TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቄዶንያ❤️ 🔵 “ የጎዳና ኑሮ ከባድ ነው፣ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ” - የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ 🔴 “ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል ” - ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከመቄዶንያ በጎ…
#መቄዶንያ

“ ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” - መቄዶንያ

መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው እርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።

ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ “ በሰይፉ ኢቢኤስ የዩቱብ ቻነል ” ድጋፍ ማድረጊያ መርሀ ግብር ስለሚጀመር ደጋጎች ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ በአንጽንኦት ተጠይቋል።

ይህ የተባለው ዛሬ በመቄዶኒያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የመቄዶንያ መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ደግሞ፣ “ ይህን ህንፃ ጀምረነዋል። ለማጠቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” ብለዋል።

ህንፃው ምን የማጠቃለያ ስራዎች ቀርተውት ነው ድጋፍ ያስፈለገው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ ሴራሚክ የባኞ ቤት እቃዎች፣ 7 ሊፍቶች፣ የኤሌክትሪክ ፊኒሽንግ እቃዎች ገና ናቸው ” ሲሉ መልሰዋል።

በመቄዶንያ ምን ያክል የአእምሮ ህሙማን አሉ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ወደ 2,500 የአእምሮ ሆሙማን፤ ከ2,000 በላይ ዳይፐር ተጠቃሚዎች፣ ከዚያ ውጪ ያሉት አረጋዊያን ናቸው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ፣ “ በ44 ቅርንጫፍ ከ8,000 በላይ ሰዎች አሉ። በየጊዜው ሰው እየጨመረ ነው የሚሄደው። ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ጭምር ናቸው ያሉት ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከ8,000 በላይ ወገኖችን ከጎዳና በማንሳት በ44 ቅርንጫፎች በቀን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ሰብዓዊ ድጋፍ የሚረዳ ማዕከል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከ5 ሺህ በላይ ሰራተኞች ውላቸው እንዲቋረጥ መመሪያ ተሰጠ።

ጤና ሚኒስቴር በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ (USAID) ድጋፍ የተቀጠሩ ከ5 ሺህ በላይ ስራተኞችን ውል እንዲቋረጥ መመሪያ ሰጠ።

ጤና ሚኒስቴር ከአሜሪካ መንግሥት በሲዲሲ (CDC) ወይም ዩኤስኤይድ (USAID) አማካኝነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጃንዋሪ 24 ,2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ እንደደረሰው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተፈርሞ ለሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች የተሰራጨው ደብዳቤ " በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ የተቀጠሩ እና ተቋማችሁ ከCDC ወይም USAID ጋር በሚያደርገው ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኞችን በተመለከተ ስራ ላይ እንዲውል አሳስባለሁ " ይላል።

ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የደብዳቤውን #ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡን ተጨማሪ ማብራሪያ በመላው ሃገሪቱ በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ አማካኝነት በኮንትራት እያገለገሉ ያሉ ሰራተኞች ቁጥር 5 ሺህ እንደሚሻገር ገልጸዋል።

ሚንስትሩ " ሰው እንዲዘጋጅ ነው እንጂ የአሜሪካ መንግሥትም ሃሳቡን ሊቀይር ይችላል የተቀየረ ነገር ካለ የሚቀጥል ይሆናል አሁን ባለው ሁኔታ ግን ድጋፉን ካቋረጠ ሌላ መፍትሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

" ለዚህ ደግሞ ሰራተኞቻችን እንዲዘጋጁ ከመንግስት ጋርም ንግግር እየተደረገ ነው ያለው የመንግስት ሰራተኞች ስራውን እንዲያስቀጥሉ የCDC እና USAID ሰራተኞች ስራውን እንዲያቆሙ ተወስኗል " ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በዝርዝር ምን አሉ ?

" እኛን በዋናነት የሚመለከተን በጀቱ በቀጥታ በእኛ በኩል ስለሚመጣ የሲዲሲ ሰራተኞችን ነው ዩኤስኤይድ ግን ቅጥር የሚያከናውነው በራሱ በኩል ነው ውሉንም የሚያቋርጡት ራሳቸው ናቸው።

የአሜሪካ መንግሥት ሃሳቡን ቀይሮ ሌላ መረጃ የሚያስተላልፍ ከሆነ እኛም ሌላ መረጃ የምናስተላልፍ ይሆናል አሁን ባለው የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ግን ኮንትራታቸውን ማቋረጥ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ደብዳቤ አስተላልፈናል።

ከ5 ሺ በላይ ይሆናል ትክክለኛ ቁጥራቸውን ለማወቅ መረጃ የመሰብሰብ ስራ እየሰራን ነው ሁሉም በኮንትራት ናቸው ኮንትራታቸው በየአመቱ ይታደሳል ስራቸውም ከኤች አይ ቪ ጋር የተገናኙ ስለሆነ አብዛኞቹ የቆዩ ሰራተኞች ናቸው።

በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው ነበር በዚህ ያህል በጀት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረው 15 እና 20 ዓመት የሞላቸውም አሉ ስራው ላይ ችግር ሊያመጣ ይችላል።

በአንድ ጊዜ ይሄን ያህል ሰው ከሴክተሩ ከተቀነሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል ዋናው ነገር ግን ስራው እንዳይስተጓጎል ሃላፊነቱን ላለው የመንግስት ሰራተኛ እያስተላለፉ መሄድ ያስፈልጋል።

ቀላል ስራ አይደለም የሚጠብቀን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን።

የመጨረሻ ውሳኔዎችን አልሰማንም ከአሜሪካ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ውሳኔዎች እየተላለፈ ስለሆነ ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ ነው የሚባለው ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ተመሳሳይ ነገር ነው እያደረጉ ያሉት ከሁሉም ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅትም በቦርድ ደረጃ ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።

ሰራተኞችም እንዲያውቁ እኛም ጫናውን ለማሳወቅ እና መፍትሄው አብሮ ለመፈለግ እንዲቻል ለመንግሥትም አሳውቀናል ስራ እንዳይጎዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል።

በዚሁ ከቀጠለ ሌላም ከባባድ ውሳኔዎች ሊወሰን ይችላል የመድኃኒት ግዢ እና ሌሎችም ድጋፎች ሊቋረጡ ይችላሉ አይታወቅም እንዳይቋረጥ እና እንዲቀጥል እኛም እንደሃገር የምንችለውን ጫና እናደርጋለን።

በውስጥ አቅም በውስን የሰው ሃብት ባለን በጀት ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ በሽታዎች ተመልሰው ከፍ እንዳይሉ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረግን እንገኛለን በሚቀጥሉት ጊዜያት የሚመጡ ውጤቶችን እና ቀጣይ ውሳኔዎችን እናሳውቃለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ድልድዮች ዘላቂነት ያላቸው አይደሉም የብረት ናቸው። ወደ ኮንክሪት እንዲቀየሩ ጥያቄ እያቀረብን ነው ” - የሰሜን ወሎ ዞን መንገድ መምሪያ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የሚገኘውና ከባድ ጭነት ያየዘ ተሳቢ ሲጓዝበት ትላንት የተሰበረው ብረት ድልድይ በኮንክሪት መሰራት እንደሚገባው፣ ይህንንም ለፌደራል አካላት ማሳሰቡን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የድልድዩ መሰበር ያስከተለውን የትራንስፓርት እንቅስቃሴ መስተጓጎል ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄም፣ ለጊዜው ተለዋጭ መንገድ እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ መንገድ መምሪያ ገልጿል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፀሐይነው ሲሳይ ምን አሉ?

“ትላንት ከሰዓት በኋላ የተሰበረው መንገዱ ከወልዲያ ቆቦ አላማጣ ቆቦ የሚያዘልቅ፣ ከትግራይ ክልል የሚያገናኝ፣ ከፍተኛ ትራፊክ የሚተላለፍበት መንገድ ነው።

ከፍተኛ ጭነት የጫነ ተሳቢ መኪና ሲጓዝበት የብረት ድልድዩ ከነመኪናው ታጥፏል። የፌደራል መንገድ ስለሆነ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት አድርሰናል።

በሰዓቱም ችግር እንዳይፈጠር ተራ የሚያስጠብቁ አካላት እንዲያውቁት ተደርጎ ሥራ እየተሰራ ቆይቷል። ትላንትና ህብረተሰቡ እንዳይጉላላ በቅብብሎሽ ሰው እንዲተላለፍ ጥረት አድርገናል። 

መንገዱ አስቸኳይና ተለዋጭ መንገድ ስለሌለው ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ማሽን መድቦ በሰዓቱ ደርሷል። ሥራም ጀምሯል። ተለዋጭ መንገድ ከፈታ እየተደረገ ነው። ከፈታው አልተጠናቀቀም።

አሁን እየተሰራ ነው። የትራፊክ መጨናነቁን በከፈታው ትንሽ ማስተንፈስ ተችሏል። ሥራው እንደቀጠለ ነው። ግን ዘላቂ ነው ማለት አይቻልም። ለጊዜው ካጋጠመው ችግር አኳያ ነው ተለዋጭ መንገድ እየተሰራ ያለው”
ብለዋል።

አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ ጭኖ ነው ወይስ የድልድዩ የጥራት ችግር ነው? ስንል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄም ምላሽ ያሉትን ነግረውናል።

ምን መለሱ?

“በሚመለከታቸው ባለሙያዎች እናሳያለን። ግን ጭነቱም ክብደት እንዳለው ያሳያል። ተሽከርካሪው የድንጋይ ከሰል ነው ተጭኖ ወደ ድልድዩ የገባው የጭንት ክብደት ሊኖር እንደሚችል ያሳያል።

የሌላም ከሆነ ይታያል። በዋናነት ግን ድልድዩም ቢሆን የብረት ድልድይ ነው። ለስምንት ዓመታት አገልገልግሏል።

ይህ ብቻ ሳይሆን አካባቢው፣ በዚሁ በቀጠናችን በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ድልድዮች ዘላቂነት ያላቸው አይደሉም የብረት ናቸው። ወደ ኮንክሪት እንዲቀየሩ ጥያቄ እያቀረብን ነው። ሌሎችም የሚያሰጉን ይኖራሉ”
ነው ያሉት።

ይሄው ድልድይ በሰሜኑ ጦርነት የመሰበር አደጋ ደርሶበት ነበር እንዴ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ “ይሄኛው ሳይሆን አላውሃ ድልድይ ነበር ጉዳት የደረሰበት። እሱም የብረት ነው። ይሄም እዛው ቀጥሎ ያለ ነው” ብለዋል።

አሁን የመሰበር አደጋ የደረሰበት ድልድይ ለመጠገን ምን ያክል ወጪ እንደሚጠይቅ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ “እኛ ሥራ እንዲሰራ ነው ጥያቄ እያቀረብን ያለነው። ርዝመቱ ከ48 እስከ 50 ሜትር ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

“ቀላል ወጪ ይጠይቃል ተብሎ አይታሰብም። ምንም ቢሆን ከመሰራት ውጪ አማራጭ የለውም። ፌደራል ተለዋጭ መንገድ የለውም። መንገዱ ክልልን ከክልል፣ ወረዳዎችን ከዞን የሚያገናኝ ነው” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቄዶንያ “ ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” - መቄዶንያ መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው እርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ። ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ “ በሰይፉ ኢቢኤስ የዩቱብ ቻነል ” ድጋፍ ማድረጊያ መርሀ ግብር ስለሚጀመር…
“ ለአእምሮ ህሙማን ብቻ በየወሩ እስከ 5 ሚሊዮን ብር መድኃኒት እንገዛለን። የህክምና ባለሙዎች እጥረት አለብን ” - የመቄዶኒያ ህክምና ክፍል

የመቄዶንያ አረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል ህክምና ክፍል የመድኃኒት መወደድና የስፔሻሊት ሀኪሞች እጥረት እንደፈተነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የማዕከሉ የህክምና ክፍል አስተባባሪ አቶ ዮናስ ሙሉጌታ በሰጡን ቃል፤ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ እውቀት ያለው በእውቀቱ፣ ጳጳሳቱ በጸሎታቸው እርዳታ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የማዕከሉ ህክምና ክፍል በዝርዝር ምን አለ?

በመቄዶንያ ካሉት 8,000 ሰዎች ወደ 2000 የሚሆኑት የአእምሮ ህሙማን ናቸው። የአእምሮ ህሙማኑ መድኃኒቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ አገር ውስጥ አይገኙም።

ቢኖሩም ውስን ፋብሪካዎች ናቸው የሚያመርቷቸው ጥሬ እቃ ከውጪ አገር እያስመጡ። የተወሰኑ መድኃኒቶችም በቀጥታ ከውጪ አገር ነው የሚመጡት። 

ከገበያ የሚጠፉ መድኃኒቶችም አሉ ከምንዛሪ እጥረት ጋር በተያያዘ። መድኃኒቶቹ መጥፋታቸው ህሙማኑ ህመሙ እንዲያርሽባቸው ይዳርጋቸዋል። ወደ ጤንነታቸው ለመመለስም ጊዜ ይወዳል።

አዲስ አበባ፣ ሰንዳፋ፣ ፃድቃኔ፣ ሶማሌ ክልል ጎዴ፣ አማራ ክልል ደሴ፣ ሀረር፣ ድሴዳዋ በብዛት የአእምሮ ህሙማን የሚገኙባቸው ቦታዎች ናቸው። 

በመቄዶንያ ደግሞ የአእምሮ ህሙማንና አረጋዊያን ብቻ ሳይሆኑ ያሉት የደም ግፊት፣ ስኳር፣ አስም፣ ካንሰር፣ የኩላሊት (ዲያሌሲስ የሚያደርጉ) ህሙማንም አሉ። 

የአእምሮ ህሙማን መድኃኒቶች በጣም ውድ ናቸው። የምንገዛው ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ነው። ለአእምሮ ህሙማን ብቻ በየወሩ እስከ 5 ሚሊዮን ብር እንገዛለን። የህክምና ባለሙያዎች እጥረት አለብን”
ብሏል።

“ካለው ቁጥር አንጻር የባለሙያዎች ቁጥር በቂ አይደለም። ሳይካትሪ እንኳ ወደ 18 ነው የሚሆኑት። ግን ስፔሻሊስቶች ያስፈልጉናል። ባለሙያዎች በበጎ ፈቃደኝነት እንዲያገለግሉ እንፈልጋለን” ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

“በወር ለአንድ እንኳ ሰዓት የህክምና አገልግሎት ቢሰጡ ለህሙማኑ ቀላል አይደለም” ያሉት የህክምና ክፍሉ፣ “የአእምሮ ስፔሻሊቲ፣ የዓይን፣ የጥርስ፣ የፊዚዮትራፒ፣ የሳይኮሎጁ ባለሙያዎች እጥረት አለብን” ብለዋል።

በሙያቸው ወደ ውጪ አገር ሂደው በትላልቅ የህክምና ተቋማት፣ ፋብሪካዎች የሚሰሩ ወገኖች መድኃኒት ቢልኩላቸው መቄዶንያ በህጋዊ መንገድ ፕሮሰስ አድርጎ መቀበል እንደሚችል፣ ድጋፉ ቢገኝ ህሙማን ሳያቋርጡ ህክምናቸውን መከታተል እንደሚችሉ ተመልክቷል።

#ማስታወሻ : የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በSiefu Show Tube ላይ ድጋፍ ለማድረግ ይዘጋጁ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ‘እስካሁን የተፋጠነ ምላሽ አላገኘንም' እያሉ ያሉ በችሎት ሁሌ ነው የሚያነሱት፤ በኛ እምነትም የተፋጠነ ፍትህ እያገኙ አይደለም ” - የእነ አቶ ክርስቲያን ጠበቃ እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለድ ትላንት የችሎት ቀጠሮ ነበራቸው። ጉዳዩን የሚከታተሉ የቅርብ ሰዎች፣ “የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ነበር ትላንት ተዘጋጅተው የሄዱት ግን ያ ሳይሆን ቀርቷል” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ…
" ፍትህ የለም እንጂ ፍትህ ካለ እኔ ነጻ ሰው ነኝ። ፍርድ ቤት በነጻ ለቆ ለደረሰብኝ በደል ሁሉ ካሳ ሊያሰጠኝ በቻለ ነበር " - አቶ ዮሐንስ ቧያለው

እነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስትና የሽብር ወንጀል ችሎት በረበባቸው ክስ የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደረሰው የሰነድ ማስረጃ ለማወቅ ችሏል።

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል፣ " የቀረበብኝን ውንጀላና አሉባልታ አልቀበልም። ወንጀልም አልፈጸምኩም " ማለታቸውን ሰነዱ ያወሳል። 

አክለው፣ " ፍትህ የለም እንጂ ፍትህ ካለ እኔ ነጻ ሰው ነኝ። ፍርድ ቤት በነጻ ለቆ ለደረሰብኝ በደል ሁሉ ካሳ ሊያሰጠኝ በቻለ ነበር። ግን እንዴት ሆኖ/ ራሱ ነጻ ያልሆነ ማንን ሊያደርግ ይችላል " ነው ያሉት።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ18/07/2016 ዓ/ም በስማቸው በሚጠራው መዝገብ ላይ ያቀረበውን ክስ " ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም " ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

የተቃውሟቸውን ምክንያት የገለጹበት ሰነድ፣ " ሁሉም የክስ ጭብጦች በፈጠራ ተሞሉ ናቸው " ይላል።

የክስ ጭብጡ፣ " ‘የሽብር ቡድን አመራር በመሆን፣ አባል በመሆን፣ ራሱን በመሰየም፣ በማደረጃት፣ የሰራተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና ጽንፈኛ ፋኖን በመምራት የሽብር ወንጀል ፈፅሟል’ ይላል " ሲሉ አስረድተዋል በሰነዳቸው። 

ዮሐንስ በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል፣ " የተጠቀሰው ሀሳብ በአንድ በኩል መረጃ አልባና ከእውነት የራቀ ሲሆን፣ በሌላ መልኩ ደግሞ የአንድን የህዝብ ባህላዊ ተቋም ለመክሰስ የሞከረ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " ሲሉ ወንጅለዋል።

" መረጃ አልባነቱን " ጭምር በገለጹበት ሰነድ አቶ ዮሐንስ ምን አሉ ?

“ በኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየመ አሸባሪ ቡድን ማን እንደሆነ፣ በዚህ ቡድን ላይ የእኔ ኃላፊነትና የፈጸምኩት ወንጀል ምን እንደሆነ ከመግለጽ ይልቅ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ራሱ በጭንቅላቱ የፈጠረው ‘አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድን አመራርና አባል ነው’ የሚል የፈጠራ ድርሰት መቅረቡ ነው።

በአንጻሩ አንድን የህዝብ ባህላዊ ተቋም ፍትህ ሚኒስቴር (ጠቅላይ አቃቢ ህግ) በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን በመተላለፍና በደመኝነት መንፈስ ‘አሸባሪ’ ብሎ መሰየሙ ነው። 

ፋኖ የአማራ ህዝብ ተቋም ሆኖ እያለ የፋኖ አመራርና አባል የሆኑ ሰዎች አሸባሪ ናቸው ብሎ መክሰስ ህዝቡን እንደ ህዝብ ከመክሰሱም በላይ ለአማራ ህዝብ ተቋሙ ያሳየውን ንቀት የሚያረጋግጥ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

የአማራ ጠላት የሆነው ዘረኛው ስርዓትም ይሁን በመሳሪያነት እያገለገለ ያለው ጠቅላይ አቅቢ ህግ ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ሁሉም አማራ ፋኖ መሆኑን ነው። የእኔ ‘ፋኖ’ መሆንም በቀጥታ ከአማራነቴ ጋር የተያያዘ ነው።

ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው መላው የአማራ ህዝብ እስካሁን ድረስ ምናአልባትም በጉዲፈቻና በሞጋሳ ከተሸጡት ጥቂት የአብይ አህመድ ቡድን የሆኑ የካቢኔ አባላት ውጪ ሁሉም አማራ ፋኖ እንደሆነ ሁሉ እኔም በፋኖነቴ አላፍርም። እኮራለሁ እንጂ !

ቄሮነትና አባገዳነት ወንጀል እንዳልሆነው ሁሉ ፋኖነትን መንካት በአንድ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከመሆኑም በላይ ምንጊዜም ቢሆን በማንነቴ ላይ የሚመጣን ጥቃት እንደ ባንዳዎችና በጉዲፈቻ እንደተሸጡ የስራዓቱ (የብልጽግና ቡድን) አባላት ዝም ብዩ ልቀበለው እንደማልችል በድጋሚ ላረጋግጥ እወዳለሁ። 

ፋኖነት ወንጀል ሳይሆይን በክብር የሚሰውለት አማራዊነት ነው
" ብለዋል።

አቶ ዮሐንስ ቧያለው ሙሉ የእምነት ክህደት ቃል ገለጻ የያዘው ሰነድ ከላይ የተያያዘ ሲሆን የአቶ ክርስቲያን ታደለ የእምነት ክህደት ቃል ደግሞ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም” - አቶ ክርስቲያን ታደለ

እነአቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ጉዳዩን ከሚከታተሉ ሰዎችና ቃላቸውን ካቀረበበት ሰነድ መረዳት ትችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው አቶ ክርስቲያን የእምነት ክህደት ቃል የሰጡበት ሰነድ፣ “በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም። ጥፋተኛም አይደለሁም” ይላል።

አቶ ክርስቲያን በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ምን አሉ?

“ለ550 ቀናትም በግፍና ጭካኔ እገታ ውስጥ የምገኘው ለአንዲት ደቂቃ እንኳን በጥፋተኝነት የሚያስቀጣ አንዳችም የወንጀል ድርጊት የሚያቋቁም የህግ መተላለፍ ስለፈጸምኩ አይደለም። የአማራ ሕዝብ የሚያነሳቸውን የህልውና ጥያቄዎች በይፋ በማቅረቤ፣ በሕዝቤ የሚደርሰውን ግፍ፣ በደል በማስረጃ በመሞገቴ፣ የገዢውን ፓርቲ አፈናና የመንግስት አሰራሮችንና አመራሮችን ብልሹነትና ዘረፋ በመታገሌ ነው ” ብለዋል።

“ ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት ባሳዩ አካላትም የወንጀልና የፍትሃብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ክስ እንዲመሰረት ፍትህ ሚኒስቴር አዝዥለው ” የሚሉና ሌሎች ድርጊቶችን በአደባባይ እንደታገሉ ገልጸዋል።

“ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው የፋይናንስ ገልጸኝነትና ህጋዊነት እንዲከተሉና እንዲረጋገጡ እንዲሁም ኦዲት ለመደረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቄከለሁ ” ነው ያሉት።

እነዚህን ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች ለማግባባት እንደሞከሩ ገልጸው፣ “ አንዳንዶቹም ሊገድሉኝ፣ ሊያስሩኝና አንዳች ነገር ሊያደርሱብኝ እንደሚችሉ ጭምር ነግረውኛል፤ መልዕክትም አድርሰውኛል ” ብለዋል።

“ አንዳች ወንጀል አልፈጸምኩም ” ያሉት ክርስቲያን፣ “ ይህን በተመለከተ ከክሱ ይዘት ብቻ ሳይሆን በራሴ መንገድ ይህን ክስ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብብኝ ካደረገው አካል ዘንድም አረጋግጫለሁ ” ሲሉ አስረድተዋል።

“ እኔ አማራ የሆንኩት አማራ ሆኘ ስለተወለድኩ ነው። የከማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ የሆንኩትም ፈቅጄ፣ መርጨና ወድጄ ነው። በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ለአማራነቴ ጥብቅና መቆምም ተፈጥሯዊ ግዴታዬ ነው ” ብለዋል።

“ አማራዊ እሴቶታችን ለኛ ቅዱስ ነው ” ብለው፣ “ ይሁንና አቃቢ ህግ ባቀረበው የፓለቲካ ውንጀላ ሰነድ ላይ፣ ‘አማራ ርስቱን ተቀምቷል፤ አገሪቱ በአማራ እሴት መመራት አለባት’ የሚል የርዕዮተዓለማዊ አቋም መያዛችን ክስ ሆኖ ቀርቧል” ብለዋል።

“ ይህ የአቃቢ ህግ ክስ ግን መንግስት ከአማራና ከአማራነት የጸዳች ኢትዮጵያ ነው ወይ የሚፈልገው ? የሚል ሙግት ያስነሳል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከአማራና ከአማራነት በስተቀር እንዲሆኑ የሚደነግግ ህግስ አለ ወይ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል “ በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ‘ቋሪትና ደጋ ዳሞት ላሉ የሽብር ቡድን አስተባባዎች በስልክ ሐምሌ 25/2015 ዓ/ም በመደወል መከላከያን ማጥቃት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በማሳወቅ እንዲመቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል’ ” ማለቱን ጠቅሰል።

“ አቃቢ ህግ ለዚህ ክስ አስረጅ የሆነ አንዳችም ማስረጃ አላቀረበም ” ብለዋል።

(ሙሉ የእምነት ቃላቸውን የሰጡበት ሰነድ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከግምገማ በኋላ በደረስንበት ውጤት ነዋሪዎቹ መቶ በመቶ ጥፋተኞች ናቸው " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ለኮንስትራክሽን ሥራ በገቡ እና እንዲነሱ ባልተደረጉ ቆጣሪዎች ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች በህገወጥ መንገድ ሃይል እንዲጠቀሙ ምክንያት ሆኗል መባሉ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተመዘገቡት ቆጣሪዎች…
➡️ " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " -ነዋሪዎች

🔴 " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


በቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ብሎክ 534 እና 535 ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር የገቡበትን ውዝግብ በሚመለከት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ በአካባቢው በመገኘት እውነታውን መመልከት እንደሚቻል ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ያለውን እውነታ ለመመልከት እና ቅሬታውን ለመፍታት ከቀናት በፊት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር ፣ የሪጅኑ የህግ ክፍል፣ የጸጥታ አካላት እና ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ምልከታ ተደርጓል።

በምልከታው ወቅትም የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብም በቦታው በመገኘት ከአገልግሎቱ ሃላፊዎች እና ነዋሪዎች እውነታውን ለመመልከት ጥረት አድርጓል።

አገልግሎቱ በአራብሳ የጋራ መኖሪያ መንደር ሳይት ሶስት ሃይልን ከቆጣሪ ላይ በህገወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ እንደተደረሰባቸው በመግለጽ የቆጣሪውን እዳ እንዲከፍሉ በማሳወቅ ሃይል ያቋረጠባቸው ብሎኮች 534፣ 535፣ 550 እና 551 ናቸው።

የቲክቫህ አባል ቦታው ተገኝቶ እንደተመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት " በህገ-ወጥ መንገድ ቆጣሪን እንዳይቆጥር በማድረግ ሃይል ሲጠቀሙ እንደነበር ደርሼበታለሁ " በማለት ሃይል ካቋረጠባቸው አራት ብሎኮች ውስጥ ሁለቱ ማለትም ብሎክ 550 እና 551 ሃይል ተቀጥሎላቸው አገልግሎት እያገኙ ነበር።

የእነዚህ ቆጣሪዎች እዳ ባልተከፈለበት እና ከሌሎች ብሎኮች ጋር በጋራ ሃይል በተቋረጠበት ሁኔታ ለእነርሱ በማን እና በምን ሁኔታ ተቀጠለ ? የሚል ጥያቄ ለሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ዳይሬክተሩም ፤ የቆጣሪዎቹ እዳ ባልተከፈለበት ሁኔታ የእነሱ ሃይል መጠቀም ከእርሳቸው እውቅና ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተቋረጠ በኃላ በራሳቸው ሃይሉን ቀጥለው ይጠቀሙ ወይስ የአገልግሎቱ ሰው ቀጠለላቸው የሚለውን ጉዳይ ማጣራት በማድረግ " አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

በመቀጠለም ምልከታ የተደረገው ብሎክ 534 እና 535 ላይ ሲሆን እነዚህ ብሎኮች " ሃይል በህገ ወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ በኢንስፔክሽን ወቅት ተገኝተዋል " በሚል ሃይል ከተቋረጠባቸው ወር እንዳለፋቸው ተናግረዋል።

አገልግሎት በበኩሉ " ሃይሉን ያቋረጥኩት ከጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች ለአንድ ዓመት ከአራት ወር በላይ ቀጥዬ ተጠቅሚያለው ያሉ እና የሚጠቀምም ስለመኖሩ በደረሰኝ ጥቆማ መሰረት ነው " ብሏል።

ነዋሪዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ቀጥለው አለመጠቀማቸውን ተከራክረዋል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሞያዎች ግን የቆጣሪውን ሃይል ባቋረጡበት ወቅት እነዚህ ብሎኮች መጨለማቸውን እንደማስረጃ በመጥቀስ ሃይል በህገወጥ መንገድ እየተጠቀሙ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል።

" ሃይል የተቋረጠብን ለብሎካችን የገባው ስሪ ፌዝ ቆጣሪ በመቆረጡ እንጂ ከተጠቀሰው ቆጣሪ ላይ ሃይል አልቀጠልንም " ሲሉ የተከራከሩት ነዋሪዎች " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።

" ከጋራ መኖሪያ ብሎኩም የተጠቀመ ቢኖር ለይቶ እነሱን ተጠያቂ ማድረግ የአገልግሎቱ ሃላፊነት ነው ሁሉም ባላጠፋው ለወር ያህል ነዋሪው ለምን ይቀጣል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

አገልግሎቱም በምላሹ " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " ቢልም ነዋሪዎች ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሪጅኑ ዳይሬክተር በቦታው በተገኙበት ወቅት ለነዋሪዎች መፍትሔ ለመስጠት ሃይሉን እንዲቀጠልላቸው ያደረጉ ሲሆን ለህገ ወጥ ድርጊት ምክንያት የተባለውን ቆጣሪም ከቦታው እንዲነሳ አድርገዋል።

ዳይሬክተሩ አቶ ብርሃኑ ሲጠቀሙ የነበሩትን አካላት ማንነት ከነዋሪዎቹ ወይም ኮሚቴዎቹ ማግኘት እንደሚፈልጉ እና በጊዜ ሂደት ማንነታቸውን የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ ሃይሉ በድጋሚ እንዲቀጠል በተደረገበት ወቅት በብሎኩ ካሉ ሁለት ቆጣሪዎች ለመታዘብ እንደተቻለው 1,500 ብር የተሞላው በ19/02/17 ዓ/ም የነበረ ቢሆንም ሃይል እስከተቋረጠበት 15/04/17 ዓም ድረስ ባለው ሁለት ወር ውስጥ ከካርዱ ጥቃም ላይ የዋለው ከ 10 ብር በታች ሆኖ ተገኝቷል።

" ቆጣሪው ሲገናኝ ያሳየው የብር መጠን 1,492. 5  አና 1,455.32 ብር ነው ይህ ማለት በ2 ወር ጊዜ ውስጥ የተጠቀሙት ከ10 ብር በታች ነው ይህ ሁሉ ህብረተሰብ በ10 ብር 2 ወር ሊጠቀም አይችልም ያማለት ቀጥታ ሲጠቀሙ እንደነበር ተጨባጭ ማስረጃ ነው " ሲሉ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

በብሎኮች በመዟዟር በተደረገው ምልከታ በቀጥታ ያለቆጣሪ ከመስመር ላይ በመቀጠል ሃይል የሚጠቀሙ ሰዎች ስለመኖራቸው ለመታዘዘብ ተችሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
“በሌሎች ተብሎ የተገለጸው ቃጠሎ በምርመራው ያልተደረሰባቸው ማለት ነው” - ፌደራል ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ በ2017 ዓ/ም በ6 ወራት በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የተከሰቱ 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎችን መንስኤ “በፎረንሲክ ምርመራ” ማጣራቱን የሚገልጽ ውጤት ይፋ አድርጓል።

50 ቃጠሎዎች በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ፣ 11 በመካኒካል ችግር ፣ 10 ሆን ተብሎ ፣ 17 በቸልተኝነት፣ 15 በሌሎች ምክያቶች የደረሱ መሆናቸውን ገልጿል።

አጠቃላይ ባለፉት 6  ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 96 እና በክልሎች ደግሞ 7 በአጠቃላይ እንደ ሀገር 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ደርሰው የአደጋ መንስኤዎችን ማጣራቱን ጨምሮ ገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር የተከሰተ አደጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤት፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1965 ንግድ ቤቶች፣  በ6 ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ አመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ 15 ቃጠሎ በሌሎች ምክንያቶች እንደተከሰቱ ገልጿችኋል፤ ሌሎች ሲባል ምንድን ናቸው? የሚልና ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለፌደራል ፓሊስ አቅርቧል።

በፌደራል ፓሊስ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ፣ “በሌሎች ተብሎ የተገለጸው ቃጠሎ ስቲል በምርመራው ያልተደረሰባቸው ማለት ነው” ሲሉ መልሰዋል።

“ለምሳሌ እሳት አደጋ ይደርስና ከዛ ቦታ ላይ ለማስረጃ የሚሆኑ ኢቪደንሶችን፣ ማስረጃዎችን ማጥፋት፣ ቁሳቁሶችን ጠራርጎ ማውጣት እሳቱ ከጠፋ በኋላ። አሁን ይሄ አይነት ቃጠሎ በምን እንደተፈጠረ አይታወቅም” ብለዋል።

“ሆን ተብሎ በሰው” የደረሱ 10 ቃጠሎች በፈጸሙ እርምጃ ተወስዷባቸዋል? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ የሰጡን ምላሽ፣ ደግሞ፣ “ተጠያቄ ይሆናሉ ተጣርቶ። ይሄ ፕሮሰስ ላይ ነው። ኢቪደንሱ ተገኝቷል። በዚህ ኢቪደንስ መሰረት ይጠየቃሉ” የሚል ነው።

“ለምሳሌ አንድ ሰው ‘ራሱን አቃጥሎ ነው የሞተው’ ብሎ ሰው ቢገድል ኢቪደንሱ ሲገኝ፣ ግድያው በሰው መሆኑ ሲረጋገጥ ለግድያውም ተጠያቂ ነው የሚሆነው” ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን ያክል ሰዎች ናቸው? “ሆን” ብለው በማቃጠል የተጠረጠሩት? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ኃላፊው፣ “አሁን ስለእሳቱ ብቻ ነው መግለጽ የፈለግነው። ወደፊት ይገለጻል” ከማለት ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በቸልተኝነት የደረሰ ቃጠሎ ማለትስ ምን ማለት ነው? ለሚለው ጥያቄም፣ “ለምሳሌ ሻማ አቀጣጥሎ ሳያጠፋ ቢተኛ፣ ተሽከርካሪ ላይ ጌጁ ሙቀት መጨመሩን እያሳዬ አሽከርካሪው እርምጃ ካልወሰደ በቸልተኝነት ይቃጠላል እንደዛ ማለት ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“በቸልተኝነት ማለት ባልተገባ ሁኔታ ወይም በነግሊጀንስ ማለት ነው” ነው ያሉት አቶ ጀይሉ።

ደረሱ በተባሉት 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ምን ያክል ንብረት እንደወመስ ታውቋል? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ፣ “እሱ ሌላ ነው። አሁን ዋናው ነገር በምን ተቃጠለ የሚለው ነው የተጣራው” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔈 #የሹፌሮችድምጽ

“ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ባለማድረጋቸው ለአጃቢ እስከ 2,000 ብር ለመክፈል ተገደናል። በቀናት ብቻ ከ12 በላይ ሹፌሮች ታግተዋል ” - ማኀበሩ

የጸጥታ መደፍረስ በሹፌሮችና ተሳፋሪዎች ግድያና እገታ ማስከተሉን፣ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ባለማድረጋቸው አሽከርካሪዎች ለአጃቢ 2,000 ለመክፈል መገደዳቸውን ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

“ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ባለማድረጋቸው ለአጃቢ እስከ 2,000 ብር ለመክፈል ተገደናል። በቀናት ብቻ ከ12 በላይ ሹፌሮች ታግተዋል ” ሲልም በሁነቱ ተማሯል።

በአማራ ክልል ከገንዳውሃ ወደ ጎንደር ባለው መንገድ ረቡዕ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ/ም አንድ ሰው ተገድሎ፣ ሁለቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጿል።

“ በአስር ቀናት ደቡብ ጎንደር 3 ሹፌሮች፣ በደባርቅ ዙሪያ 2 ረዳቶችና 6 ሹፌሮች፣ ገንዳውሃ 2 ሹፌሮች፣ አብርሃጀራ አንድ ሹፌር በታጠቁ አካላት ታግተዋል። በአብርሃጅራ ሹፌር ተተኩሶበት አምልጧል፤  ሁለት ቦቴዎችን ወቅንና ገደብዬ መካከል አግተዋቸዋል ” ነው ያለው።

ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል በዝርዝር  ምን አለ ?

“ ከአሸሬ እስከ ሶረቃ የሚያስፈራ ቦታ አለ። በፈቃድ ለታጠቁ የአካባቢው ሰዎች 2,000 ብር እየከፈልን ነው የምናልፈው። በቅርቡ አንድ አጃቢ አጋች መትቷል ሹፌር ሊያግት ሲል ወርዶ ተኮሰበት።

ጨንቆን ነው እንጂ ይሄ ሂደት ደግሞ መጥፎ ነው። ህግ ባለመከበሩ ምክንያት ለሹፌሮች እለታዊ መፍትሄ ሆኗል። ግን የአጃቢነት ስራ እየሰሩ ያሉ ሰዎች እንዴት ነው የአካባቢ ሰላም እንዲመለስ የሚፈልጉት?

ስለዚህ እገታ ያለባቸው ቦታዎች ይታወቃሉ። በአርማጭሆ በኩል ከከተማው አፍንጫ ስር ከ10 ጊዜ በላይ እገታ ተፈጽሞበት ቦታው ላይ የጸጥታ አካል አይቀመጥም። 

የጸጥታ ዘርፉ ትኩረት ቢሰጥ ችግሩን መቆጣጠር ይችላል። ምክንያቱም በአንድ አጃቢ ከፍለን የምናልፈው አካባቢ ነው። መዝረፊያ በሮች የሚታወቁ ናቸው”
ብሏል።

ለአጃቢ ከመክፈል በተጨማሪ ሹፌሮች ከጸጥታ ስጋት አንጻር በ100ዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ዙሪያ ጥምጥም እንዲጓዙ እየተገደዱ መሆኑም ተገልጿል።

ማኀበሩ በመንገዱ ዙሪያ ምን አለ ?

“ በደባርቅ በኩል ባለው መንገድ ከደብረ ታቦር ጋይንት መንገዱ ችግር ትልቅ አለበት። መንገዱ አማራ ክልል ከጅቡቲ የሚገናኝበት ነው። ማደበሪያ የሚገባው በጋይንት ነው። በሚሌ፣ ጭፍራ፣ ሃራ፣ ወልዲያ አድርጎ በደብረ ታቦር አድርጎ ይመጣል።

ግን ማዳበሪያ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች በዚህ አመት በጸጥታው ችግር ምክንያት ተጨማሪ መንገድ እየተጓዙ በአዲስ አበባ በኩል ለመምጣት ተገደዋል። ከደጀን በእጀባ ነው የሚመጡት ወደ ጎጃምና ጎንደር ጭምር።

በጸጥታው ችግር ተሽከርካሪዎች ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ተጨማሪ መንገድ ለመሄድ ተገደዋል። ይህ ለአርሶ አደሩም ጉዳት አለው። 1,950 ብር ነው አንድ ኩንታል ማዳበሪያ ከጅቡቲ የሚመጣው። ትራንስፓርት ኮስቱ 1,900 ብር ሲሆን፣ የማዳበሪያው ዋጋ ይንራል።

በጋይንት ቦቴዎች ይሄዳሉ። ጭነው ይመጡና በጸጥታው ችግር መመለሻ ሲያጡ በደባርቅ፣ ዛሪማ፣ በሽሬ፣ ከሽሬ መቀሌ፣ ከመቀሌ አብዓላ አድርገው በአፍዴራ ይወጣሉ። ይሄ ማለት ከ600 በላይ ተጨማሪ ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ።

በጎንደር መተማ መንገድ በመተማ በኩል ነው ኢምፖርት ኤክስፖርት የሚገባው። የመተማ ጎንደርን መንገድ የጸጥታ ችግሩን በመፍራት አሽከርካሪዎች በአብርሃጅራ ዙረው እየገቡ ነው። 

180 ኪሎ ሜትር ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች 140 ኪሎ ሜትር በመጨመር 320 ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ ”
ብሏል።

(ስለጉዳዩ ለጸጥታ አካላት ጥያቄ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#እናትፓርቲ እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የጣሪያ ግድግዳ/ ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ መመሪያው "ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም" ሲል ፍርድ ቤት ጥር 9 ቀን ብይን መስጡቱን ፓርቲው አስታውቋቃ። ፓርቲው የወጣው መመርያ " ሕግን ባልተከተለ መንገድ እና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ሥልጣን የወጣ…
" ፋይናንስ ቢሮ ይግባኝ በመጠየቁ አፈጻጸሙ ከትላንትና በስቲያ ጀምሮ ታግዶ ነው ያለው " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የጣሪያ ግድግዳ / ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ መመሪያው "ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም " ሲል ፍርድ ቤት ጥር 9 ቀን ብይን መስጠቱን ፓርቲው ማስታወቁ ይታወሳል።

ይህንንም የፍርድ ቤት ውሳኔ በጋዜጣዊ መግለጫው አሳውቆ የነበረው ፓርቲው የፋይናንስ ቢሮ ይግባኝ በመጠየቁ ምክንያት የውሳኔው አፈጻጸም ከትላንትና በስቲያ ጀምሮ መታገዱን የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰይፈሥላሴ አያሌው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የፓርቲው ፕሬዝዳንት በዝርዝር ለቲክቫህ በሰጡት ሃሳብ ምን አሉ ?

" ጥር 9 ቀን 6:30 ላይ ውሳኔውን ከፍተኛ ፍ/ቤት አሳልፎ 7:30 ላይ የፋይናንስ ቢሮ አቃቢ ህግ በቃለ መሃላ ' ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ይግባኝ እስከምል ድረስ አፈጻጸሙ ይታገድልን ለ15 ቀንም ፓርቲው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ ' አሉ።

የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ መጠበቅ ስለነበረብን እኛም ለ15 ቀናት ጠበቅን 15 ቀኑ የሞላው አርብ ነበር ሰኞ መግለጫ ሰጠን።

በ15 ቀን ውስጥ ይግባኝ ባይጠይቁም ከትላንት በስቲያ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አፈጻጸሙ ታግዶ እንዲቆይ በሚል ይግባኝ መጠየቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ቢሮአችን ላይ ተለጥፎ አግኝተናል።

እየተነጋገርን ያለነው ስለ ህግ ጉዳይ ነው ክፍያው ይቀጥል አይቀጥል አይደለም እኛ እያልን ያለነው ከተማ መስተዳደሩ የጣለው ግብር ከህግ አግባብ ውጪ እንደሆነ ነው መሆኑን ደግሞ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አረጋግጦልናል።

እያንዳንዱ ከህዝብ የሚሰበሰብ ሳንቲም የህግ መሰረት ሊኖረው ያስፈልጋል ይህ የጣራና ግድግዳ ግብር እየተሰበሰበ ያለው ከህግ አግባብ ውጪ ነው የሚከፈለው ገንዘብ መቆም አለበት ብለን ነው ክስ የመሰረትነው።

ፍርድ ቤቱም ክፈሉ አትክፈሉ አይደለም እያለ ያለው ነገር ግን ለክፍያ መመሪያ የነበረው በሚያዝያ 2015 የወጣው እና እንዲፈጸም የሚያስገድደው መመሪያ መሻሩን ነው የገለጸው።

በዚህም መሰረት የህግ ውሳኔ አፈጻጸም አካሄድ ቢኖረውም የከተማ መስተዳደሩ ይህንን ግብር ወደ ፊት እንዲሽረው ይጠበቃል።

የፋይናንስ ቢሮ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢጠይቅም የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ ያጸድቀዋል ብለን ነው የምናምነው ቢሽረው እንኳ ሰበር ሰሚ ችሎት በመኖሩ ጉዳዩን እስከመጨረሻው እንገፋበታለን።

የኢትዮጵያ ህዝብ 10 ሺ፣20 ሺ እና ሚሊየን ለጣራ እና ግድግዳ በሚል ከፍሎ አያውቅም እንዲህ መክፈል የተጀመረው ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ ነው መቼም ይጀመር መመሪያው ህገ ወጥ ነው " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia