TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አርቲስት አለምፀሀይ⬇️

አርቲስት አለምጸሐይ ወዳጆን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ የተቋቋመው ኮሚቴ ዝግጅቱን አጠናክሮ እየሰራ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከ27 አመታት በኋላ ወደ አገሯ የምትመለሰው አለምጸሐይ ወዳጆ #ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ማለዳ 1፡00 ሰአት አዲስ አበባ ስትገባ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ቤተሰቦቿ፣ የሙያ አጋሮቿ እና የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች በተገኙበት በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

አዘጋጅ ኮሚቴው ባወጣው መርሀግብር መሰረት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከሚደረግ ደማቅ በኋላ ለአመታት ወዳገለገለችበት ብሔራዊ ቴአትር በመምጣት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ለተጋባዦች በማቅረብ እንኳን ደህና መጣሽ ለዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል ተብሏል።

ከእንኳን ደህና መጣሽ መርሀግብሩ በተጨማሪም በብሄራዊ ቴአትር ከአድናቂዎቿ ጋ የምትገናኝበት ልዩ ዝግጅት እየተሰናዳ ሲሆን የዝግጅቱ ቀንም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ተሰምቷል።

©ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ድሬዳዋ ፖሊስ⬆️

በድሬዳዋ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች በቤቶች ላይ ምልክት መደረጉን ተከትሎ ምልክቱ የጥቃት ነው በሚል በማህበራዊ ድረ ገፅ #ስጋት
ፈጣሪ ሀሳቦች ተሰራጭተዋል። በመሆኑም የአስተዳደሩና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ከትላንት ጀምሮ #የተጠናከረ ጥበቃና ክትትል እያደረጉ
መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግኑኝነት ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ሳጂን ባንታለም ግርማ ገልፀዋል።

እስከ አሁን በተጨባጭ የተፈጠረ #ችግር የለም ያሉት ዋና ሳጂን ባንታለም ግርማ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ድረ ገፅ በሚለቀቁ መረጃዎች ተደናግሮ ለሁከትና ግጭት በር ሳይክፈት የለት ተለት ሠላማዊ ኑሮውን ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። ብጥብጥ ለመፍጠር የሚፈልግ አካል ካለም በድሬዳዋ #የማይሳካ መሆኑና ፖሊስም የማይታገስ መሆኑን አውቆ ከጥፋት ድርጊት እንዲታቀብ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡ ስጋት ፈጣሪ እንቅስቃሴዎች ባየ ጊዜ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም ዋና ሳጅኑ ጠይቀዋል፦

☞025 111 16 00
☞025 111 52 11

በተያያዘ ፦ ሀምሌ 29 - 2010 በድሬዳዋ ለ13 ንፁሀን ዜጎችና ህልፈትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ሁከት ተከትሎ ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት የፊታችን #ማክሰኞ ለሕዝብ በይፋ የሚገለጽ መሆኑን ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ አሳውቀዋል።

©Diredawa Mayoroffice
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!! 1493ኛው የነብዩ ሙሃመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል መውሊድ #ማክሰኞ ሕዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፋር ክልል ጥቃት ተፈፀመ‼️

#ሰኞ መጋቢት 16 እና #ማክሰኞ መጋቢት 17 በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ከጎረቤት ሀገራት መጡ የተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ። ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሌ ላንድ እና ከጅቡቲ አዋሳኝ አካባቢዎች በኩል በገቡ ኃይሎች መሆኑን የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ አህመድ ኻሌይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/በአፋር-ክልል-ጥቃት-ተፈፀመ-04-04-2
#ማክሰኞ

√ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ

√አዲስ አበባ ስታዲየም

√ጨዋታው የሚካሄድበህ ሰዓት 10:00

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቤኔ ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ዶክተር ሙሉ ነጋ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ስራ ያቆሙ የመንግስት ሰራተኞች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በተጠቀሰው ቀን ወደ ስራ ገበታው የማይመለስ የመንግስት ሰራተኛ ካለ በገዛ ፈቃዱ ስራውን እንደለቀቀ ተደርጎ ይወሰዳል ተብሏል።

የንግድ ድርጅቶች ከነገ እሁድ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራቸው መመለስ አለባቸው ተብሏል።

ይህን በማያደርጉ የንግድ ድርጅቶች ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እርመጃ መውሰድ እንደሚጀምር ገልጿል።

በህጋዊም ሆነ በህገ-ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ሁሉ እስከ #ማክሰኞ ድረስ እንዲያስረክብ ጥሪ ቀርቧል።

ከማክሰኞ በኋላ "የቤት ለቤት ፍተሻ" ይደረጋል ፤ በፍተሻው ትጥቅ የተገኘበት ግለሰብ ሲያጋጥም ተጠያቂ እንደሚሆን ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SUDAN #ETHIOPIA

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት በሚቀጥለው #ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የሱዳን ጠ/ሚ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው ሐምዶክ እና ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው በመጪው ማክሰኞ ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለቱን አገሮች ድንበር ለማካለል የተቋቋመው ኮሚቴ በሚያደርገው ድርድር ላይ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን 1,600 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር ይጋራሉ።

ምንጭ፦ AFP / Deutsche welle
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኢድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?

#ኢድ_አልፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ  ማታ ከታየች #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ አንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ዒድአልፈጥር

የዒድ አልፈጥር በዓል #ጨረቃ ዛሬ ከታየች ነገ #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ ይከበራል።

በሳዑዲ አረቢያ የሸዋል ጨረቃ ለማየት በቱማይር እና ሱዳይር የመመልከቻ ቦታ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia