TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መቐለ

" ዲግሪ ለመያዝ 8 ዓመታትን መማር #ፍትሃዊ አይደለም " - ተማሪዎች

ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ በኃይል እንዲበተኑ ተደርገዋል።

ተማሪዎቹ ምንድነው ጥያቄያቸው ?

" አንድ ዲግሪ ለመያዝ 8 (#ስምንት) ዓመታትን መማር  #ፍትሃዊ አይደለም " ያሉት ተማሪዎቹ " ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የምንለይበት ምክንያት የለም ፤ የመውጫ ፈተና መፈተን አለብን " ብለዋል።

" ተመርቀን ወጥተን ስራ መስራት ፤ ህይወትን ማሸነፍ ባለብን በዚህ እድሜያችን የመጀመሪያ ዲግሪ ለማግኘት 8 ዓመታት መጠበቅ የለብንም ፣ የወጣትነት እድሜያችን ያሳስበናል ፤ ብንጮህ ብንጮህ ሰሚ አላገኘንም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በዚህ ዓመት መመረቅ ሲገባን ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ትማራላችሁ እያሉን ነው ይሄ በፍፁም የማንቀበለው ነው " ብለዋል።

ዛሬ ተማሪዎቹ ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በመነሳት የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ ወደ ከተማ ለማምራት ሲሞክሩ በፓሊስ እንግልትና ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።

የትራፊክ ፖሊስ አባላት ሰልፉን ለማደናቀፍ መንገድ ሲዘጉ ፤ ታጣቂዎች ሰልፈኛ ተማሪዎች ሲደበድቡ ታይተዋል።

ጥያቄ  ካነሱ ሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል ሶስት ሴት ተማሪዎች በፓሊስ #ሲደበደቡ መመልከቱን ህሉፍ በርሀ የተባለ የአይን እማኝ ገልጿል።

ከዛሬው ሰልፍ ጋር በተያያዘም አንድ የፖሊስ አባል አንዲት #ሴትን እያንገላታ #ገፍትሮ መሬት ላይ ሲጥላት የሚያሳይ ቪድዮ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ስልፍ በማስመልከት የዩቨርስቲው አስተዳደር እና የትምህርት ሚንስቴር እንዲሁም የከተማው ፖሊስ እስከ አሁን ያሉት ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተቋማቱ የሚሉት ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
ከተጠቀሱት የባንክ አማራጮች ወደ M-PESA ገንዘብ በመላክ እስከ 50 ብር ስጦታ እናግኝ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
#ፊቼጨምባላላ

የፊቼ ጨምበላላ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉ ዋነኛ መለያው ሰላም ፤ አንድነትና ፍቅር ሲሆን በዚህ በዓል ተጣሉ ሰዎች ይታረቃሉ ፤ ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል። ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም ፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይም እንዲሰማሩ ይደረጋል።

በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል። እንደ ሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች " ፊቼ ጫምባላላ " መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት

የደብር ብርሃን - ደሴ ዋና የፌዴራል መንገድ ከዛሬ መጋቢት 28/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንደሚሆን የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ገልጿል።

ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ከየካቲት 16 /2016 ዓ.ም አንስቶ ተቋርጦ የቆየው ይኸው መንገድ ከዛሬ አንስቶ ለህዝብ ትራንስፖርት ክፍት ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
የኢድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?

#ኢድ_አልፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ  ማታ ከታየች #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ አንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በነዳጅ የሚሠሩ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ውጪ ተገጣጥመው ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ ተደረገ።

የጉምሩክ ኮሚሽን በነዳጅ የሚሠሩ እና ሙሉ በሙሉ ውጭ ተገጣጥመው ወደ ሃገር  የሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ መጣሉን አሳውቋል።

ዕቀባው ያስፈላገበት ዋና ምክንያት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ እና በሃይብሪድ /በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ/ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ ለማበረታት ነው ተብሏል።

አሰራሩ ፥ የአረንጓዴ ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለነዳጅ እና በነዳጅ ለሚሰሩ አውቶሞቢሎች ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጪ ምንዛሬ ለመቀነስ ይረዳል ሲል ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ይህ እቀባ #ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል።

በነዳጅ የሚሠሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ የሚያስገቡ አስመጪዎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ #ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba “ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” - የሟች ቤተሰብ “ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ ወጣት ሶፎኒያስ አስራት የሚባል ሹሬር ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ ሰዎችን አሳፍሮ እንደወጣ አለሙለሱን፣ በመጨረሻም ሹፌሩን ገድለው ፣ ተሽከርካሪውን…
#Update

ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ' ማንነታቸው ያልታወቁ ' ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ከዘረፉት ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ሟች ወጣት ሶፎኒያስ መጋቢት 24/2016 ዓ/ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ናሆም ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ 3 ግለሰቦችን አሳፍሮ ወደ ቦሌ ሚካኤል ለማድርስ መሄዱን ጉዳዩን ለመከታተል የተቋቋመው የፖሊስ የምርመራና የክትትል ቡድን አባላት ባደረጉት ክትትል አረጋግጠዋል።

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅደው እና ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ መስለው ሹፌሩን በመቅረብ ከተሳፈሩ በኋላ አንገቱን በገመድ አንቀው በመግደል አስክሬኑን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ በመጣል አይነቷ ቪትዝ የሴሌዳ ቁጥር ኮድ ' 2A 93488 ' ተሽከርካሪ ጨምሮ 2 ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ይሰወራሉ፡፡

ፖሊስ ሌት ተቀን ባደረገው ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰረቁትን ተሽከርካሪ ለመሸጥ እየተስማሙ መሆኑን በበቂ ማስረጃ ካረጋገጠ በሗላ ክትትሉን በመቀጠል ሦስቱን ዋና ወንጀል ፈፃሚዎች የሰረቁትን መኪና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለመሸጥ እየተደራደሩ እንዳለ በቁጥጥር ስር በማዋል የተሰረቀችውን መኪና ፣ 2 ሞባይል ስልኮችን ልዩ ልዩ ኤግዚቢቶችን ይዞ ምርመራውን መቀጠሉን ገልጿል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ምርመራ ማንነታቸው የማይታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ በመለየት 3 ዋና ወንጀል ፈፃሚዎችንና 3 ግብራበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል፡፡

የምርመራ ሥራው እንዳበቃ የፍርድ ሂደት ውጤቱን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገለፅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

@tikvahethiopia