TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ' ህወሓት ' ውስጥ እየሆነ ያለው ምንድነው ? ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከትግራዩ ጦርነት በፊት እንደ ህጋዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ስር ተመዝግቦ ይንቀሳቀስ ነበር። ነገር ግን ቦርዱ ፓርቲው " ኃይልን መሰረተ ያደረገ የአመጽ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል ሰርዞታል። የተወካዮች ምክር ቤትም ፓርቲውን " ሽብርተኛ ድርጅት " ሲልም ፈርጆት ነበር። ደም አፋሳሹና አስከፊው…
#TPLF
በአመራሮች መካከል ከፍተኛ ክፍፍል የፈጠረውና በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ በዝግ ሲመክር ውሏል።
በዛሬ ውሎው የአዘጋጅ ኮሚቴ ሪፓርት አቅርቦ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በሙሉ ድምፅ ማፀደቁ ተሰምቷል።
ከመላው ትግራይ በድምፅ መሳተፍ ከሚገባቸው 950 ጉባኤተኞች 785 ማለትም 83% ተገኝተዋል ተብሏል።
የተለያዩ ወረዳዎች በድምጽ የሚሳተፍ ሰው እንዳላኩ ተሰምቷል።
ከዛሬው የዝግ ስብሰባ በኃላ ድርጅቱ ባሰራጨው መረጃ ፤ " በጉባኤው አንሳተፍም ያሉ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስህተታቸው በማረም ወደ ጉባኤው በመግባት ሃሳቦች ለማቅረብ ዝግጁ ከሆኑ በሩ ክፍት ነው " ብሏል።
የህወሓት የ14ኛው ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋይ ገ/እግዚአብሔር " በኮሚቴው ስራ ውስጥ የሚታዩ ጣልቃ የመግባት ፣ ከፕሮግራም ውጪ ስብሰባ መጥራት፣ ውሳኔዎችን መጠምዘዝ የመሳሳሉ ተግባራት እንዲታረሙ ለመስራት ብሞክርም አልተሳካም " በማለት ደብዳቤ ፅፈው ከሃላፊነት ራሳቸው ስለማግለላቸው መዘገባችን ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በዛሬው ዕለት የወጡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጉባኤውን የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ጨምሯል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የዚን መረጃ ትክክለኝት ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
@tikvahethiopia

#TPLF በአመራሮች መካከል ከፍተኛ ክፍፍል የፈጠረውና በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ በዝግ ሲመክር ውሏል። በዛሬ ውሎው የአዘጋጅ ኮሚቴ ሪፓርት አቅርቦ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በሙሉ ድምፅ ማፀደቁ ተሰምቷል። ከመላው ትግራይ በድምፅ መሳተፍ ከሚገባቸው 950 ጉባኤተኞች 785 ማለትም 83% ተገኝተዋል ተብሏል። የተለያዩ ወረዳዎች በድምጽ የሚሳተፍ ሰው እንዳላኩ ተሰምቷል። ከዛሬው…
#TPLF
ከህወሓት ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆኑት የማይጨው ከተማ ከንቲባ አቶ የማነ ንጉስ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል ፤ " ጉባኤው የተወሰነ ቡድን ለማጥቃት በችኮላ የተጠራ ነው " ብለዋል።
በዚህም እሳቸው ጨምሮ በርካቶች ተቃውሞዋቸውን በመግለፅ ከመድረኩ መቅረታቸውን አመልክተዋል።
የህወሓት ማእከላዊ ቁጥጥር ኮምሽን ሊቀ መንበር አቶ ተክለብርሃን አርአያ ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ " 14ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተብሎ የተጀመረው ስብሰባ ህወሓትን ወደከፋ ችግር የሚያስገባ ነው " በማለት ጉባኤውን አውግዘዋል።
አቶ ተክለብርሃን ፥ " አንድነታችን ይዘን ፣ የፕሪቶርያው ውል ማእከል አድርገን፣ ለአላዊነታችን አረጋግጠን በተጨማሪም አንድ ላይ በመንቀሳቀስ ሕጋዊ እውቅናችን መልሰን ሊደረግ የሚገባው ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይህ ጉባኤ ግን ወደ ቅርቃር ውስጥ የሚያስገባን ነው " ብለዋል።
" ተግባብተን ወደ አንድ መንገድ መጥተን ልናደርገው ይገባ የነበረ ነው። ላይ ያለው አመራሩ ብቻ ሳይሆን ታች ያለው አባልም ጭምር መግባባት የፈጠረበት ሊሆን ይገባ ነበር " ማለታቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

#Tigray " ሁሉንም የፓለቲካ ሃይሎች ያቀፈ መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ያስፈጋል " - ሦስት የፓለቲካ ፓርቲዎች በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ባይቶና፣ ሳወት፣ ናፅነት የፓለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ ፤ " ሳምንቱን በስርዓቱ ባለቤቶች መካከል በመካሄድ ያለው ህገ-ወጥ እንቃስቃሴና ፍጥጫ ተው መባል ይገባዋል " ብለዋል። በህወሓት አመራሮች የተፈጠረው ፍጥጫ ተከትሎ በህዝቡ የሚታየው መረበሽ…
#TPLF
" በህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ስም ማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም " - እነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ጉባኤ ውሳኔ
በአመራሮች መካከል ክፍፍል የፈጠረው የህወሓት ጉባኤ ባወጣው መግለጫ ፥ " የተለየ ሃሳብ አለኝ " የሚል በጉባኤ ያልተገኘ አካል ወደ ጉባኤው ቀርቦ ሃሳቡ በነፃነት እንዲገልፅ ፣ በዴሞክራሲያዊ ምጉት ለሚተላለፉት ውሳኔዎች ተገዢ እንዲሆን ነሃሴ 8/2016 ዓ.ም ጥሪ ማቅረቡ አስታውሰዋል።
" የድርጅቱ ጉባኤ ከተሰየመበትና ከተጀመረበት ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም ቀን በኋላ ተራ አባል እንጂ የማእከላዊ ኮሚቴ የሚባል ሃላፊነት የላቸውም " ብሏል የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ አቋም በመደገፍ ጉባኤውን ላወገዙ የቀድሞ ጉምቱ አመራሮቹ።
" ስለሆነም ከህግና ተቋማዊ የደርጅታችን አሰራር ውጪ በአሁኑ ወቅት በህወሓት ስም ማንኛውም የፓለቲካ ስራ ለመፈፀም ሃላፊነት ያለው የማእከላዊ ኮሚቴና የማዕከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሆነ ሌላ አካል የለም " በማለት አብራርቷል።
" ስለዚህ ህዝባችንና መላ አባላችን ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የጉባኤውን ውሳኔ በመረዳት እንዲተገብሩና እንዲተገበር እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርባለን " በማለት አክለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ ቀደም ብሎ ለዚህ ጉባኤና በጉባኤው ለሚተላለፉ ማናቸውም ውሳኔዎች ምንም እውቅና እንደማይሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።
በምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት አሰራሩን ያልተከተለ ጉባኤ null and void / ምንም እውቅናና ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው።
በሌላ በኩል ፥ በአሁን ሰዓት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ም/ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ እየሰጡ ናቸው፤ ያነሷቸውን ሀሳቦች እናደርሳችኋለን።
#TikvahEthiopiaMekelle

#አሁን : በመቐለ ከተማ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ በወቅታዊ የህወሓት የፓለቲካ ሁኔት ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ መድረኩ ላይ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " ብለው የተቃወሙ ፦ ➡️ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ፣ ➡️ የድርጅቱ የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን ፣ ➡️ የክልል ፣ የዞን ፣ የወረዳና ሌሎች አመራሮች…
#TPLF
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?
ዛሬ መቐለ ሁለት ስብሰባ ሲካሄድ ውሏል።
አንዱ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚገኙበት 14ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ሌላኛው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጉባኤውም የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ የክልል፣ የዞን እና ወረዳ አመራሮች የተገኙበት ነው።
አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?
- ያለ ልዩነት (በአመራሮች መካከል) " ጉባኤ ይደረግ አይደረግ " የሚል ሳይሆን እንዴት ይደረግ የሚል ነው።
- የእውቅናው ጉዳይ ከፌደራል መንግስት ጋር በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት መፍትሔ እንዲገኝለት ሁሉም ተግባብቶ እያለ፥ የተወሰኑ ግለሰቦች በጎን በመንቀሳቀስ ወደ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወረቀት በማስገባት ከመግባባቱ ያፈነገጠ ስራ ከውነዋል።
- የተፈጠረው አለመግባባትና ክፍፍል፥ የፕሪቶሪያ ስምምነት ያለባለቤት የሚቀርበት ዕድል የሚፈጥር ነው። ይህን አደጋ ለመቀልበስ ጥረት ይደረጋል።
- ሁኔታው የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ሂደት ባለቤት አልባ ሊያደርግ የሚችል ነው። ይህን ጉባኤ የፌደራል መንግስት አልተቀበለውም። ፌደራል አለመቀበሉ የራሱ ትርጉም አለው። ዋናው ነገር ግን በፓርቲያችን ውስጥ አንድነት እና መቀራረብ፣ በሐሳቦች ዙርያ አብሮ መስራት ሳይሆን መከፋፈል እና መራራቅ የሚያስከትል አደገኛ መድረክ ነው።
- የተፈጠረው ልዩነት አስጊና 'ጠላቶች' ሊጠቀሙበት የሚችል ነው።
ትላንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ፥ " የህዝብ የሰላም ፍላጎት ወደጎን በመተው፣ ለግዜው ማን መሆኑ በግልፅ ከማይታወቅ እና እነሱ ደጀን ይሆነናል ያሉት የውጭ ኃይል ተማምነህ፥ ያልሆነ ዝግጅት፣ የተወሰነ ግለሰቦች ጠባብ ፍላጎት ሲባል የትግራይ ህዝብን ዳግም ወደ አደጋ ለመዳረግ የሚደረግ እንቅሰቃሴ ነው እየተካሄደ ያለው " ብለው ነበር።
ለዚህ ቃላቸው የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ቃል አቀባይ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ አማኑኤል " ይህ አገላለጽ ትክክል አይደለም። ህወሓት እምነቱ በትግራይ ሕዝብ፣ በፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት በተቋማዊ አሰራር ነው። ሁሉም ችግሮች በሰላማዊ ፖለቲካዊ መንገድ ይፈታሉ ብለን ነው የምናምነው " ነው ያሉት። #ዶቼቨለ

#TPLF ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል። ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። " በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት…
ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ?
" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ
በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል።
አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ተሰብስቦ ስለ አንድ ድርጅት ውስጣዊ ጉዳዮች መወሰን ወደ ጦርነት የሚያስገባ አንድም ምክንያት የለም " ሲሉ ተናግረዋል።
" ጦርነት በዚህን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ አይደለም " ብለዋል።
" ጦርነት አስፈላጊ ሆኖ አማራጭ ቢሆን ኖሮ ትግራይ ውስጥ ያሉት ችግሮች ሌላ ጦርነት ይጋብዙ ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።
እንዚህ ችግሮች ለተፈጸሙ ወንጀሎች የተጠያቂነት አለመረጋገጥ ፣ በህገመንግስት ላይ የተቀመጠው የክልሉ ግዛት አለመመለስ ፣ የተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው አለመመለስ ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ ...ወዘተ እንደሆኑ ነው የጠቆሙት።
" ዛሬም ትግራይ ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ። ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለባቸው ነው ግን የተጀመረውን የሰላም ተስፋ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለ እየኖረ ነው " ብለዋል።
" ያሉ ችግሮች ወደ ጦርነት ሳያስገቡ አንድ ህወሓት የሚባል ድርጅት በፕሪቶሪያ ስምምነት አካል የሆነ ባለቤት የሆነ ውስጣዊ ችግሮች አጋጥመውት ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል ስራ በመስራቱ ወደ ጦርነት ሊገባ አይችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።
" ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ ብለዋል ... እንዲህ ብለዋል ተብሎ የተለያየ ትርጉም ከተሰጠው በኃላ ይሄን በሚመለከት ህወሓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን engage አድርጓል። " ብለዋል።
" በዚህ ደረጃ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባን ነገር እንደሌለ ግልጽ ሆኗል " ሲሉ አክለዋል።
" ህወሓት አንድ ድርጅት ነው " ያሉት አቶ አማኑኤል አሰፋ ፥ " የተለያዩ ስራዎች ሊሰራ ይችላል ፤ ያን ስራ በሚመለከት መወያየትና መነጋገር ይቻላል። ችግሮች ካሉ ለመወያየት እና አብሮ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የተጀመረ የሰላም ማዕቀፍ አለ ያን መሰረት አድርጎ መወያየት እና መፍታት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ የተደረጉ ጦርነቶች ናቸው የዛሬውን ችግር ያመጡት " የሚሉት አቶ አማኑኤል " ብዙ ችግር ባለበት ሀገር ሆነን አሁንም ጦርነት ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል።
" ስለተሰበሰብን ፣ አንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ህወሓት የሆነ ነገር ስላደረገ ጦርነት አይመጣም ፤ እንዴት ጦርነት በዚህ ልክ ርካሽ ይሆናል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው ፤ ውስጣዊ ችግሩን ለመፍታት ነው ጉባኤ የሚደረገው " ሲሉ ለወይን በሰጡት ቃለ መጠየቅ ተናግረዋል።
#TPLF #TIGRAY

ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ? " ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል። አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ…
#TPLF
በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ።
ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል።
ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም ብሎ የቦርዱን አሰራር ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እና በጉባኤው የሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎች ተቀባይነት እንደማይኖረው አሳውቆ ነበር።

#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም…
#TPLF
በሊቀ-መንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በተመራውና ለ7 ቀናት በቆየው የህወሓት 14ኛው ጉባኤ አዳዲስ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ተመርጠዋል።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር እና ጉባኤውን ሲቃወሙ የቆዩትን አቶ ተኽለብርሃን ኣርኣያ ተነስተው አቶ ገብረ ካሕሳይ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
አሁን ከሊቀመንበር ቦታቸው ተነስተው በአቶ ገብረ የተተኩት አቶ ተኽለብርሃን ይመሩት የነበረው የቁጥጥር ኮሚሽን ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን ፥ " ጤናማ ያልሆነ ሂደት ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር ስለማይችል የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ነው " በማለት ከጉባኤው ራሱን ማግለሉን ይታወሳል።
በሌላ በኩል ፥ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ ፤ በጉባኤው ላይ ያልተሳተፉ አባላትን አግዷል።
" ጉባኤው እንዳይካሄድ እንቅፋት ፈጥሯል " ያለውን ቡድን ነው ያገደው።
ያታገዱት አባላት ጥያቄቸውን በጹሁፍ የሚያቀርቡ ከሆነ ወደ አባልነታቸው ሊመለሱ ይችላሉ ብሏል።
ቀደም ብሎ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጉባኤውን እንደማይሳተፉ ማሳወቃቸው ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትም ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል።

#TPLF #Tigray
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።
አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል።
ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።
በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው " ብለው በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን " ካቋቋሙ ወገኖች ጋር ውይይት ያስፈልጋል " ብለዋል።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግ ራይ ሠራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።
በጉዳዩ ዙሪያ ከፌድራሉ መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ፥ " እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።
ከሰሞኑን ህወሓት " የድርጅቱን አመራሮች የከፋፈለ ነው " የተባለለትን 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን በድጋሚ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን በማንሳት አቶ አማኑኤል አሰፋን እንዲሁም ሌሎችንም አዳዲስ የማዕከላዊና የስራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ይታወቃል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን ቀደም ብሎ ጉባኤው ሳይጀመር የቦርዱን አሰራር ላልተከተለ ጉባኤ እና በጉባኤው ለሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎችና ለውጦች እውቅና እንደማይሰጥ በይፋ አሳውቋል።
#TPLF #EthiopiaInsider

#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ። ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ…
#TPLF #Tigray
በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ።
በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ " ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ኢህጋዊ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ " ሲል አስጠንቅቋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ መሾማቸው ዘግበናል።
ነሃሴ 18/2016 ዓ.ም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዋና አስተዳዳሪና በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት ተክላይ ገ/መድህን ምትክ የክልሉ የስፓርት ኮሚሽን ኮምሽነር የነበሩት ተኽላይ ፍቓዱ ተሹመዋል።
ትግራይ ካሉዋት ሰባት የዞን አስተዳደሮች በአሁኑ ጊዜ ስድስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ የመቐለ ከተማ ብቻ በቅርቡ በተካሄደ ጉባኤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይመራል።

#TPLF #እንዳስላሰሽረ
በሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተከለከለ።
ህወሓት ሰላማዊ ስልፍ ለማካሄድ ከጳጉሜን 3 - 5 ባሉት ቀናት የጠየቀ ሲሆን ሰልፉ የሚካሄድበት ቦታ ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ ነው።
የህወሓት ፅህፈት ቤት እንዳስላሰ ሽረ ቅርንጫፍ ነሃሴ 29/2016 ዓ.ም በፃፈው የሰላማዊ ሰልፍ የፍቃድ ደብዳቤ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በሰላማዊ መንገድ ድምፁ ለማሰማት መፈለጉ ያትታል።
ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ፍቃድ በጠየቀበት ሰላማዊ ሰልፍ ፦
"
- ከባቢያዊ መለያየትና አገር የሚበትኑ ተግባራት ይቁሙ !
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የፀለምቲና ራያ ተመላሽ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ይጠበቅ !
- የህዝበኝነት ፓለቲካ በትግራይ እንቃወማለን !
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ይተግበር !
- ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመለት ዓላማ ይተግብር !
- ህወሓትን ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- ህወሓት ሰላምን ይደግፋል !
- ጦርነት የሚናፍቅ የህወሓት መሪ የለም ! "
የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እንደሚያሰማ በፍቃድ መጠየቂያ ደብዳቤው ላይ ገልጿል።
ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ለጠየቀው ' ሰላማዊ ሰልፍ ' የማካሄድ ጥያቄ መልስ የሰጠው የእንዳስላሰ ሽረ ከተማ አስተዳደር በወቅቱ ባለው የፓለቲካ ትኩሳት እና የአዲስ ዓመት መለወጫ በመሆኑ ምክንያት የፀጥታ ሃይሉ የተደራረቡ ስራዎች ስላሉበት ሰላማዊ ስልፉ እንዳልተፈቀደ አሳውቋል።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልኡክ በተምቤን ዓብዩ ዓዲ ዓዲግራትን ማይጨው ካካሄዳቸው ህዝባዊ ውይይቶች በመቀጠል በአክሱምና በእንዳስላሰ ሽረ ከተማዎች ለማካሄድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም አቶ ጌታቸው ባጋጣመቸው የጤና እክል ምክንያቱ ውይይቱ ለሌላ ጊዜ መዛወሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መዘገቡ ይታወሳል።