክስተት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት (TPLF) አልያም በትግራይ እና በአማራ ክልል አስተዳደሮች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም " ብለዋል።

ይህ ሁለቱ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ፈራሚ ወገኖች " ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የሆኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ... የተኩስ ልውውጡ የነበረው ከሚሊኒየም አዳራች በሰንሻይን በኩል ወደ ቦሌ መድኃኒዓለም በሚያስወጣው መንገድ ነበር " - የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ቦሌ በፖሊስ እና ፋኖ አባላት መካከል የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚሊኒየም አዳራሽ ጎን በሰንሸይን ቪላ ቤቶች አድርጎ ወደ ቦሌ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ወደ ሚያስወጣው መንገድ ላይ እንደነበር በአካባቢው የነበሩ…
#Update

በአዲስ አበባ ከተሞ ቦሌ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቀናት በፊት መገደላቸው የተነገረው የፋኖ አባላት ወላጆች የልጆቻቸው አስከሬን እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግረዋል።

ይህ የተናገሩት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጡት ቃል ነው።

ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለት የተገደሉት ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው ከሞቱ አራተኛ ቀናቸውን ቢያስቆጥሩም አስከሬናቸውን እስካሁን ማግኘት እንዳልቻሉ እናቶቻቸው ገልጸዋል።

እናቶቹ የልጃቸውን አስከሬን ለማግኘት እታች ላይ እያሉ እንደሆኑ አመልክተዋል።

እናቶቻቸው ምን አሉ ?

ወ/ሮ ሐረገወይን አዱኛ (የናሁሰናይ አንዳርጌ እናት) ፦

" ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አምርቼ ነበር። ጉዳዩን የሚያየው የፌደራል ፖሊስ ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አስከሬን እንዲሰኝ የማመልከቻ ደብዳቤ ያስገባሁ ሲሆን ይህ ነው የሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ አልተሰጠኝም።

' ይሄንን ጉዳይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነበር እኮ መመለስ የነበረበት፤ ለምንስ እዚህ ድረስ መጣችሁ ? ' ነው የተባልኩት።

ዛሬ ደግሞ እንደገና ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ሄጄ የሚሉኝን እሰማለሁ።

ከባድ ነው ለእናት፤ በጣም ከባድ ከሚገባው በላይ። አስከሬን ነው የጠየቅኩት፤ ግድ ስለሆነ ምላሹን ለማግኘት ያው በተስፋ እየጠበቅኩ ነው። ምላሹንም ከመልካም ነገር ጋር እጠብቃለሁ። "

 ወ/ሮ ኤልሳ ሰለሞንም (የአቤነዘር አባተ እናት) ፦

" ልጄ በተገደለ ማግስት ነው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት አስከሬን ለማግኘት ውጣ ውረድ ገጥሞኛል።

ያሳዝናል ፤ ህጻን ነው ደግሞ። አንድ ልጄን ምን ላድርግህ ? ከባድ ነው።

ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አቅንቼ ኃላፈውን እና ኮሚሽነሩን አግኝቼ ማናገር ባልችልም በዚያው የሚሠሩ ሠራተኞች ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራል ፖሊስን ነው የሚል ምላሽ ነው የሰጡኝ።

የፌደራል ፖሊስ ትላንት ምላሽ አልሰጠኝም ዛሬ ተመልሼ እሞክራለሁ።

ጳውሎስ ሆስፒታል አምርቼ የልጄ ስም ዝርዝሩ ውስጥ እንዳለ ከተነገረኝ በኋላ ከፖሊስ ትዕዛዝ ማምጣት እንዳለብኝ ተገልጾልኛል። "

ፖሊስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

ወላጆቻቸው የልጆቻቸውን #አስክሬን እስካሁን አለመቀበላቸውን በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ተጠይቀው ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃው እንደሌላቸው እና ይሄን የሚመለከተው የፀጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይል ወይም የፌደራል ፖሊስን እንደሆነ ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጄላን አብዲ ደግሞ ፥ " ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሆነ " ገልጸዋል።

የፋኖ አመራር ነው የተባለው ናሁሰናይ አንዳርጌ እንዲሁም እንዲሁም አቤነዘር ጋሻው ባለፈው ሳምንት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደላቸውን ሌላኛው የፋኖ አባል ሀብታሙ አንዳርጌ ምንም ሳይሆን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“አጋቾቹ እያሰቃዩት ነው። ዱብ እዳ ወረደብኝ። ወደ 950 ሺሕ ጠይቀዋል። ልጄ ‘በአንድ መጋዘን ወደ 200 ሰዎች ታጎርን’ ነው የሚለው ” - የታጋች አባት በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ካሜራ ማን ሆኖ ሲሰራ ነበር የተባለው ወጣት አብርሃም አማረ #በሊቢያ በአጋቾች #ታግቶ በየቀኑ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ፣ አጋቾቹ ታጋቹን ወጣት ለመልቀቅ 950 ሺሕ ብር እንደጠየቁ፣ ይህን ገንዘብ ማሟላት እንዳልተቻለ የታጋች…
#Update

“ ለአጋቾቹ 700 ሺሕ ከከፈልኩ በኋላ እንደገና 400 ሺሕ ጠየቁኝ ” - በሊቢያ ልጃቸው የታገተባቸው አባት

በአዲስ አበባ ከተማ በካሜራ ማን የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ይሰራ የነበረው አብርሃም አማረ የተባለ ወጣት ሕይወቱን ለመለወጥ ወደ ውጭ እየተሰደደ በነበረበት ወቅት በሊቢያ በደላሎች እንደታገተባቸው፣ አጋቾቹ ልጁን ለመልቀቅ 950 ሺሕ ብር እንደጠየቋቸው የታጋች አባት አቶ አማረ ዓለም መግለጻቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት ዝርዝር መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

የታጋቹ አባት በወቅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ አጋቾቹ እያሰቃዩት ነው። ዱብ እዳ ወረደብኝ። ወደ 950 ሺሕ ጠይቀዋል። ልጄ ‘በአንድ መጋዘን ወደ 200 ሰዎች ታጎርን’ ነው የሚለው ” ማለታቸው አይዘነጋም።

አሁንስ የታጋቹ ጉዳይ ከምን እንደደረሰ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቶ አማረ ዓለምን ጠይቋል እሳቸውም ፥ “ ለአጋቾቹ ከ700 ሺሕ ከከፈልኩ በኋላ እንደገና 400 ሺሕ ጠየቁኝ ” ብለዋል።

“ ባለፈው ጎረቤቶች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ በጎ አድራጊዎች ተባብረው ገንዘብ ተሰባሰበልኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ብዬ ከታሰረበት ወጣልኝ። አሁን እንደገና ወደዚህ (ወደ ኢትዮጵያ) መመለስ አይችልም ተብሎ እንደገና 400 ሺሕ ብር ደግሞ ተጠይቀናል ” ሲሉ አክለዋል።

ከዚህ በፊትም በተገለጸው መሠረት አጋቾቹ ታጋቹን ለመልቀቅ እንዲላክላቸው ጠይቀው የነበረው 950 ሺሕ ነበር ቀንሰውላችሁ ነው 700 ሺሕ የላካችሁት ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፥ ቀንሰውልላቸው እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ከተጠየቁት 400 ሺሕ ብር ሲደመር ግን በአጠቃላይ ደላሎች የጠየቋቸው የገንዘብ መጠን ከ1 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ አስረድተዋል።

አሁን 400 ሺሕ ብሩን ላኩ የተባሉት ለምን እንደሆነ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ ' ልጁ ወደ ጣሊያን እንዲሻገር 'በሚል ሊቢያ እና ጣሊያን ያሉ ደላሎች ገንዘቡን እንደጠየቋቸው፣ ልጃቸው አሁን ትሪፓሊ ከተማ ውስጥ እንደሚገኝ ፣ ገንዘቡ ካልገባ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ልጃቸው ጭምር እንደነገራቸው ነው ያስረዱት።

ድጋሚ የተጠየቀውን 400 ሺህ ብር አሟልቶ ለመላክ 150 ሺሕ ብር እንደጎደላቸውም የታጋቹ አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአቶ አማረን ልጅ ጨምሮ በሊቢያ ታግቶ 1.7 ሚሊዮን ብር የተጠየቆበት፣ 800 ሺሕ ብር ለአጋቾቹ በመላኩ ይለቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ያለውን የሀዋሳውን ታጋች የጌድዮ ሳሙኤልን ጉዳይ ከጊዜ በኋላ በዝርዝር መረጃ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamhlyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ራያ “ ሕወሓት /TPLF ወረራ ፈጽሟል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ” - አቶ ሀይሉ አበራ የትግራይ እና አማራ ክልሎች የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ አካቢዎች ሰሞኑን በተለይ ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአላማጣና አካባቢው ባለስልጣናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የአላማጣ ከተማ እና ዙሪያው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የትግራይ…
#Update

አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊትና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን ከንቲባው አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውንም ገልፀዋል።

አቶ ኃይሉ አበራ ምን አሉ ?

- " ከትላንት ሰኞ ጀምሮ ከተማው በመከላከያ ሠራዊት እና ፌዴራይል ፖሊስ ስር ይገኛል። "

- " አላማጣ ከተማው መከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ነው ያለው። ዙሪያው የተያዘው ግን በትግራይ ታጣቂዎች ነው። "

- " የራያ አላማጣ ወረዳ እና የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከሰኞ ጀምሮ አካባቢውን ለቅቀው ወጥተዋል። በአሁኑ ሰዓት ቆቦ ነው የሚገኙት። "

- " አሁን እኛ እዚያ እየሠራን አይደለም። " 

አቶ ኃይሉ አበራ ፥ የራያ አላማጣ አካባቢዎች በአማራ ክልል ስር ከሆነ በኋላ በተመሠረው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የነበሩት ኃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት ከተማውን እያስተዳደሩ አይደለም ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሞላ ደርበው እና ለሌችም ሰዎች በትናንትናው ዕለት መገደላቸውን አቶ ኃይሉ አበራ ተናግረዋል።

" አቶ ሞላ ሕይወታቸው ያለፈው ከህወሓት ጋር በተያያዘ አይደለም። ሕግ የያዘው ነገር ስለሆነ ተጣርቶ የሆነ ነገር እስከሚባል ድረስ ዝርዝሩን አልገልፅም " ብለዋል።

ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በርካታ የአላማጣ ነዋሪዎች ወረዳውን እና ከተማውን ለቀው በመውጣት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሸሻቸውን ተነግሯል።

ነዋሪዎች ሸሽተውባቸዋል ከተባሉ አጎራባች አካባቢዎች አንዱ ቆቦ ከተማ ሲሆን አንድ የቆቦ ከተማ ኃላፊ ከትናትን ጀምሮ በርካታ ወደ ከተማዋ እየገቡ መሆኑን ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ያሉ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን " በተለይም የአለማጣ ከተማ ከትላንት ጀምሮ ከማንም ታጣቂ ነፃ ናት " ብለዋል።

" የአማራ ይሁን የትግራይ ታጣቂዎች በቦታው አለመኖራቸውን " ገልጸው ስጋት ያደረበት ነዋሪው ወደ አጎራባች አካባቢ መሄዱን አስረድተዋል።

እስካሁን በራያ ጉዳይ በአማራ እና በትግራይ ክልል ደረጃ እንዲሁም በፌዴራሉ መንግሥት በኩል የተሰጠ ማብራሪያም ሆነ አስተያየት የለም።

@tikvahethiopia